Get Mystery Box with random crypto!

ቃል የሌለው አንደበትና ቀልሀ የሌለው መሳሪያ አንድ ናቸው። አንደበታችሁ የእግዚአብሔር ቃል ካ | Kingdom of God🏥🏥🏥

ቃል የሌለው አንደበትና ቀልሀ የሌለው መሳሪያ አንድ ናቸው።

አንደበታችሁ የእግዚአብሔር ቃል ካለበት መሳሪያ ይሆናል።የእግዚአብሔር ቃል ከሌለው መመገቢያ ብቻ ይሆናል።

ኤርሚያስ እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ አፌን ዳስስኝ ብሎ ከተናገረ በኃላ እነሆ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ እንዳለው ይናገራል።በህይወት ያሉ የጨለማ ፍላፃዎችን መንቀልና መስበር የሚቻለው በአንደበት ነው።

ነገር ግን ይህን የሚያድረገው የእናንተ አንደበት ሳይሆን በአንድበታችሁ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው።አንደበታችሁ የእግዚአብሔር ቃል ከሌለው ከጩህት ያለፈ የምታፈርሱት ጨለማ አይኖርም።አንደበት ያለ እግዚአብሔር ቃል መሳሪያ ያለ ቀልሀ ማለት ነው።

ገበሬ በእጁ የዘራውን እንደሚያጭድ ሁሉ ክርስቲያንም በአፉ የዘራውን ያጭዳል።የህይወታችሁ ምርት በአፍችሁ ከምዘሩት ውጪ እንደማይሆን ማወቅ ተገቢ ነው።