Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ልጅ ባሕርይ እና የአምላክ ባሕርይ። የኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪይ እና የእግዚአብሔር ባሕርይ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

የሰው ልጅ ባሕርይ እና የአምላክ ባሕርይ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪይ እና የእግዚአብሔር ባሕርይ ሲነፃፀር።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
እግዚአብሔር... እና... ኢየሱስ ክርስቶስ የተለያዩ ማንነቶች እና ምንነቶች ናቸው ያላቸው።

እስቲ ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት።

ብዙ ክርስቲያን ወገኖቻችን ኢየሱስ ማለት እግዚአብሔር ራሱ ነው (ዮሐ 10:30) ብለው ይናገራሉ።

ነገር ግን ንግግራቸው የተሳሳተ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ ።

ምክንያቱም ኢየሱስ እና እግዚአብሔር በጣም የተለያዬ ባሕርይ ያላቸው #ማንነቶች እና #ምንነቶች ናቸው።

እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመለከት።

ምሳሌ አንድ
እግዚአብሔር አምላክ እንጂ * #ሰው_አይደለም።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
— ሆሴዕ 11፥9

አምላክ ሰው ካልሆነ ሰው ደግሞ አምላክ መሆን አይችልም ማለት ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም።

*አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን #ሰው_ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?
ዮሐንስ 8:40
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ምሳሌ ሁለት

*እግዚአብሔር አይደክምም አታክትምም
እግዚአብሔር አይደክምም አይታክትም።
ኢሳያስ 40:28።

ኢየሱስ ደሞ ይደክማል ይታክተዋል
“ "ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ "ደክሞ" በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤
— ዮሐንስ 4፥6

ምሳሌ ሦስት

እግዚአብሔር "አይበላም" "አይጠጣም።
“የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?”
— መዝሙር 50፥13

ኢየሱስ ግን ይበላል ይጠጣል።
ሉቃስ 24
⁴² እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤
⁴³ ተቀብሎም በፊታቸው *በላ*።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ምሳሌ አራት
እግዚአብሔር አይተኛም አያንቀላፋም።
እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ "አይተኛም" "አያንቀላፋምም።”
— መዝሙር 121፥4

ኢየሱስ ግን ይተኛል ያንቀላፋል።
“እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።”
— ማርቆስ 4፥38

ምሳሌ አምስት

እግዚአብሔር "ቸር" ነው።
እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።”
— መዝሙር 25፥8

ኢየሱስ ግን"ቸር" አይደለም።
“ኢየሱስም፦እኔን ስለ ምን "ቸር" ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።”
— ማርቆስ 10፥18
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

ምሳሌ ስድስት
እግዚአብሔር በክፉ መንፈስ አይፈተንም
“ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ *እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም*።”
— ያዕቆብ 1፥13

ኢየሱስ ግን በሰይጣን ይፈተናል።
“አርባ ቀን ከዲያብሎስ *ተፈተነ*። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።”
— ሉቃስ 4፥2

ምሳሌ ሰባት
እግዚአብሔር የሰው ልጅ አይደለም።
“ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ *የሰው ልጅ አይደለም*።
— ዘኍልቁ 23፥19

ኢየሱስ ግን የሰው ልጅ ነው።
*“የሰው ልጅም ስለ ሆነ* ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።”
— ዮሐንስ 5፥27
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
==================

ታዲያስ ክርስቲያን ወገኖቼ ሆይ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ለይ ቅል (የተለያየ ማንነትና ምንነት) የሆነ ባሕርይ ያላቸው "ማንነቶች" እና "ምንነቶች" ሆኖ ሳለ እንዴት እግዚአብሔር እና ኢየሱስ አንድ ናቸው ትላላችሁ??

ወይስ መጽሐፉን አታነቡትም?

ጊዜው ሰይመሽባችሁ ወደ አሏህ ተመለሱ።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
{ Qur'an5:75}

ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይሁን።
{ Qur'an 20:47}

ቴሌ ግራም ይቀላቀሉ።
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC