Get Mystery Box with random crypto!

Kingdom of God🏥🏥🏥

የቴሌግራም ቻናል አርማ kingdom_ofgod — Kingdom of God🏥🏥🏥 K
የቴሌግራም ቻናል አርማ kingdom_ofgod — Kingdom of God🏥🏥🏥
የሰርጥ አድራሻ: @kingdom_ofgod
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 487
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የተሰቀለውን ኢየሱስን የምንሰብክበት ስፍራ ነው ።
መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎች ጥበብን ይሻሉ👉 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይህ ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው.
1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ1:22
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-20 08:13:23 እንግዲህ ሁሉን በትጋት እናድርገው!

አንድን ነገር ማድረግና አንድን ነገር በትጋት ማድረግ ልዩነት አለው።ድርጊቶቻችሁን ውጤት እንዲኖራቸው የሚያደርገው ማድረጋችሁ ብቻ ሳይሆን በትጋት ማድረጋችሁ ነው።

በትጋት የማይደረግ ማንኛውም ነገር ውጤት አልባ ነው።ለአንድ ሥራ ዋጋ የሚሰጠው ትጋት ይባላል።ትጋት ከሌለ ውጤት የለም ውጤት ከሌለ ደግሞ መቀጠል የለም።

የምታድርጉትን የእግዚአብሔርን ነገር ለማድረግ ያህል አታድርጉት እርሱን በትጋት አድርጉት።

ሮሜ 12
⁷ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤
⁸ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።
750 views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 07:52:48 ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ።መከራህን ለእግዚአብሔር ደስታህን ለዓለም አታድርግ።ሆኖም ዓለም በኃጢአት ስታደክምህ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ።ህፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም በሃጢአት ስትቆሽሽ ወደ መሀሪው ጌታህ ሽሽ እርሱም ይምርሃል።

“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።ኢሳይያስ 1፥18
1.3K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 14:05:03 አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ

ትናንትና ዛሬ እንዳይደገም ያለፉት ዓመታት ውጤቶች በሚመጡት ዓመታት እንዳይደገሙ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ።

“አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። ኢዮብ 22፥21

ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ማለት በተሰጣችሁ የእግዚአብሔር መንግስት የህይወት ስርአት መመላለስ እንጂ ቤተክርስቲያን መመላለስ አይደለም።

እግዚአብሔር ከሰጣችሁ የህይወት ስርአት ጎድላችሁ በእግዚአብሔር መንግስት መመላለስ ክብር አይደለም።ሰው በእግዚአብሔር ፊት ሙሉ የሚሆነው እግዚአብሔር በሰጠው የህይወት ስርአት በእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ቤት ሲመላለስ ነው።

አሁን ይህ ትውልድ የሚያስፈልገው በቤቱ መመላለስ ሳይሆን በፊቱ መመላለስ ነው።
538 views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 16:11:34 ከያዝኩት እግዚአብሔር የያዘኝ እግዚአብሔር ይበልጣል፡፡ከእግዚአብሔር ጋር እየቀጠልኩ ያለሁት እኔ በያዝኩት ልክ ሳይሆን እርሱ በያዘኝ ልክ ነው፡፡ከፀሐይ በታች ያለ ሀይል ሊያስቆመኝና
ሊገድበኝ አይችልም ምክኒያቱም ያመንኩትን ደግሞም የያዘኝን አውቀዋለሁና፡፡

ኢሳይያስ 41
¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
595 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 06:13:53 Loyalty ምንድን ነው?

የማይከዳ ማንነት፣በሁኔታዎች የማይለወጥ፣የማይቀያየር ወጥ የሆነ ባህሪ፣የማይወጣና የማይወርድ ስሜት፣ፍፁም የሆነ ግልፅነት፣በስሜት ላይ ያልተመሰረተ
ውሳኔ፣አንድ መልክ አንድ ድርጊት የተሞላ ከራስ በላይ አደራን የሚያስቀድም የተገለጠ መሰጠት ነው።

የታማኝነት ትክክለኛ ፍቺ እግዚአብሔርና እግዚአብሔር ነው።"የታማኝነት ውሃ ልክ እግዚአብሔር ነው።ታማኝነት ልክ አለው እርሱም እግዚአብሔር ይባላል"!!!
934 views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 05:52:47 በእግዚአብሔር ሰዎች ብቻ የማትሆኑት ነገር አለ።በእግዚአብሔር ብቻ የምትሆኑት ነገር አለ።

