Get Mystery Box with random crypto!

.......... '... ምድር ለኛ የመጨረሻ መድረሻችን ሳትሆን ወደ ዘላለም የምንሻገ | የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

..........
"... ምድር ለኛ የመጨረሻ መድረሻችን ሳትሆን ወደ ዘላለም የምንሻገርበት ድልድይ ናት... የሠማይ መንገደኞች ነን... ወደዚች ምድር የመጣነው እኛ ፈልገን ሳይሆን ምድር ስለፈለገችን ነው... እንዴት እንደምንኖር ግን እኛና አካባቢያችን እንወስናለን...
ትልቁ መኖርም እኛ እንደፈለግን ሳይሆን በምድር እንደተፈለግን መኖር ነው.. ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም.. ሁሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል...
የተፈጠርንለት ዐላማ ለሌሎች ሰዎች ጥቅምም ነው... የህይወት ዐላማችን የሚፈጸመው በሌሎች ውስጥ ነው... ነገር ግን ለሌሎች መኖር የምንጀምረው ለራሳችን በተገቢው መኖር ስንጀምር ነው....."
#ዮቶራዊት
@Mahder_Kasahun