Get Mystery Box with random crypto!

.............. አንዴ ተመልክቷት አቅሉ ቢዞርበት ምንም አላቅማማ ለፍቅሯ ለመሞት ለ | የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

..............

አንዴ ተመልክቷት አቅሉ ቢዞርበት
ምንም አላቅማማ ለፍቅሯ ለመሞት
ለምኖ ለምኖ ከእግሯ ስር ተደፍቶ
ጠዋትና ማታ ቤተክርስቲያን ስሞ
ደጅ ጠንቶ ቢያገኛት ቤቱ ብትገባለት
ወራትን አርግዛ ለቀናት አምጣ ልጆች ብትወልድለት
በኑሮ ወላፈን ቢረግፍ ያ... የሚያምር ውበት
ያዘነበው እ ን ባ የተሳለው ስለት
የመሀላ ጋጋታ ሁሉም ተዘንግቶት
ሚስቱን ችላ ብሎ አንዲት ወጣት ጉምል ልቡ ከጀለበት
ማመኗ ሳይገደው ባቆሸሸው ገላ እያቀፋት ሲኖር
ለውበቷ ሌባ ካለው እግዜር ይቅር
ብያለሁ ነፍስይማር!
ነፍስ ይማር

#ዮቶራዊት ..
@Mahder_Kasahun