ብዙ ክርስቲያኖች ህብረታቻው ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር አይደለም።የክርስትና ህብረት የሚጀመረው ከእግዚአብሔር እንጂ ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር አይደለም።ወደ እግዚአብሔር ህብረት እደጉ እንጂ ወደ እግዚአብሔር ሰዎች ህብረት አትደጉ።

በእግዚአብሔር ሰው ፀሎት ወደ መለኮት ህብረት አታድጉም።ወደ መለኮት ህብረት የሚያሳድጋችሁ የግል የፀሎት ህይወታችሁ ነው።ምክኒያቱም ክርስትና መፀለይ እንጂ ማፀለይ አይደለም።ከእግዚአብሔር ሰው ፀሎት ተማር ፀሎትህን ግን ራስህ አሰማ።
797 views02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 06:05:56 የመንግሥቱ ስልጣን

በእግዚአብሔር መንግስት ስልጣን የብቃት ጉዳይ ሳይሆን የሹመት ጉዳይ ነው።በእግዚአብሔር መንግስት ሰውን የበላይ ገዢ አድርጎ የሚያመጣባችሁ ብቃት ሳይሆን ሹመት ነው።ሹመት የስልጠና ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ምርጫ ውጤት ነው።

ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግስት ፊተኞች ሆነው ሰዎች ከመጡባችሁ ስለሚችሉ ሳይሆን ስለተመረጡ ነው።እግዚአብሔር በማይችሉ የሚችል መሆኑንም አትርሳ።

ሮሜ 9
¹⁰ ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥
¹¹ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥
¹² ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።
691 views03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 09:49:38 ቃል የሌለው አንደበትና ቀልሀ የሌለው መሳሪያ አንድ ናቸው።

አንደበታችሁ የእግዚአብሔር ቃል ካለበት መሳሪያ ይሆናል።የእግዚአብሔር ቃል ከሌለው መመገቢያ ብቻ ይሆናል።

ኤርሚያስ እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ አፌን ዳስስኝ ብሎ ከተናገረ በኃላ እነሆ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ እንዳለው ይናገራል።በህይወት ያሉ የጨለማ ፍላፃዎችን መንቀልና መስበር የሚቻለው በአንደበት ነው።

ነገር ግን ይህን የሚያድረገው የእናንተ አንደበት ሳይሆን በአንድበታችሁ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው።አንደበታችሁ የእግዚአብሔር ቃል ከሌለው ከጩህት ያለፈ የምታፈርሱት ጨለማ አይኖርም።አንደበት ያለ እግዚአብሔር ቃል መሳሪያ ያለ ቀልሀ ማለት ነው።

ገበሬ በእጁ የዘራውን እንደሚያጭድ ሁሉ ክርስቲያንም በአፉ የዘራውን ያጭዳል።የህይወታችሁ ምርት በአፍችሁ ከምዘሩት ውጪ እንደማይሆን ማወቅ ተገቢ ነው።
827 views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 05:51:18 እግዚአብሔር ሰፍር ውስጥ የሚወለድ ህልም እንጂ ሰፍር ውስጥ የሚጨርስ ህልም አልሰጠንም።

“ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።ኢዮብ 8፥7
784 views02:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:21:44 ማደግ

የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በዕድገታችሁ ልክ ይገለጣል።<<የጌታን መልክ በመወለድ ትካፈሉታላችሁ በዕድገት ትገልጡታላችሁ።>>በጌታ ያልተወለደ ዘሩ እንደማይገኝበት ሁሉ እንዲሁ ያላደረገ ደግሞ መልኩ አይገለጥበትም።

ስለዚህ መወለዳችሁ ለእግዚአብሔር ደስታ እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም።እግዚአብሔር ከእናንተ ህይውት ክብር የሚያገኝው ስትወለዱ ሳይሆን ስታድጉ ነው።

<<የክርስትና ውሃ ልክ ወይም መለኪያው ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን የልጁ መልክ ነው።በእግዚአብሔር ፊት የምትለካው ባለህ ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን ምን ያህል የልጁን መልክ ገልጠሃል በሚለው ነው።>>

ቅባት የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጣል ዕደገት የልጁን መልክ ይገልጻል።ቅባት በእግዚአብሔር የመቀባት ውጤት ነው መልክ ግን ክርስቶስን የመኖር ውጤት ነው።
980 views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