Get Mystery Box with random crypto!

🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

የቴሌግራም ቻናል አርማ lailaha_ilellah_islamic — 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿
የቴሌግራም ቻናል አርማ lailaha_ilellah_islamic — 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿
የሰርጥ አድራሻ: @lailaha_ilellah_islamic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.39K
የሰርጥ መግለጫ

#ረውደቱል_ኢስላም_የቁርአን_እና_የተርቢያ_ማዕከል ሲሆን በደሴ በአሁን ሰአት ትውልዱን በዲን በማነፅ ላይ ይገኛል። ይሁንና ተደራሽነቱን ለማስፋት በሶሻል ሚዲያው ብቅ በማለት ኡማውን ማገልገል ይፈልጋል።
#አላማችን
● በማዕከሉ የሚሰጡ ትምህርቶች እንዲሁም ተሰምተው ታይተው የማይታወቁ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በዩቲዩብ በማዘጋጀት ለሙስሊሙ ኡማ ማድረስ https://youtube.com/@farzanmedia

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-06 20:07:15 ውሐን ቁጭ ብሎ መጠጣት የሚያስገኜው ጤናዊ ፋይዳ

ውሐ ስንጠጣ ቆመን ከምንጠጣ ይልቅ ቁጭ ብለን ብንጠጣ የሚከተለውን ጥቅም እናገኛለን፡፡

❖ውሐን #ቁጭ ብለን ብንጠጣ ጥምን ይቆርጣል፤ ምክንያቱም ቆመን ስንጠጣ ውሀው በፍጥነት ነው የሚጓዘው ስለዚ የደረቀውን የምግብ ቱቦ ላያርሰው ይችላል፡፡

ቆመን በምንጠጣበት ጊዜ ከላይ ተንደርድሮ የሚመጣው ውሀ በሆዳችን ግርግዳ እና በዙሪያው ባሉ አካሎች በረጅም ጊዜ ልምድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤

#ልብ በሉ ትንሽ የውሀ ጠብታ እንኳን ከጊዜ ብዛት ድንጋይ ትሰብራለች ብዛት ያለው ውሀ ደግሞ በፍጥነት ሲንደረደር ተርባይን ያሽከረክራል ቁጭ ስንልና ስንቆም የሆዳችን ፖዚሽን ይለያያል ይህም ቆመን ስንጠጣ ከላይ የመጣው ውሀ ሆድ ውስጥ ሳይቆይ በቀጥታ ወደትንሹ አንጀት የመጀመሪያው ክፍል #Duodenum ይገባል ቁጭ ብለን ስንጠጣ ደግሞ ውሀው ሆድ ውስጥ የመቀመጥ እድል ይኖረዋል በዚህም ሆድ ውስጥ በሚገኙ አሲዶች ይጣራል ይህም ለኩላሊት ጤንነት ጠቃሚ ነው ቆሞ መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያለውን የፈሳሽ ባላንስ ያዛባል ይህም በረጅም ጊዜ #Arthritis ለተባለ የመገጣጠሚያ ህመም ያጋልጣል። የመሳሰሉት.....

ወሰላሙ አለይኩም
234 views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 19:19:08 የዓለም ሙስሊሞችን ያስቆጣው የህንድ ሙስሊም ጠልነት
==========================================
(በነብያችን ﷺ ድርድር የለም! )
የህንድን ምርቶች ማንም እንዳይገዛ! መልዕክቱን እናሰራጭ!
||
የሂንዱ እምነት ተከታዮች በብዛት የሚኖሩባት ሃገረ ህንድ ከበፊት ጀምሮ በበርካታ ሙስሊም ጠል ተግባሮቿ ትታወቃለች። በሃገሪቱ ውስጥ ባንኩም ታንኩም፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነቱም በብዛት በዚሁ እምነት ተከታዮች እጅ የወደቀ ነው። እንደ Worldometer የ2022 መረጃ ከሆነ የሃገሪቱ የህዝብ ብዛት 1, 406, 087, 920 ነው። ከዚህ መካከል 2021 ላይ በወጣው መረጃ መሠረት 209 ሚሊዮን ያክሉ ሙስሊም እንደሆነ ይገመታል። ይህ ማለት የህንድ ሙስሊም ብቻውን በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ 2ኛ ደረጃ የሆነችውን የሃገራችንን ኢትዮጵያን አጠቃላይ ህዝብ እጥፍ ይሆናል እንደማለት ነው።


