Get Mystery Box with random crypto!

ስለ -ህይወት 👉🎤🎧📒📗📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ historysharee — ስለ -ህይወት 👉🎤🎧📒📗📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ historysharee — ስለ -ህይወት 👉🎤🎧📒📗📖
የሰርጥ አድራሻ: @historysharee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 516
የሰርጥ መግለጫ

"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፤ለዓላማ መቆም፤ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፤ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርዓያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው??????"
Join👉🌹 @historysharee
➳➳➳ @Betsitaye ➢➢➢
◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-11-24 15:42:41 አትፍረድ

እንዲ ነው አትበል ውስጡን ሳትረዳ
ጠልቀህ ሳትመረምር የስሜቱን ጓዳ
ብዙ ብዙ ነገር በህይወቱ ሲከሰት
ከተፈጥሮው ውጪ የሰው ልጅ በሂደት
ሌላ ሰው ይሆናል ተቃራኒ ይለምዳል
ከትላንቱ የራቀም ጎዳና ይራመዳል
.
.
ይለፍ ይቅር ብሎ ህመሙን ደብቆ
ቁስሉ ባይደርቅም ከሳቀው ጋር ስቆ
ያዘነም ሲያገኝ ሀዘኑን ተካፍሎ
እንደየአመጣጡ እንደ አየሩ ውሎ
ከቤቱ የገባም ለት ስሙ ከደጅ አድሯል
የልብ ሳይታይ ውይ እስሱ ተብሏል
.
.
ማይወራ ጉዳት ትንተና ያጣ ስሜት
ከእያንዳንዱ ሰው ጋር አለና በየቤት
በደፈናው ብቻ አንፍረድ ይቅርብን ከመንገድ እንውጣ
ነገ እኮ ሚስጥር ነው ማን ምኑን ያውቅና የመጪውን እጣ


@historysharee
1.6K viewsedited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 16:15:25 ተቀይረው ወይስ ተቀይሬ?

ገጣሚ ኢብራሂም ለጃ
አንባቢ @ebro43


@historysharee
1.5K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-13 16:32:02 መኖር ግን ምንድነው ? እንጃ መኖርማ መኖር ነው ይላሉ አንዳንዶች ሌሎች ደግሞ መኖር መታወስ ነው ፣ በሰዎች ልብ ውስጥ መገኘት ፣ ሳይገኙ መገኘት አልፎ አለመረሳት ፣ ሰው መሆን... መኖር መለወጥ ነው ፣ መኖር የራስን ስሜት መግደል ነው ይሉናል ግን እውነት ማነው የሌሌችን ህመም የሚታመመው ማነውስ እራሱን ገሎ ሌሎችን የሚያኖር ? ኧረ እኔጃ አለመኖርስ ምን ይሆን ? በቃ አለመኖርማ አለመኖር ነው አለመታወስ ፣ አለመገኘት ወይ ደግሞ እየኖሩም መሞት ብቻ ብዙ ይሉናል ....

@historysharee
897 views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 18:35:01 የሰው ልብ

የቅርብ እሩቆቹ ወዳጆቼ ሁሉ
ልበቢስ ነህና ልብ ግዛ ሲሉ
እኔግን ቸገረኝ ልብ ከየት ልግዛ
ማን ነቅሎ ይሸጣል ልቡን እንደዋዛ...

@historysharee
1.6K viewsedited  15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 20:57:37
ጎደኝነት
ጎደኝነት ማለት በዕድሜ የማይለካ ፣በችግር ጊዜ የማይገታ በማግኘት ያልተጀመረ በማጣት የማይቀየር በፍቅር የፀና የሰብአዊነት ጥምረት ጎደኝነት ማለት የእኔነት ስሜት የሌለበት ድብቅነት የሌለበት ከልብ የማይወጣ በገንዘብ የማይመዘን የማይተካ ግልጽነት የሞላበት ጎደኝነት ስንወደው የሚወደን ብቻ አይደለም ስንደሰት ብቻ አብሮን የሚሆንም አይደለም ስናስቀይመው ከጥላቻ ስሜት አልፎ ይቅር የሚለን ነው ጎደኝነት ከዚህ በላይ................ነው።

ይህ ካልሆነ ጎደኛ መሆን ምን ጥቅም አለው የእኔነት ስሜት የሌለበት ድብቅነት የሌለበት ከልብ የማይወጣ በገንዘብ የማይመዘን የማይተካ ግልጽነት የሞላበት ጎደኝነት እናዳብር እንሁን



@historysharee
1.5K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 20:35:24 ..... ጅማሬው ተስፋ , ምኞት , ጉጉት ... ማብቂያው ደግሞ.. ስንብት ሲሆን ይገርማል .. ግን ጊዜ እንደዚ ነው.. ሁሌም አዲስ መሆን የለም ..

... በሰው መንገድ አትመላለስ.. የሰው መንገድ የሰው ነው .. ልብ ካለክ ያንተን መንገድ ስራና ተራመድ ...



... አንዳንድ መጥፎ ቀናት..ጥሩነገሮችን ይወልዳሉ ...


