Get Mystery Box with random crypto!

ምቀኛም የባሰ በህይወት ዉጣ ዉረድ ዉስጥ ሰዎች አንዳንዴ ከመሬት ተነስተዉ ይጠሉሃል! (እደግመዋ | 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

ምቀኛም የባሰ

በህይወት ዉጣ ዉረድ ዉስጥ ሰዎች አንዳንዴ ከመሬት ተነስተዉ ይጠሉሃል! (እደግመዋለሁ) ከመሬት ተነስተዉ ይጠሉሃል፡፡

በጣም ምርጥ ፀባይ ሊኖርህ ይችላል፡፡ ለሰዎች አሳቢና ቸርም ልትሆን ትችላለህ፣ በክፉ ጊዜ እንኳን ለወዳጅ ለጠላትህም የምትደርስ አይነት ባህሪ ሊኖርህ ይችላል፡፡

ማወቅ ያለብህ ነገር የሆነ የሰዉ ሁል ጊዜ ስላንተ መልካምነት ሲወራ ያስጠላዋል፣ አይደላዉም፣ ይደብረዋል፣ ራስ ምታቱ ይነሳል፡፡

ይሔ ሰው ከምቀኞች ግሩፕ ዉስጥ እንዳትቀላቅለዉ፡፡ ምቀኛ ማለት በምትሰራዉ መልካም ነገር ቀንቶ ክፉ የሚያስብ ነዉ፡፡ ምቀኛ ለማፍራት ቢያንስ የተሻለ ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል፡፡

እነዚህ ሰዎች ግን የምትሰራዉ ነገር በሙሉ አይመቻቸዉም፡፡ ብትስቅም ብታለቅስም አይደላቸዉም፡፡

ብቻ አንተነትህ ከነአካቴዉ በዚህ ምድር ላይ በመፈጠሩ ይጠሉታል፡፡ ምቀኞች ከምታደርገዉ ነገር ቅናት ሲይዛቸዉ እነዚህ ልዩ ሰዎች ግን ከማንነትህ ጋር ቅናት ይይዛቸዋል! ምናለ ባልተፈጠረ! ዉሃ ሆኖ በቀረ! ይላሉ፡፡

የእነዚህ ሰዎች መሰረታዊ ችግር አንተን ሆነዉ ባለመገኘታቸዉ ብቻ ነዉ! አንተን ቢሆኑ ደስ ባላቸዉ ግን አንተን መሆን አይችሉም! ስለዚህ እነዚህን ሰዎች ጠንቀቅ በላቸዉ፡፡

ለምሳሌ ምቀኛህ “ቪዛዉ አልተሳካለትም እሰይ! የታባቱ እዚቹ አፈር መስሎ ይኖራታል!” ሲልህ ያኛው የባሰው ሰው ግን “ምነዉ በሞተ! በጣም እኮ ነዉ የሚያስጠላኝ...እንኳን ቪዛ መኖርም ባይሳካለት የምረካም አይመስለኝ!” ይልሃል !

ከእንደዚህ አይነቱ ይሰውረን

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር