Get Mystery Box with random crypto!

ባዶ ጩኸት አንድ ተማሪ ሂሳብ አስተማሪው በማስተማር ላይ ሳለች አንድ ትንሽ ስህተት በመሳሳቷ በጣ | 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

ባዶ ጩኸት

አንድ ተማሪ ሂሳብ አስተማሪው በማስተማር ላይ ሳለች አንድ ትንሽ ስህተት በመሳሳቷ በጣም ሳቀባት ።

እንዴት እንደዚህ አይነት ስህተት ትሳሳቻለሽ አኔ ካንቺ የተሻለ የሂሳብ ቀመሮችን መስራት እንደምችል ታዉቂያለሽ? ሰዎች 'ከባባድ' ናቸዉ የሚሏቸዉን መፃህፍትን ሳይቀር እንዳነበብኩ አልሰማሽም ??”

እያለ ያደረገዉንና ጥግ የደረሰ እዉቀት ባለቤት መሆኑን በድፍረት መናገር ጀመረ ፡፡

አስተማሪዋም ያወራዉን ሁሉ አዳምጣ ከጨረሰች በኋላ እንዲህ አለችዉ “ሂድና ግማሽ ዉሃ በዚህ ኮዳ ይዘህ ና!”ሔዶ ግማሽ ዉሃ አመጣ...ኮዳዉን አንስታ አወዛወዘችውና ፡፡ “ምን ተሰማህ ?” አለችዉ ።

“ የዉሀዉ ድምፅ ይሰማኛል” አላት “ጥሩ! አሁን ደግሞ ይህንን ኮዳ እስከአፉ ድረስ ሞልተኸዉ ና” አለችዉ፡፡ ሄዶ ሞልቶ ሲመጣ ኮዳዉን ተቀብላ ስታወዛዉዘዉ አየና “ አሁን ምንም ድምፅ የለዉም አላት፡፡

እሷም እንዲህ አለችው ...“እዉቀትም እንደዚሁ ነዉ፡፡ በትንሹ ወይም በግማሹ የሚያዉቁ ሰዎች ብዙ ያወራሉ... 'ካልተደመጥኩ! ፣ጆሮ ካልተሰጠኝ' ብለዉ ችግር ይፈጥራሉ...

ነገር ግን ምርጥ ጭንቅላትና የበሰለ እዉቀት ያላቸዉ ባገኙት ነገር ላይ በሙሉ 'እኔ እኔ እኔ!' እያሉ እጃቸዉን አያወጡም፡፡

ማዉራት ሲኖርባቸዉ ብቻ ጥቂት ያወራሉ፡፡ በእዉቀት እስከ ገደፉ የተሞሉ ሰዎች ጩኸት አያበዙም፡፡

ረጋ ያሉ ናቸዉ! ታዋቂዉ ፈላስፋ ፕላቶ እንዳለዉ ‘ ብልህ ሰዎች ማዉራት ያለባቸዉ ሃሳብ ስላለ ብቻ ያወራሉ ሞኞቹ ግን ማዉራት ስላለባቸዉ ያወራሉ ’”
ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር