Get Mystery Box with random crypto!

ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪

የቴሌግራም ቻናል አርማ httpyechalal — ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪
የቴሌግራም ቻናል አርማ httpyechalal — ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪
የሰርጥ አድራሻ: @httpyechalal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው
የራሣችንን ኢትዮዽያዊ ቀለም ይዘን፡፡
ባህልና ማንነታችንን በሃገር ተረካቢ
እፃናት እና ወጣቶች ላይ ለማስቀረት
ብሎም በጥበብ የተናፀነ ጥበበኛ ሠው
ለመፍጠር ፤ የአባቶቻችን እውቀትን
ጀግንነትንና ሃገር ወዳድነትን እያስተማርን
ጀግኖች አባቶች አሣምረው ያስቀመጡልንን
ሃገር ከዘረኝነትና ከፖለቲካ በፅዳ መንፈስ
እንዴት ማቆየት እንዳለብን እያስተማርን እንጓዛለን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-01 21:51:08
መኖር ምንድን ነው?
መሞትስ ምንድን ነው?
ህልም ምንድን ነው ?
ተስፋችንስ የት ነው?
እንግዲ የመጀመሪያው የህይወት ጥያቄዎች ከዚህ ይጀምራሉ፡፡ ለምን እንደምንኖር ለምን እንደምንሞት እና ለምን እንደምናልም ማወቅ መቻል በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በአጋጣሚ የምናገኘውም የምናጣውም ምንም የለም፡፡ ለነገሩ አጋጣሚስ ምንድን ነው፡፡ ሌላ ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄን በጥያቄ የምንሸፍነው የነገው ተስፋችንን እያለምነው ነው እየተመኘናቸው ነገሮች ሠፊ ልዩነት አላችው ግን ጥያቄው አሁንም ሌላ ጥያቄ ነው፡፡ወዳጄ ለጥያቄ መልስ ከመፈለግ አንተም ጠያቂ መሆን ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ለምን እንደምትኖር ካላወከው መወለድክን ፍራው!!!

ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!

@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
183 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 20:55:58
ዛሬ ነገ አይደለም!!!
ዛሬ ነገ አይደለም!!! ነገን በዛሬው ጥቁር ጥላ አትመዝነው!! የወደከው ዛሬን እንጂ ነገን አይደለም!!! ዛሬ ለነገ ብርታት ይሁንክ ለውጥክን ሰው አየው አላየው አትጨነቅ ለውጥክ ለራስክ መጀመሪያ ይታይክ!!! ለልብክ ሁሌም አንድ ነገርን ንገረው "ነገ ከዛሬ የተሻለ ነው" ዛሬ ከፍቶክ ይሆናል!!! ዛሬ ደክሞክ ይሆናል!!! ዛሬ ተሸንፈክ ይሆናል!!! ነገር ግን ነገ ታሪክ ይቀየራል ነገ ትደሰታለክ!!! ነገ ትበረታለክ!!! ነገ ታሸንፋለክ!!! ምክንያቱም አንተ ከሞት በፊት ካለው ጨለማ እና ከሞት በዋላ ካለው ጨለማ መሃል ያለከው ብርሃን ነክ!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!
@Httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
198 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 21:48:51
የአህምሮ ትግል

ዛሬ ለነገ ትግል ናት!!! ዛሬን ለማሸነፍ ሩጫው እና ትግሉ የግድ ነው!!! ሁሉንምን ማሸነፍ ደግሞ ቀላል ነው!!! ዋናው አሻግሮ ማየት መቻል ብቻ ነው፡፡ እራስክን ከንስር በላይ አጠንክረክ እይታክን አጥረተክ ሃይልክን ጨምረክ ወደነገ ገስግስ!!! የጠነከረ ነገ ካለክ የማታሸንፍበት ነገር የለክም!!! ወዳጄ አንተ ውድድርክ ከሰው ጋር ካደረከው የመጀመሪያው ሽንፈት ይጀምራል!!! ማንም ያንተን ኑሮ አይኖርልክም!!! ትግልክን ከራስክ ጋር አድርገው ያኔ አንተ አሸንፈካል!!! አሁን የተኛውን አህምርክን ቀስቅሰውና ሩጫክን አስጀምረው!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!
@Httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
232 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:46:48
ብዙ ርቀትን አሻግረን አይተናል!!! ዛሬ ላይ ቆመን ነገን ኑረነዋል!!! ከባድ ሆኖ የሚታየውን ነገር ቀላል እንደሆነ በተግባር አይተናል!!! መውደቅና መሠበር አጠነከረን እንጂ አልገደለንም!!! ሁላችንም ራሳችንን ካዳመጥነው ነገ ላይ መድረስ ቀላልነቱን እንረዳለን ውድድር ከራስ ጋር ነው ራስን ካሸነፍክ አንተ የተለየክ ትሆናለክ:: ያንተ ብርሃን ፅልመት አይኑን ለጋረደበት በሙሉ ያበራል!!!
ስለዚህ የዛሬን ጨለማ በነገው ብርሃን አድምቀው ምክንያቱም ትችላለክ!!!
ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
234 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 20:35:52
ይንጋልሽ ሃገሬ
ብርሀን ከመውጣቷ በፊት በዙሪያዋ ያለውን ድቅድቅ ጨለማ ተጋፋታ ታግላ ጎህ ትቀዳለች። በብሩህ ሰማይ ላይ ማለዳ የወጣችው ፀሀይ ሲያሻት ትግላለች ሲያሻትም ቀዝቀዝ እያለች ብርሀኗን ለአለም ታስተጋባለች። ግን ያቺ ታግላ የወጣችው ፀሀይ ሲመሻሽ ዳግም ጨለማ ብርሀኖን ይነጥቃታል።
ሃገሬ እንደ ፀሀይ እና እንደ ጨለማ አይደለችም። የሃገሬ ብርሀን ጠዋት ላይ እንዳለችው ፀሀይ በትግል ወቶ አይቅርም ማታም በጨለማ ዳግም ጭልመት አይሆንም።
ሃገሬ ብርሃኗ ፈንጥቆ ከጨለማው መውጣቱን ነው የሚጠባበቀው። የሃገሬ ብርሀን ፈንጥቆ ከወጣ ሊጨልምም ሊደበዝዝም አይችልም። ሃገሬ የትልቅ ብርሀን ባለቤቶች ነች!!! የጨለመው በብርሃን ይሞላል!!!

@Httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
296 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 19:09:07
የተቀረውን ብርድ እና ትካዜ የሚበዛበትን ጊዜ ድል አርጎ ስለማለፋ

እኛ ብርቱዋች ነን። ምክንያቱም አሁን ካለንበት ይልቅ ያሳለፍነው ከባድ እና መሰናክል የበዛበት ነበር። ትናትን አልፈን ዛሬ ላይ ስለደረስን ዛሬን ለነገ ማሻገር ትንሹ ስራችን ነው።

ብርዱ ቢበዛ የክረምቱ ወጨፎ ተከማመንበት ሰውነታችን በላይ ቢሆን ጨልመትና ጨለማ ቢከበን የክረምቱ ሰቀቀን ተስፋችንን አሟጦ ተስፋ የሌለን ቢይስመስለን።

አሁንም ትናትን ስላለፋን ዛሬ ወደ ነገ አይከብደንም።

ምክንያቱም ነገ ይሄ ጭጋግ አልፎ የአዲስ ነገሮች መጀመሪያ የብሩህ ብርሀን ባለቤት መሰክረም አዲስ አመትን ይዛ ትመጣለች።

ይሄ ሁሉም የሚተማመንበት ትልቅ ተስፋ ነው።
ተስፋ!!!

ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!

@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
254 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 21:28:57
ብርሃናማ ነገ በትናንት ጨለማ አልፎ የሚገኝ ፍካት ነው፡፡ በጉም የደበዘዘ ሰማይ ስለ ህልም እና ስለ ህልመኞቹ አጥርቶ ያሳያል። ፅልመትና ብርሀን ያጣው ምድር በተስፋ እና በተስፈኞች ብርሀን አዲስ ፀሀይ ይጎናፀፋል።
ብዙ ነገሮች ነጋችን ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
ነገን ማለም ስራችንም ሂወታችንም ነው።
ካለፈው ትናንት የማያንስ ትልቅ ነገ አለን።
እውነት ነው ስለነገ ያለመ ነገን ይኖራል። ይሄ የእኛ የእውነተኛ መንገድ ነፀብራቅ ወጤት ነው።
ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!

@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
277 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:35:45
ከተራራው ማዶ ያለችው ድንቅ ፀሀይ ጨለማ ውስጥ ለኖረ ማንነት ከልብ በእውነተኛ ስሜት ትናፍቃለች። የሚናፍቃትንም ማንነት እሷን ለማግኘት ብዙ የጨለማ ጊዚያትን ብዙ ጭልመቶችን ያሳልፋል። ጨለማን አልፎ ትልቁ ህልሙ ፀሀይ ላይ ሲደርስ ግን በጨለማ ስለኖረ ለማየት ይከብደዋል። ምክንያቱም በጨለማ ለኖረ ብርሀን ከባድ ነው። ብርሀን ለማየት ሀይል ይኑረን።

ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!

@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
282 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 22:35:44
በማይነቃነቅ ምሰሶ ቤት ውስጥ የተሰበሰብ የእውነት መንገድ ተጓዦች። ህልማቸው ሊፈርስም ሊጠፋም አይችልም ምክንያቱም በህልመኛው መሀል ብዙ አላሚዎች አሉ በብዙ አላሚዎች መካከልም ትልቅ ህልመኛ አለ። ስለዚህ ቤቱ ህልሙም የእውነት መንገድ ጉዞውም ይቀጥላል........

ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!

@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
332 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 21:00:16
አመታቶች ያልፋሉ ጊዜም በጊዜ አመታትም በአመታት ሲሻር እዚህ ደርሰናል።
ምስክርነቱ ለኖረው ሳይሆን እንዲኖር ላደረገው ነው። እውነት ነው የዋላው ከሌለ የፊቱ ሊኖር አይችልም። የዋላውን አሳምረው በማይነቃነቅ ተስፋ ከምንም ነገር በጠነከር ህልም ገንብተው ያቆዩ ታሪክ አስተላላፊዎች ምን ጊዜም ጠንክሮ አጠንካሪዎች ናቸው። እውነት ጊዜ ሲሸኝ ጊዜን ወልዶ ዛሬ ላይ ብንደርስም የትናንት ታሪካችን ግን በእውነት መንገድ ተጓዦች አምሯል። የእውነት መንገደኞች ደግሞ ትናንት እንደ ታሪክ ዛሬ በትዝታ አይነሱም በልብ ውስጥ ነግሰው ይኖራሉ እንጂ።

ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!

@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
362 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