ይህ በሆነባት ህንድ የሃገሪቱ ገዢ ፓርት ቢጄይፒ (Bharatiya Janata Party - BJP) ቃለ አቀባይ የሆነችው ኑፐር ሻርማ (Nupur Sharma) በአንድ የቴሌቪዥን የክርክር መድረክ ላይ ቀርባ ነቢያችንን ﷺ እና እናታችንን ዓኢሻህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ስማቸውን የሚያጠለሽ ንግግር አድርጋ ነበር።
የሞዲ ፓርቲ BJP ባለስልጣን የሆነው Naveen Kumar Jindalም በትዊተር ገጹ ሙስሊም ጠል መልዕክት አስተላልፎ ነበር።


ይህ የህንድ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ድርጊት ሙስሊሙን ዓለም አስቆጥቷል። በተለይም የባህረ ሰላጤው ሃገራት ቁጣቸውን በአስቸኳይ ከመግለፅ ባሻገር ወዲያውኑ በውጭ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል። የኩዌይት፣ የኳታር፣ የኦማን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስታት በሃገራቸው የሚገኘውን የህንድ አምባሳደር በመጥራት ማብራሪያ ጠይቀዋል። ድርጊቱንም የሚያወግዝ መግለጫ አውጥተዋል። ኳታር የህንድ መንግስት ይህንን ጸረ ሙስሊም ድርጊት በአደባባይ በህዝብ ተቃውሞ ሊያወግዝ ይገባል ብላለች። የፓኪስታን፣ የአፍጋኒስታን ኢስላማዊ ኢሚሬት፣ የባኅረ ሰላጤው ሃገራት ጥምረት Gulf Cooperation Council - GCC፣ Organization of Islamic Cooperation - OIC፣ የባንግላድሽ፣ የግብጹ አልአዝሃርና ሌሎች ሙስሊም ሃገራትና ኢስላማዊ ተቋማት ድርጊቱን በጥብቅ አውግዘዋል። ሁሉም ሙስሊም የህንድን ምርቶች እንዳይገዛና ከመደርደሪያው አውጥቶ እንዲጥል አዘዋል። ይህ የመጀመሪያውና ቀላሉ በህንድ ላይ የሚጥሉት ማዕቀብ መሆኑን አሳውቀዋል። የህንድ መንግስት ግን በዚህ ማዕቀብ ብቻ ልቡ ርዷል። ፓርቲው ቃለ አቀባይዋን ከኃላፊነት አግዷል። በትዊተር ገጿ ሙስሊሞችን ለመንካት ፈልጌ ሳይሆን የሂንዱን አምላክ ሺቫን የነኩብኝን ለመንካት በማሰብ ነው በማለት ካስከፋኋችሁ ይቅርታ ብትልም ሰሚ አላገኘችም። ይህ ብቻ በቂ አይደለም ባይ ናቸው ሙስሊም ሃገራት! በህንድ ገዢው ፓርቲ በአንጻሩ በሃገሪቱ አናሳ ሙስሊሞችን በተደጋጋሚ ሲጨቁን ይስተዋላል ብለዋል። አጥፊዎች ያሻቸውን ከተናገሩ በኋላ በይቅርታና መሰል ነገር ተደበስብሶ እየታለፈ ቅጣት ካልተጣለባቸው ነገም ሌላው ተነስቶ ላለመናገሩ ዋስትና የለምና እስካሁን ድረስ «የህንድ ምርቶችን አትግዙ፣ ከሱቃችሁ አውጥታችሁ ጣሉ!» የሚለው ዘመቻ አድማሱ እየሰፋ ዓለም አቀፍ እየሆነ መጥቷል። በሃገረ ኦማን የህንድ ምርቶችን ከሱቅ እያወጡ ወደ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ሲጥሉ የሚያሳዩ ቪድዮዎች እየወጡ ነው። የህንድ ኢኮኖሚ እየተመዝገዘገ ይገኛል። ማዕቀቡ ከዚህም በላይ ከሰፋና ዓለም አቀፍ ይዘት እየያዘ ከመጣ፤ ህንድ አይታው የማታውቀው የኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ መግባቷ አይቀሬ ነው። ያላት አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው። በነዚህ ሙስሊም ጠል አካላቶች ላይ ተገቢውን የማያዳግም የሆነ መቀጣጫ እርምጃ መውሰድ ብቻ!



