Get Mystery Box with random crypto!

ምሽት ብቻዬን እራመዳለሁ ከጎኔ አንተ የለህም ኮከቦቹ ያሾፉብኛል ጨረቃም አንቺ የማትረቢ ነሽ | የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

ምሽት ብቻዬን እራመዳለሁ ከጎኔ አንተ የለህም ኮከቦቹ ያሾፉብኛል ጨረቃም አንቺ የማትረቢ ነሽ ትለኛለች ቆይ ለምን?

ሁሌ የለህም ብዬ ሳስብ ባንተ ተስፋ ስቆርጥ ትመለሳለህ ድንገት ሳላስበው አለሁ ብለህ የትም እንደማትሄድ እየነገርክ አዲስ ያላረጀ ጉልበት ያለው ተስፋ ትሰጠኛለህ ግን መተሃል ብዬ ደስታዬን ሳልጨርስ ለራሴ የደገስኩት ድግስ ሳያልቅ ከአይኔም ከጆሮዬም ትሰወራለህ ፈልጌ እስካጣህ ድረስ ትሰወራለህ በቃኝ ከዚ ቡሃላ ብዬ ራሴን እያታለልኩ ፍለጋ እወጣለሁ የማገኝህ ይመስል የሌለህበት ቦታ ሄጄ እጠብቅሃለሁ ሲመሽ እመለሳለሁ በጨለማና መብራቶቿ ስድብ የሚመስል አስተያየት እየታየው ወደ ቤት እገባለሁ ግን አሁን የሰጠኸኝን ተስፋ ጨረስኩት መተህ ብትሰጠኝም መቀበያ ቦታ የለም ተሰባብሮ አለቀ ከሚችለው በላይ ተሸክሞ ተሰባበረ የበቃው ይመስለኛል ባዶ ስሜት እየተሰማኝ ነው ጨረቃን ለማየት ምወጣው እንድታጫውተኝ እንድደሰትባት ነው ከዚ ቡሃላ ብትመጣ ሚፈጠረው አይታወቅም





#እናት