Get Mystery Box with random crypto!

የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmejerrymejerry — የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋
የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmejerrymejerry — የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋
የሰርጥ አድራሻ: @itsmejerrymejerry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 687
የሰርጥ መግለጫ

በዚ ቻናል ደብዳቤዎች -
ወግ
ትረካዎች
ግጥሞች -በድምፅ፣ በፅሁፍ
አነቃቂ ንግግሮች
አስተማሪ ታሪኮች እና ሀሳቦች ይቀርቡበታል።

"መኖር ጥሩ ነው....

ሀሳብና አስተያየት እቀበላለው
(ኪያብ) @Jerrysisayyy
@itsmejerrymejerry

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-20 21:31:02
: I know im just a random stranger, but im happy you're here. Grateful that you're still sticking around…

@filimon6
289 viewsjerusalem , 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 08:57:42
አበደ አሉኝ እኳ አለሜ ........ እንደው ባብድስ ይገርማል ወይ አብሬሽ የኖርኩባቸው አመታቶች በቂ ነበረስ ወይ? አለሜ ሁሉም ነገር ዝም ጭጭ አለብኝ እነዛ ውብ የነበሩ ስፍራዎች ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ ተቀየሩ እነዛ ውብ መናፈሻዎች አበባቸው ደረቁ ይሀው አንቺ ከሄድሽ በኃላ የቀረኝ ነገር ቢኖር አበደ የሚለው ቃል ሆነ .........

አለሜ የምር እንዳሉት አበድኩ እንዴ ተነሺ ንገሪኝ አለሜ አው አብደሀል በይኝ አንቺ ነው የማምነው ሌላማ የትኛውን ሰው አምናለው አንቺ አለመኖርሽን እያወቁ አብደሀል ያሉኝን አላምንም........ አለሜ ትዝ ይልሻል ያ ሁሌ ከዛ ሰፈር ስላንፍ " እንደደመቃቹ ኑሩ እያሉ የሚመርቁን አባት " ዛሬ እንዲህ ሆኜ ቢያዩኝ " አረ ተው ልጄ በቃ እርሳት አሉኝ " እሺ ማነው ውሸታም ያልሆነው በኔ እና ባንቺ አለም? ንገሪኝ መልሺልኝ .......... እውነት ነበረሽ ለካ እንዲህ አትውደደኝ ስትይኝ የነበረው ።

አዎ አለሜ እንደዛ ወድጄሽ ይሀው አበድኩልሽ ........ አዎ አለሜ እንደዛ አፍቅሬሽ ይሀው....... እብድ ተባልኩልሽ አዎን አብጃለው ነይና ተመልከቺኝ አዎ አቅቷኛል ያላንቺ ማን አለኝ አዎ ጎዳናውም የለም ፣አዎ መናፈሻውም የለም አዎ አንቺም የለሽም አዎ እኔም አብጃለው ።

#ኢንት

ሰናይ ምሽት
231 viewsEnat, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 22:07:02 ..............

አንዴ ተመልክቷት አቅሉ ቢዞርበት
ምንም አላቅማማ ለፍቅሯ ለመሞት
ለምኖ ለምኖ ከእግሯ ስር ተደፍቶ
ጠዋትና ማታ ቤተክርስቲያን ስሞ
ደጅ ጠንቶ ቢያገኛት ቤቱ ብትገባለት
ወራትን አርግዛ ለቀናት አምጣ ልጆች ብትወልድለት
በኑሮ ወላፈን ቢረግፍ ያ... የሚያምር ውበት
ያዘነበው እ ን ባ የተሳለው ስለት
የመሀላ ጋጋታ ሁሉም ተዘንግቶት
ሚስቱን ችላ ብሎ አንዲት ወጣት ጉምል ልቡ ከጀለበት
ማመኗ ሳይገደው ባቆሸሸው ገላ እያቀፋት ሲኖር
ለውበቷ ሌባ ካለው እግዜር ይቅር
ብያለሁ ነፍስይማር!
ነፍስ ይማር

#ዮቶራዊት ..
@Mahder_Kasahun
199 viewsmadi@, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 19:16:53
251 viewsjerusalem , 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 19:00:28 ምቶዳቸውን ላለማጣት ብዙ ትሆናለህ ሁሌም ትደክማለህ ከስራቸው አትጠፋም ዝምታቸው ባወራኸው ባደረከው ነገር የተከፉብህ እየመሰለህ ትጨነቃለህ እነሱ ግን ቅንጣት ታህል አይረዱህም ሁሌም ልታገኛቸው አብረሃቸው ልታሳልፈው የፈለከውን ግዜ መሄጃ እንደሌለህ ፈላጊ እንደሌለህ አስበው ሊጎዱህ ይፈልጋሉ