እኛም ሃገር ላይ የህንድ ምርቶች ካሉ ማንኛውም ሙስሊም እንዳይገዛ።


መልዕክቱን ለሁሉም ሙስሊም እናሰራጭ! ይህ ለዓለም ሙስሊሞች የተላለፈ ጥሪ ነው። በውዱ ነቢያችንና ﷺ በእናታችን ዓኢሻህ ቀልድ የለም።
ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ወ ሩሒ ወ ደሚ ወ ነፍሲ ያ ረሲለ-ልሏ'ህ ﷺ


‌‏‌ #إلا_رسول_الله_يا_مودي
587 views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 09:09:15
በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙስሊሞች የቀረበ ጥሪ...
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
#Ethiopia | የኦማን ታላቁ ዓሊም ሙፍቲ ሸይኽ አሕመድ ቢን ሐማድ አል-ኸሊል የሕንድ ገዢው ፓርቲ (BJP) ቃል አቀባዩ ነብዩ ሙሐመድ [ሰ.ዓ.ወ] የሚሰድብ መግለጫ ከሰጠ ቡኃላ በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙስሊሞች ሁሉ ሰበር መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሽይኹ የሕንድ ምርቶችን #Boycott በማድረግ ላይ የረሱልን መልዕክት የተቀበለ፤ በመልካም ስብዕናቸው ተማርኮ በውዴታቸው ሙስሊም ሁሉ አደራቸውን አስተላልፈዋል።

ረሱል [ሰ.ዓ.ወ] ያነወረው የጠ/ሚኒስትር ሙዲን ስርዓት አልበኝነትን በማስተንፈስ ላይ የመጀመሪያ ያሉትን ማዕቀብ ሁሉም ሙስሊም እንዲሳተፍ አደራ ብለዋል።

እኛም የኢትዮጲያ ሙስሊሞች #Boycott ዘመቻውን በመቀላቀል የረሱልን ጠላቶች በኢኮኖሚ ለመዋጋት ከዛሬ ጀምሮ እንቅስቃሴያችንን እንጀምራለን! ሼር በማድረግ ለሁሉም ማድረሰዎን አይርሱ።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
እባካችሁ ይህን መልዕክት ሼር ሼር ያድርጉልኝ !
429 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 21:25:08 የሰው ልጅ ባሕርይ እና የአምላክ ባሕርይ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪይ እና የእግዚአብሔር ባሕርይ ሲነፃፀር።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
እግዚአብሔር... እና... ኢየሱስ ክርስቶስ የተለያዩ ማንነቶች እና ምንነቶች ናቸው ያላቸው።

እስቲ ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት።

ብዙ ክርስቲያን ወገኖቻችን ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር ራሱ ነው (ዮሐ 10:30) ብለው ይናገራሉ።

ነገር ግን ንግግራቸው የተሳሳተ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ ።

ምክንያቱም ኢየሱስ እና እግዚአብሔር በጣም የተለያዬ ባሕርይ ያላቸው #ማንነቶች እና #ምንነቶች ናቸው።

እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመለከት።

ምሳሌ አንድ
እግዚአብሔር አምላክ እንጂ * #ሰው_አይደለም።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
— ሆሴዕ 11፥9

