Get Mystery Box with random crypto!

ወንዶቹ እንዲህ ነበሩ ዑመር ሙኽታር በችሎት ፊት ቀርበው ከዳኛው ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

ወንዶቹ እንዲህ ነበሩ

ዑመር ሙኽታር በችሎት ፊት ቀርበው ከዳኛው ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

ዳኛው - ከጣሊያን ጋር ተዋግተሀል?
ዑመር ሙኽታር - አዎ
ዳኛው - ሰዎችስ እንዲፋለሙ አነሳስተሀል?
ዑመር ሙኽታር - አዎ
ዳኛው - በዚህ ተግባርህ የሚከተልህን ቅጣት ታውቃለህ?
ዑመር ሙኽታር - አዎ አውቃለሁ
ዳኛው - ከጣሊያን ጋር ስንት ዓመታትን ተዋግተሀል?
ዑመር ሙኽታር - ከ 20 ዓመታት በላይ
ዳኛው - ቅጣትህ ሞት መሆኑንስ ታውቃለህ?
ዑመር ሙኽታር - በሚገባ አውቃለሁ
ዳኛው - ይህ መጨረሻህ በመሆኑ አዝናለሁ
ዑመር ሙኽታር - ይህ ሕይወቴን የማጠናቀቅበት በጣም ጥሩው መንገድ በመሆኑ እደሰታለሁ
ዳኛው - ሙጃሂድ ጓደኞችህ የጂሃድ ትግላቸውን እንዲያቆሙ ደብዳቤን ጻፍና በምህረት ልልቀቅህ
ዑመር ሙኽታር - በየሰላቱ ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን የምትመሰክረው ጣቴ ባጢልን መፃፍ ከቶ እንዴት ይቻላታል?

═════════════════
ይህ ደግሞ የቴሌግራም አካውንቴ ነው

https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
═════════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ
╔═══════════════╗
Like Comment Share
ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት
╚═══════════════╝