... ታስሮ የጠ'በቀውን ህይወት.. ሳቅ አይፈታውም .. እንባ ግን ያላላዋል.. ወደ ነፍስም ያቀርበዋል.. በቦታው እንባ መድሀኒት ነው.. ያለቦታው ሳቅም መርዝ ነው.. አንዳንዴ ማልቀስም ትክክል ነው.. ልክ እንደዚህ ...


...አዎ, ማልቀስ መፍትሄ አይሆንም .. ግን ደግም.. አለማልቀስም ነገሩን አይቀይረውም. .. በእንባ ውስጥ ያለውን የእንባ ዘለላ ማን ሊቆጥራቸው ይቻለዋል?. . ማንም, አይደል? .. አዎ ማንም አይቆጥረውም.. ልብ ውስጥ ሆነው የሚያቃጥሉ ህመሞችንም ማንም አያድናቸውም .. #እንባዎቹ ግን ቢያንስ ስቃዩን ከውስጥ ያወጡታል ...

@historysharee
1.7K views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 15:05:10
የታመሙ መድሃኒቶች - ግጥም
@historysharee
1.4K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-24 18:40:06 ተስፋ አልቆርጥም
ጊዜ ቢጨክንም
ስማኝ ተስፋ
እኔ ተስፋ አልቆርጥም።
ከዛሬዉ ዉጥኔ
ከገልቱ ኑሬዬ
አሻግሮ መመልከት
እንዲያስችለኝ ብዬ
አንተን ተስፋን ብጠይቅህ
ተስፋን ስጠኝ ብዬ
ና እና ሰጥሀለዉ
ብለህ ከቀየዬ
ተስፋ ጭረህብኝ
የተስፋ ጭላንጭል
ቀዬህን ሳትነግረኝ
ለምን ነዉ ያልከዉ እልም?


አድራሻህን እንኳን
ምነዉ ሳተዉልኝ
መገናኛ መሥመር
ስልክህን ሳትሰጠኝ
እንኳን አሱ ቀርቶ
ሀገርህን ሳትነግረኝ
ከቶ ትጠፋለህ
እንዲዉ ገትረኸኝ?
እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
ላንተ ይብላኝልኝ
በቃልህ ለሌለህ
በቃልህ ማትገኝ።
እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
እናፍቅሀለው
የተስፋ ሰበዙን
ዉስጤ አግኝቼዋለዉ
እመነኝ አንድ ቀን
በእጄ አስገባዋለዉ

......ለካ ይሄ እራሱ
አንዱ ተስፋዬ ነዉ።.....

@historysharee
1.1K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 13:15:39 #ምርጥ_ግጥም
#እንቁጣጣሽ
#ምስራቅ_ተረፈ
.
@historysharee
714 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-16 19:15:14 መወዳደር ብቻ ሳይሆን መተባበርም እንልመድ ። ውድድር ብቻ ከሆነ ጥላቻ እና ትንቅንቅ ይስፋፋል ። መተባበር ሲጨመርበት ደግሞ እኛ በሁሉም ነገር እንሰፋለን እናድጋለን !! ምክንያቱም መተባበር ብቻችንን መፈጸም የማንችለውን በጋራ ለመፈፀም ስለሚያስችለን ነው !!



ብፎክር ባባትህ ፤ ብትኮራ ባባቴ
እናትህ እናቴ ፤ ሚስትህ ናት እኅቴ
ሀገርህ ሀገሬ ፤ መክበርህም ክብሬ
መሞትህ ሞቴ ነው ፤ ውርደትህ ውርደቴ
ናና እንዋደድ ፤ አባክህ በሞቴ።



እኛ ስንዋደድ ገበታችን ሞልቶ ይተርፋል ፣ የጠላታችን ጉልበት ይርዳል ፣ እንደ ንጋት ፀሀይ ተሙቀን አንጠገብም ፣
እንደ ሮማን አበባ መዓዛችን ያውዳል ፣ እንደ ቅዱሳንም መንደር ህያውነት ይነግሳል ፣ እንደ ድር አንበሳን እናስራለን ፣
ከችግራችን እኛ እንበልጣለን ፣ ከሚያስጨካክኑን የሚያሳተባብሩን ይበልጣሉ ፣ ጸሎታችን ይሰምርልናል ፣
ውዶቼ ፍቅር ያድለን! አሜን!


“ ትልቅ ነበርን ፤ ልብ የገዛን ቀን ፤ ትልቅ እንሆናለን !”

....

. . .አንዳንዴ ባላስተዋልነው የጊዜ እንቅፋት ላይ መውደቅ ፤ በከንቱነት ስሜት ውስጥ መዘፈቅ ፤ በፅልመት መታጠር አንዱ የህይወት ነጎድጓድ መታያ ጭላንጭል ነውና ስለዚህ በእያንዳንዱ የህይወት፣ ትንታ እጅ አንስጥ።
,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,

ተስፋ

በተስፋ ይኖራል እልፍ አእላፍ ዘመን
በሀዘን ላይ ስቀን ሁሉን አሳልፈን
የመከራን ስቃይ ሁሉንም ሰቆቃ
ተስፋችን ያደርጋል ጨዋታ እቃቃ
አንዴ ስንነሳ ዳግም ስንሰበር
ተስፋችን ፈውስ ነው ይመስላል ሚሰምር !!

@historysharee
❥❥________⚘_______❥❥
2.1K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