Get Mystery Box with random crypto!

ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ።መከራህን ለእግዚአብሔር ደስታህን ለዓለም | Kingdom of God🏥🏥🏥

ሲነጋ ወደ ዓለም ሲመሽ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር አትገስግስ።መከራህን ለእግዚአብሔር ደስታህን ለዓለም አታድርግ።ሆኖም ዓለም በኃጢአት ስታደክምህ ወደ እግዚአብሔር ሽሽ እንጂ ከእግዚአብሔር አትሽሽ።ህፃን ልጅ ሲቆሽሽም የሚሸሸው ወደ እናቱ ነውና አንተም በሃጢአት ስትቆሽሽ ወደ መሀሪው ጌታህ ሽሽ እርሱም ይምርሃል።

“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።ኢሳይያስ 1፥18