አምላክ ሰው ካልሆነ ሰው ደግሞ አምላክ መሆን አይችልም ማለት ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም።

*አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን #ሰው_ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?
ዮሐንስ 8:40
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ምሳሌ ሁለት

*እግዚአብሔር አይደክምም አታክትምም
እግዚአብሔር አይደክምም አይታክትም።
ኢሳያስ 40:28።

ኢየሱስ ደሞ ይደክማል ይታክተዋል
“ "ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ "ደክሞ" በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤
— ዮሐንስ 4፥6

ምሳሌ ሦስት

እግዚአብሔር "አይበላም" "አይጠጣም።
“የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?”
— መዝሙር 50፥13

ኢየሱስ ግን ይበላል ይጠጣል።
ሉቃስ 24
⁴² እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤
⁴³ ተቀብሎም በፊታቸው *በላ*።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ምሳሌ አራት
እግዚአብሔር አይተኛም አያንቀላፋም።
እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ "አይተኛም" "አያንቀላፋምም።”
— መዝሙር 121፥4

ኢየሱስ ግን ይተኛል ያንቀላፋል።
“እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።”
— ማርቆስ 4፥38

ምሳሌ አምስት

እግዚአብሔር "ቸር" ነው።
እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።”
— መዝሙር 25፥8

ኢየሱስ ግን"ቸር" አይደለም።
“ኢየሱስም፦እኔን ስለ ምን "ቸር" ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።”
— ማርቆስ 10፥18
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ምሳሌ ስድስት
እግዚአብሔር በክፉ መንፈስ አይፈተንም
“ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ *እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም*።”
— ያዕቆብ 1፥13

ኢየሱስ ግን በሰይጣን ይፈተናል።
“አርባ ቀን ከዲያብሎስ *ተፈተነ*። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።”
— ሉቃስ 4፥2

ምሳሌ ሰባት
እግዚአብሔር የሰው ልጅ አይደለም።
“ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ *የሰው ልጅ አይደለም*።
— ዘኍልቁ 23፥19

ኢየሱስ ግን የሰው ልጅ ነው።
*“የሰው ልጅም ስለ ሆነ* ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።”
— ዮሐንስ 5፥27
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
==================

ታዲያስ ክርስቲያን ወገኖቼ ሆይ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ለይ ቅል (የተለያየ ማንነትና ምንነት) የሆነ ባሕርይ ያላቸው "ማንነቶች" እና "ምንነቶች" ሆኖ ሳለ እንዴት እግዚአብሔር እና ኢየሱስ አንድ ናቸው ትላላችሁ??

ወይስ መጽሐፉን አታነቡትም?

ጊዜው ሰይመሽባችሁ ወደ አሏህ ተመለሱ።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
{ Qur'an5:75}

ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይሁን።
{ Qur'an 20:47}

ቴሌ ግራም ይቀላቀሉ።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
826 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 20:15:26 ╔═══════════════╗
የረሱል ኒካህ ዕለት
══════════════

የሙሽሪት እና የሙሽራው አጎቶች ተሰባስበው ወጉን ሊጀምሩ እርስ በርስ እየተያዩ ነው። የሙሽራው አጎት የሆነው አቡ ጣሊብ ከመሐል ብድግ ብሎ ቆመ።
ስፍራው ላይ የታደሙት ሰዎች አቡ ጣሊብ ለመናገር እንደቆመ ሲረዱ ፅሞናን አሰፈሩ። አቡ ጣሊብም ንግግር ጀመረ፦ "የኢብራሂም ዝርያዎች እና የኢስማዒል ፍሬዎች ያደረገን ጌታ የክብርነት ቤቱ ጠባቂያዎች እና የጎብኚዎቹም ተቀባይ ስላደረገን ጌታችንን እናመሰግናለን። በመቀጠል ይህ የወንድሜ ልጅ ምንም እንኳ ደሃ ቢሆንም ከመካ ቁረይሽ ወጣቶች ብታነፃፅሩት ብጤ የሌለው ሲሆን በልግስናም፣ በትህትናም፣ በክብርም ማንም አይስተካከለውም። ባለ ፀጋነት እንደሆን የቀን ጥላ ማታ ጠፊ ነው። ልጃችን ልጃችሁን የከጀለ ሲሆን ልጃችሁም ልጃችንን ከጅላለች እና የሻችሁን የመህር ተመን ወስኑ ከፋዩ እኔ ነኝ" ብሎ የሽምግልና ሂደቱን አስጀመረ።

