Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ሙስሊሞችን ያስቆጣው የህንድ ሙስሊም ጠልነት ============================ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

የዓለም ሙስሊሞችን ያስቆጣው የህንድ ሙስሊም ጠልነት
==========================================
(በነብያችን ﷺ ድርድር የለም! )
የህንድን ምርቶች ማንም እንዳይገዛ! መልዕክቱን እናሰራጭ!
||
የሂንዱ እምነት ተከታዮች በብዛት የሚኖሩባት ሃገረ ህንድ ከበፊት ጀምሮ በበርካታ ሙስሊም ጠል ተግባሮቿ ትታወቃለች። በሃገሪቱ ውስጥ ባንኩም ታንኩም፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነቱም በብዛት በዚሁ እምነት ተከታዮች እጅ የወደቀ ነው። እንደ Worldometer የ2022 መረጃ ከሆነ የሃገሪቱ የህዝብ ብዛት 1, 406, 087, 920 ነው። ከዚህ መካከል 2021 ላይ በወጣው መረጃ መሠረት 209 ሚሊዮን ያክሉ ሙስሊም እንደሆነ ይገመታል። ይህ ማለት የህንድ ሙስሊም ብቻውን በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ 2ኛ ደረጃ የሆነችውን የሃገራችንን ኢትዮጵያን አጠቃላይ ህዝብ እጥፍ ይሆናል እንደማለት ነው።


ይህ በሆነባት ህንድ የሃገሪቱ ገዢ ፓርት ቢጄይፒ (Bharatiya Janata Party - BJP) ቃለ አቀባይ የሆነችው ኑፐር ሻርማ (Nupur Sharma) በአንድ የቴሌቪዥን የክርክር መድረክ ላይ ቀርባ ነቢያችንን ﷺ እና እናታችንን ዓኢሻህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ስማቸውን የሚያጠለሽ ንግግር አድርጋ ነበር።
የሞዲ ፓርቲ BJP ባለስልጣን የሆነው Naveen Kumar Jindalም በትዊተር ገጹ ሙስሊም ጠል መልዕክት አስተላልፎ ነበር።


ይህ የህንድ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ድርጊት ሙስሊሙን ዓለም አስቆጥቷል። በተለይም የባህረ ሰላጤው ሃገራት ቁጣቸውን በአስቸኳይ ከመግለፅ ባሻገር ወዲያውኑ በውጭ ጠንከር ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል። የኩዌይት፣ የኳታር፣ የኦማን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስታት በሃገራቸው የሚገኘውን የህንድ አምባሳደር በመጥራት ማብራሪያ ጠይቀዋል። ድርጊቱንም የሚያወግዝ መግለጫ አውጥተዋል። ኳታር የህንድ መንግስት ይህንን ጸረ ሙስሊም ድርጊት በአደባባይ በህዝብ ተቃውሞ ሊያወግዝ ይገባል ብላለች። የፓኪስታን፣ የአፍጋኒስታን ኢስላማዊ ኢሚሬት፣ የባኅረ ሰላጤው ሃገራት ጥምረት Gulf Cooperation Council - GCC፣ Organization of Islamic Cooperation - OIC፣ የባንግላድሽ፣ የግብጹ አልአዝሃርና ሌሎች ሙስሊም ሃገራትና ኢስላማዊ ተቋማት ድርጊቱን በጥብቅ አውግዘዋል። ሁሉም ሙስሊም የህንድን ምርቶች እንዳይገዛና ከመደርደሪያው አውጥቶ እንዲጥል አዘዋል። ይህ የመጀመሪያውና ቀላሉ በህንድ ላይ የሚጥሉት ማዕቀብ መሆኑን አሳውቀዋል። የህንድ መንግስት ግን በዚህ ማዕቀብ ብቻ ልቡ ርዷል። ፓርቲው ቃለ አቀባይዋን ከኃላፊነት አግዷል። በትዊተር ገጿ ሙስሊሞችን ለመንካት ፈልጌ ሳይሆን የሂንዱን አምላክ ሺቫን የነኩብኝን ለመንካት በማሰብ ነው በማለት ካስከፋኋችሁ ይቅርታ ብትልም ሰሚ አላገኘችም። ይህ ብቻ በቂ አይደለም ባይ ናቸው ሙስሊም ሃገራት! በህንድ ገዢው ፓርቲ በአንጻሩ በሃገሪቱ አናሳ ሙስሊሞችን በተደጋጋሚ ሲጨቁን ይስተዋላል ብለዋል። አጥፊዎች ያሻቸውን ከተናገሩ በኋላ በይቅርታና መሰል ነገር ተደበስብሶ እየታለፈ ቅጣት ካልተጣለባቸው ነገም ሌላው ተነስቶ ላለመናገሩ ዋስትና የለምና እስካሁን ድረስ «የህንድ ምርቶችን አትግዙ፣ ከሱቃችሁ አውጥታችሁ ጣሉ!» የሚለው ዘመቻ አድማሱ እየሰፋ ዓለም አቀፍ እየሆነ መጥቷል። በሃገረ ኦማን የህንድ ምርቶችን ከሱቅ እያወጡ ወደ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ሲጥሉ የሚያሳዩ ቪድዮዎች እየወጡ ነው። የህንድ ኢኮኖሚ እየተመዝገዘገ ይገኛል። ማዕቀቡ ከዚህም በላይ ከሰፋና ዓለም አቀፍ ይዘት እየያዘ ከመጣ፤ ህንድ አይታው የማታውቀው የኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ መግባቷ አይቀሬ ነው። ያላት አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው። በነዚህ ሙስሊም ጠል አካላቶች ላይ ተገቢውን የማያዳግም የሆነ መቀጣጫ እርምጃ መውሰድ ብቻ!



እኛም ሃገር ላይ የህንድ ምርቶች ካሉ ማንኛውም ሙስሊም እንዳይገዛ።


መልዕክቱን ለሁሉም ሙስሊም እናሰራጭ! ይህ ለዓለም ሙስሊሞች የተላለፈ ጥሪ ነው። በውዱ ነቢያችንና ﷺ በእናታችን ዓኢሻህ ቀልድ የለም።
ፊዳከ አቢ ወ ኡሚ ወ ሩሒ ወ ደሚ ወ ነፍሲ ያ ረሲለ-ልሏ'ህ ﷺ


‌‏‌ #إلا_رسول_الله_يا_مودي