Get Mystery Box with random crypto!

ማደግ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በዕድገታችሁ ልክ ይገለጣል።በጌታ ያልተወለደ ዘሩ እንደማ | Kingdom of God🏥🏥🏥

ማደግ

የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በዕድገታችሁ ልክ ይገለጣል።<<የጌታን መልክ በመወለድ ትካፈሉታላችሁ በዕድገት ትገልጡታላችሁ።>>በጌታ ያልተወለደ ዘሩ እንደማይገኝበት ሁሉ እንዲሁ ያላደረገ ደግሞ መልኩ አይገለጥበትም።

ስለዚህ መወለዳችሁ ለእግዚአብሔር ደስታ እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም።እግዚአብሔር ከእናንተ ህይውት ክብር የሚያገኝው ስትወለዱ ሳይሆን ስታድጉ ነው።

<<የክርስትና ውሃ ልክ ወይም መለኪያው ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን የልጁ መልክ ነው።በእግዚአብሔር ፊት የምትለካው ባለህ ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን ምን ያህል የልጁን መልክ ገልጠሃል በሚለው ነው።>>

ቅባት የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጣል ዕደገት የልጁን መልክ ይገልጻል።ቅባት በእግዚአብሔር የመቀባት ውጤት ነው መልክ ግን ክርስቶስን የመኖር ውጤት ነው።