የሙሽሪት አጎት እሷን ወክሎ ሊድራት ከተሰየመበት መንበር ተቀምጦ እንዲህ አለ፦ "ባወሳኋቸው ፀጋዎች ሁላ ለጌታችን ምስጋና ይገባው። የመላው አረብ በላጮች ስላደረገንም እያመሰገንን እናንተም በኑ ሀሺሞች የዐረብ ሁላ ቁንጮ መሆናችሁን እንመሰክራለን። እኛም ከናንተ በሚያስተሳስረን የዝምድና ገመድ ለመተሳሰር ከጅለናል" ብሎ ሽምግልናውን ተቀበለ።
ንግግሩን ቀጠለ። በስፍራው ወደታደሙ የቁረይሽ ነገዶች ፊቱን አዙሮም፦ "እናንተ የቁረይሽ ነገዶች ሆይ! እኔ ኸዲጃ ኹወይሊድን ለሙሐመድ ዐብዱላህ የዳርኩ ስሆን እናንተም ምስክር ሁኑ" ብሎ ለኸዲጃ የአለማቱን ክብረት ሸለማት።

ይኼኛው የረሱል (صلى الله عليه وسلم) ሰርግ ቢያመልጠንም ነገ በአኪራ በጀነት እልፍኞች ውስጥ የሚደገሰውን ሰርጋቸውን በክብር እንድናጅባቸው አላህ ይወፍቀን።

═════════════════
ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንታችን ነው

https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like Comment Share
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት
╚═══════════════╝
381 viewsedited  17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 20:12:24 ወንዶቹ እንዲህ ነበሩ

ዑመር ሙኽታር በችሎት ፊት ቀርበው ከዳኛው ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

ዳኛው - ከጣሊያን ጋር ተዋግተሀል?
ዑመር ሙኽታር - አዎ
ዳኛው - ሰዎችስ እንዲፋለሙ አነሳስተሀል?
ዑመር ሙኽታር - አዎ
ዳኛው - በዚህ ተግባርህ የሚከተልህን ቅጣት ታውቃለህ?
ዑመር ሙኽታር - አዎ አውቃለሁ
ዳኛው - ከጣሊያን ጋር ስንት ዓመታትን ተዋግተሀል?
ዑመር ሙኽታር - ከ 20 ዓመታት በላይ
ዳኛው - ቅጣትህ ሞት መሆኑንስ ታውቃለህ?
ዑመር ሙኽታር - በሚገባ አውቃለሁ
ዳኛው - ይህ መጨረሻህ በመሆኑ አዝናለሁ
ዑመር ሙኽታር - ይህ ሕይወቴን የማጠናቀቅበት በጣም ጥሩው መንገድ በመሆኑ እደሰታለሁ
ዳኛው - ሙጃሂድ ጓደኞችህ የጂሃድ ትግላቸውን እንዲያቆሙ ደብዳቤን ጻፍና በምህረት ልልቀቅህ
ዑመር ሙኽታር - በየሰላቱ ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን የምትመሰክረው ጣቴ ባጢልን መፃፍ ከቶ እንዴት ይቻላታል?

═════════════════
ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንቴ ነው

https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like Comment Share
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት
╚═══════════════╝
337 viewsedited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