Get Mystery Box with random crypto!

አበደ አሉኝ እኳ አለሜ ........ እንደው ባብድስ ይገርማል ወይ አብሬሽ የኖርኩባቸው አመታቶች | የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

አበደ አሉኝ እኳ አለሜ ........ እንደው ባብድስ ይገርማል ወይ አብሬሽ የኖርኩባቸው አመታቶች በቂ ነበረስ ወይ? አለሜ ሁሉም ነገር ዝም ጭጭ አለብኝ እነዛ ውብ የነበሩ ስፍራዎች ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ ተቀየሩ እነዛ ውብ መናፈሻዎች አበባቸው ደረቁ ይሀው አንቺ ከሄድሽ በኃላ የቀረኝ ነገር ቢኖር አበደ የሚለው ቃል ሆነ .........

አለሜ የምር እንዳሉት አበድኩ እንዴ ተነሺ ንገሪኝ አለሜ አው አብደሀል በይኝ አንቺ ነው የማምነው ሌላማ የትኛውን ሰው አምናለው አንቺ አለመኖርሽን እያወቁ አብደሀል ያሉኝን አላምንም........ አለሜ ትዝ ይልሻል ያ ሁሌ ከዛ ሰፈር ስላንፍ " እንደደመቃቹ ኑሩ እያሉ የሚመርቁን አባት " ዛሬ እንዲህ ሆኜ ቢያዩኝ " አረ ተው ልጄ በቃ እርሳት አሉኝ " እሺ ማነው ውሸታም ያልሆነው በኔ እና ባንቺ አለም? ንገሪኝ መልሺልኝ .......... እውነት ነበረሽ ለካ እንዲህ አትውደደኝ ስትይኝ የነበረው ።

አዎ አለሜ እንደዛ ወድጄሽ ይሀው አበድኩልሽ ........ አዎ አለሜ እንደዛ አፍቅሬሽ ይሀው....... እብድ ተባልኩልሽ አዎን አብጃለው ነይና ተመልከቺኝ አዎ አቅቷኛል ያላንቺ ማን አለኝ አዎ ጎዳናውም የለም ፣አዎ መናፈሻውም የለም አዎ አንቺም የለሽም አዎ እኔም አብጃለው ።

#ኢንት

ሰናይ ምሽት