የተሰጣቸው ቦታ አልገባቸውምና ተረዳቸው ንግግርህን ነ እሺታ ገልፀህ እለፈው ምናልባት ስተዋቸው ይገባቸው ይሆናል

# እናት
192 viewsEnat, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 14:55:01 .....

አምንሃለው የማምንህ ስላመንከኝ አደለም ልቤ ውስጥ ስላለህ እንጂ የምወድህ ስለምቶደኝ አደለም ከሌሎች ልዪ ስለሆንክ እንጂ.. አንተን ለመውደድና ለማፍቀር ምላሽ አልጠብቅም ደግሞም እንደምቶደኝ አውቃለው...
ታውቃለህ አይኖቼ አንተን ሲያዩ ቀጥሎ ምን እንደምልህ ረሳለው.. ስንገናኝ ልስምህ ፈልጌ ስጠጋህ ልቤ ቀጥ ትልና ድንጋጤዬን ታሳብቅብኛለች

ጠረንህ ለኔ ሽቶዬ ነው መቼም አረሳውም የእጆችህ ልስላሴ ለመንካት ያሳሳሉ ኧረ ምኑ ሁሉ ነገርህ ያደነዝዘኛል ለደቂቃም ሳጣው #ይናፍቀኛል
ሌላ ምን እልሃለሁ በቃ አሁንም የማላቀውን ነገን ጨምሬ እወድሃለሁ።

the ማካበድ ግን የምሬን ነው

#እናት
223 viewsEnat, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 21:58:23 .
.
ደስታ ማለት የምትወደውን ሁሉ ማግኘት አይደለም! አንዳንዴ ያገኘኸውን በቂ ነገር መውደድ'ም ይሆናል!..

#ዮቶራዊት ..
@Mahder_Kasahun
224 viewsmadi@, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 14:58:25 ምሽት ብቻዬን እራመዳለሁ ከጎኔ አንተ የለህም ኮከቦቹ ያሾፉብኛል ጨረቃም አንቺ የማትረቢ ነሽ ትለኛለች ቆይ ለምን?

ሁሌ የለህም ብዬ ሳስብ ባንተ ተስፋ ስቆርጥ ትመለሳለህ ድንገት ሳላስበው አለሁ ብለህ የትም እንደማትሄድ እየነገርክ አዲስ ያላረጀ ጉልበት ያለው ተስፋ ትሰጠኛለህ ግን መተሃል ብዬ ደስታዬን ሳልጨርስ ለራሴ የደገስኩት ድግስ ሳያልቅ ከአይኔም ከጆሮዬም ትሰወራለህ ፈልጌ እስካጣህ ድረስ ትሰወራለህ በቃኝ ከዚ ቡሃላ ብዬ ራሴን እያታለልኩ ፍለጋ እወጣለሁ የማገኝህ ይመስል የሌለህበት ቦታ ሄጄ እጠብቅሃለሁ ሲመሽ እመለሳለሁ በጨለማና መብራቶቿ ስድብ የሚመስል አስተያየት እየታየው ወደ ቤት እገባለሁ ግን አሁን የሰጠኸኝን ተስፋ ጨረስኩት መተህ ብትሰጠኝም መቀበያ ቦታ የለም ተሰባብሮ አለቀ ከሚችለው በላይ ተሸክሞ ተሰባበረ የበቃው ይመስለኛል ባዶ ስሜት እየተሰማኝ ነው ጨረቃን ለማየት ምወጣው እንድታጫውተኝ እንድደሰትባት ነው ከዚ ቡሃላ ብትመጣ ሚፈጠረው አይታወቅም





#እናት
304 viewsEnat, 11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 22:00:58 .
.
በልቤ ቦታ እንዳለህ...
አውጥቼ አላ'ሳይህ ነገር..............

#ዮቶራዊት ..
@Mahder_Kasahun
263 viewsmadi@, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 20:42:20 ..........
"... ምድር ለኛ የመጨረሻ መድረሻችን ሳትሆን ወደ ዘላለም የምንሻገርበት ድልድይ ናት... የሠማይ መንገደኞች ነን... ወደዚች ምድር የመጣነው እኛ ፈልገን ሳይሆን ምድር ስለፈለገችን ነው... እንዴት እንደምንኖር ግን እኛና አካባቢያችን እንወስናለን...
ትልቁ መኖርም እኛ እንደፈለግን ሳይሆን በምድር እንደተፈለግን መኖር ነው.. ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም.. ሁሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል...
የተፈጠርንለት ዐላማ ለሌሎች ሰዎች ጥቅምም ነው... የህይወት ዐላማችን የሚፈጸመው በሌሎች ውስጥ ነው... ነገር ግን ለሌሎች መኖር የምንጀምረው ለራሳችን በተገቢው መኖር ስንጀምር ነው....."
#ዮቶራዊት
@Mahder_Kasahun
269 viewsmadi@, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