Get Mystery Box with random crypto!

የመንግሥቱ ስልጣን በእግዚአብሔር መንግስት ስልጣን የብቃት ጉዳይ ሳይሆን የሹመት ጉዳይ ነው።በ | Kingdom of God🏥🏥🏥

የመንግሥቱ ስልጣን

በእግዚአብሔር መንግስት ስልጣን የብቃት ጉዳይ ሳይሆን የሹመት ጉዳይ ነው።በእግዚአብሔር መንግስት ሰውን የበላይ ገዢ አድርጎ የሚያመጣባችሁ ብቃት ሳይሆን ሹመት ነው።ሹመት የስልጠና ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ምርጫ ውጤት ነው።

ስለዚህ በእግዚአብሔር መንግስት ፊተኞች ሆነው ሰዎች ከመጡባችሁ ስለሚችሉ ሳይሆን ስለተመረጡ ነው።እግዚአብሔር በማይችሉ የሚችል መሆኑንም አትርሳ።

ሮሜ 9
¹⁰ ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንዱ ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥
¹¹ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥
¹² ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።