Get Mystery Box with random crypto!

መወዳደር ብቻ ሳይሆን መተባበርም እንልመድ ። ውድድር ብቻ | ስለ -ህይወት 👉🎤🎧📒📗📖

መወዳደር ብቻ ሳይሆን መተባበርም እንልመድ ። ውድድር ብቻ ከሆነ ጥላቻ እና ትንቅንቅ ይስፋፋል ። መተባበር ሲጨመርበት ደግሞ እኛ በሁሉም ነገር እንሰፋለን እናድጋለን !! ምክንያቱም መተባበር ብቻችንን መፈጸም የማንችለውን በጋራ ለመፈፀም ስለሚያስችለን ነው !!



ብፎክር ባባትህ ፤ ብትኮራ ባባቴ
እናትህ እናቴ ፤ ሚስትህ ናት እኅቴ
ሀገርህ ሀገሬ ፤ መክበርህም ክብሬ
መሞትህ ሞቴ ነው ፤ ውርደትህ ውርደቴ
ናና እንዋደድ ፤ አባክህ በሞቴ።



እኛ ስንዋደድ ገበታችን ሞልቶ ይተርፋል ፣ የጠላታችን ጉልበት ይርዳል ፣ እንደ ንጋት ፀሀይ ተሙቀን አንጠገብም ፣
እንደ ሮማን አበባ መዓዛችን ያውዳል ፣ እንደ ቅዱሳንም መንደር ህያውነት ይነግሳል ፣ እንደ ድር አንበሳን እናስራለን ፣
ከችግራችን እኛ እንበልጣለን ፣ ከሚያስጨካክኑን የሚያሳተባብሩን ይበልጣሉ ፣ ጸሎታችን ይሰምርልናል ፣
ውዶቼ ፍቅር ያድለን! አሜን!


“ ትልቅ ነበርን ፤ ልብ የገዛን ቀን ፤ ትልቅ እንሆናለን !”

....

. . .አንዳንዴ ባላስተዋልነው የጊዜ እንቅፋት ላይ መውደቅ ፤ በከንቱነት ስሜት ውስጥ መዘፈቅ ፤ በፅልመት መታጠር አንዱ የህይወት ነጎድጓድ መታያ ጭላንጭል ነውና ስለዚህ በእያንዳንዱ የህይወት፣ ትንታ እጅ አንስጥ።
,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,

ተስፋ

በተስፋ ይኖራል እልፍ አእላፍ ዘመን
በሀዘን ላይ ስቀን ሁሉን አሳልፈን
የመከራን ስቃይ ሁሉንም ሰቆቃ
ተስፋችን ያደርጋል ጨዋታ እቃቃ
አንዴ ስንነሳ ዳግም ስንሰበር
ተስፋችን ፈውስ ነው ይመስላል ሚሰምር !!

@historysharee
❥❥________⚘_______❥❥