Get Mystery Box with random crypto!

ሃይማኖት አንድ ናት

የቴሌግራም ቻናል አርማ haymanotanednat — ሃይማኖት አንድ ናት
የቴሌግራም ቻናል አርማ haymanotanednat — ሃይማኖት አንድ ናት
የሰርጥ አድራሻ: @haymanotanednat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.45K
የሰርጥ መግለጫ

ኤፌሶን ፬ ፡፭አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።ይቀላቀሉ በዝክ ቻናል የአባቶች ምክርና ተግሳፅ ተለያዩ በሃይማኖት ዙሪያ
ትምህርት አዘል ይለቀቃል ።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-12 08:07:11
452 views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:07:00 #ጥበብና እና #ማስተዋል ፨
"አንድ አባት ልጃቸውን እንዲህ ሲሉ
ጠየቅዋቸው" ፦

አባት፦ልጄ ሆይ ሁሌ ስትፀልይ በተደጋጋሚ ከጭንቅላት የሚመጣው ቃል ምንድነው?
ልጅ፦አባዬ እኔ ስጸልይ የሚመጣልኝ ቃል ታማኝ፣ ትልቅ(ክብር)፣ ሀብት፣ ጤና እንዲሰጠኝ ስለምፈልግ እኚህ ናቸው ትዝ እሚሉኝ።
አባት፡- አየህ ልጄ እስኪ እነዚህን ቃላት አብረን እንመልከታቸው፦

፩፦ታማኝ መሆን በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የተወደደ ነው ነገር ግን ሰው ሁሉ ሲያመሰግንህ በትቢት እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።
፪፦ክብርን
ክብርን ደግሞ መሻት ደግ ነው። ነገር ግን እስኪ አንድ ታሪክ ልንገርህ።
አንዲት እናት እቃ መደርደርያ ገዛችና የውሀ መጠጫ ጠርሙስ እና የጠላ መጠጫ ኩባያ ገዝታ ጠርሙሱን ከፍ አድርጋ ኩባያው ደግሞ ዝቅ አድርጋ ደረደረች። ከዚያም ኩባያውን ስትፈልግ ለጠላ ስትፈልግ ደግሞ ለውሀ ብቻ ለብዙ አገልግሎት ታውለው ጀመር። ይህ ኩባያም ቢወድቅ ጊዜ ስለማይሰበር አንስታ ከነበረበት ታኖረዋለች። ጠርሙሱን ግን ለበዓል፣ ለእንግዳ እና ሰው ሲበዛባት ብቻ ነው የምትጠቀመው። በሌላ ጊዜ ግን ጠርሙሱ ሁል ጊዜ ይወለወልና ይቀመጣል።

ታዲያ ከእለታት አንድቀን ሕፃን ልጇ ውሀ ለመጠጣት ከፈለገና ውሃ መጠጫው ከፍ ከማለቱ የተነሳ ሰለራቀበት መደርደርያው ላይ በወጣ ጊዜ መዳርደርያው ተንገጫግጮ እላዩ ላይ የነበርው ዕቃው በሙሉ ወደቀ።
ነገር ግን ልጄ መደርደሪያው ላይ ከነበሩ ዕቃዎች ውስጥ የቱ የሚሰበር ይመስልሃል?
ልጅ ፦እንዴ አባዬ ጠርሙሶቹ ናቸዋ!
አባት፦ ትክክል ብለሀል ልጄ አየህ ተገስፀው፡ተሰድበው፡ተኮርክመው የማያውቁ ሰዎች ልክ እንደ ጠርሙሶቹ በትንሹ ይወድቃሉ ዋጋቸውም ከአግልግሎታቸው ጋር ሲታይ እጅግ ብዙ ነው ማለትም እራሳቸውን ሁሌም ትክክል እንደሆኑ ያስባሉ ነገርግን ልክ እንደ ኩባያ አይነት ሰዎች አሉት ግን ክብራቸው ከሰው በታች ነው።

ነገር ግን በቀላሉ አይሰናከሉም ስራቸውም ከስማቸው በላይ ነው። ክርስትናቸውም በበዓልና ሰው ሲበዛ ብቻ ሳይሆን በማንኛም ጊዜና ስዓት ነው። ስለዚህ ልጄ አሁን የትኛውን አይነት ክብር ነው የምትፈልገው?
ልጅ፦ አባዬ እንደ ኩባያ ያሉት ምንኛ የታደሉ ናቸው።
አባት፦ እንግዲያውስ ፀልይ ሀብትም መለመንህ ልክ ነው ነገርግን አስራት በኩራት እየከፈልህ ነፍስህንም ቀልባት ሁሉም ሀብት የነፍስህም የስጋህም እንጂ የስጋ ብቻ አይደለምና።

በመጨረሻም ልጄ አጭር የልመና ቃል ልንገርህ ዘውትር ወደ ፈጣሪክ ስትጸልይ እንዲህ የሚለውን ቃል አዘውትር፦

''አምላኬ ሆይ ጥበብን እና ማስተዋልን ስጠኝ ጠቢቡ ሰሎሞን እንዳለው''
ይህ ከሆነ ሁሉንም ታገኛለህ።
ልጅ፦ እሺ አባቴ ከዛሬ በኃላ ጥበብና ማስተዋልን ስጠኝ በማለት እለምነዋለው።

"ከዚህ ታሪክ የምንማርው ከሁሉ የምትበልጠውን አብዝተን አምላካችንን እንድንለምነው ነው።
ጥበበኛ ብቻ ብንሆን ፍሪሃ እግዚአብሔር ከሌለን ምን ዋጋ አለው። ስለሆነም ጥበብን ከማስተዋል ጋር አድርገን ልንማጸን እና ልንጸልይ ይገባናል።
ምክንያቱም ''የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና።''

ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን፫
ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
@haymanotanednat
@haymanotanednat
@haymanotanednat
480 viewsedited  05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:50:24 «#አሥሩ የሕይወት መርሆዎች»

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ።
ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።

2. አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው፦ የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ? ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል
ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ
ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት ጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን
ሁን፦ ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ብዙ
ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው።እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት።ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይለወጣል።
መልካም ምሽት
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
@haymanotanednat
@haymanotanednat
@haymanotanednat
488 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:05:21 "የጥበብ ሁሉ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው"

ዮሴፍ የጲጥፋራ ሚስት ስትፈትነው እግዚአብሔርን ፈርቶ "እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኅጥያት እሰራለው" አለ። ኀጥያትን አለመስራት ከሰራንም ብኋላ ንስሐ መግባት በራሱ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እጅግ ብዙ ደስታ ያያል፣ እድሜውም በምድር ይረዝማል። መከራ ፈተና እንኳን ቢደርስበት እግዚአብሔር ፅናት ይሆነዋል። ዘመናችን በደስታ እንዲፈፀም እግዚአብሔርን እንፍራ። በምንሄድበት በምንውልበት በየትም ቦታ ብንሆን እግዚአብሔርን እናክብር እንፍራ።
ይ ላ ሉ
@haymanotanednat
@haymanotanednat
@haymanotanednat
538 views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 23:26:22
እናንተ ፍረዱኝ ! የ5ዓመት ልፋቴን ሳይቆጥሩ በአካል ጉዳቴ በሌላ የት/ርት ዘርፍ ከ0 ጀምር ተባልኩ !



እሄን ያህል ጊዜ የስነልቦና አገልግሎት ስሰጥ ለዚህ ልጅ የምለው ቃል አጥቼ አላወቀም ከ2 ሰዓት በላይ በዝምታ ወስጥ እሱን በማዳመጥ ቁጭ ካልኩ በዋላ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን በማለት ነበር የተለየውት ምን ማለት እችላለሁ

እሱም ምንም የምለው የለኝም ስለው ስላዳመጥከኝ አመሰግናለሁ አለኝ።

እናም ህይወት እንዴት ነች ግን ?


የእናንተ ቤተሰብ ቢሆን ምን....?

@BiniGirmachew
@BiniGirmachew
@BiniGirmachew


የእናንተን አስተያየት መስማት እፈልጋለሁ

እዚህ ላይ አድረሱኝ

@Asharayebot

ስለ እውነት ልብ ይነካል
639 views20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:51:38 #ከአዳመጥኩት_ትምህርት _ላካፍላችሁ

አንዱ እግዚአብሔር የለም አለ
አንዱ ደግሞ እሴብሆ/2/
ለእግዚአብሔር ባህሩን ተሻግረን /2/ ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የእኛ ሆነ
እያለ ከበሮ እየመታ ይዘምራል እግዚአብሔር የለም የሚለዉ መጣ ምን እያልክ ነዉ አለዉ ለእግዚአብሔር እየዘመርኩ አለ እንዴ እግዚአብሔር ምትለዉ እኮ ቀይ ባህር ከፈለ ምትለዉ ቀይ ባህር ትልቅ ባህር መስሎህ ነዉ አለዉ እንዴ እና ምን አይነት ነዉ አለዉ በር ላይ ያለችዉ ትንሽየ ቦይ የለችም በአንድ እግርህ ምትሻገራት እንደሷ እኮነች ለሱ ነዉ እንዴ ምትዘምረዉ እሱንማ እኔም እችላለሁ አለዉ ነዉ እንዴ አለዉ ያኛዉ ከበሮ አንስቶ እግዚአብሔር ይመስገን ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ ሲል ነገርኩህ አይደል ትንሽየ ናት አያዘምርም አታመስግነዉ አለዉ አሁን ነዉ እንጅ ማመስገን እንዴት አሁን ነዉ እንጅ እልልታ እንዴት አሁን ነዉ እንጅ ከበሮ እንዴት በዛ በትንሿ ቦይ ዉስጥ ያን ሁሉ የፈርኦንን ሰራዊት አፍኖ መግደሉ ገርሞኝ ነዉ እንጅ አለዉ። ላመስግን ካልን እንችላለን ለማመስገኛ ብዙ ምክንያት ሲኖረን ለማጉረምረም ምንም ምክንያት አይኖረንም ።

መምህር ምህረት አብ አሰፋ
ምንጭ ያለ ጭንቀት መኖር ከሚለዉ ስብከት

መምህራችን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን

በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤ መዝሙረ ዳዊት 95:2

ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 4:2

ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤ መዝሙረ ዳዊት 147:7

በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር የሐዋርያት ሥራ 16:25

ባለን በለለን ነገር በደስታችንም በሀዘናችንም ጊዜ እግዚአብሔርን እድናመሰግነዉ እርሱ ይርዳን አሜን
@haymanotanednat
@haymanotanednat
797 viewsedited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:46:23 @haymanotanednat
@haymanotanednat
603 viewsedited  04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 22:27:58 ቀኑ ቢመስል ጨለማ
ባንተ ስላለሁ በፍቅርህ ማማ
አንተ ያልከው ይሁን ብዬ በማመኔ
ሁሉን ስላለፍኩ ባለፈው ዘመኔ
ሁሉንም ነገሬ ላንተ ልተውና
በመጠበቅያዬ ልሁን ልበርታና!!
#እግዚአብሔር መልሴ ነውና
628 views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:58:18
784 viewsedited  03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:57:58 #እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዪሐንስ የልደት ክብረ በአል በሰላም አደረሳቹሁ ።ቅዱስ ዩሐንስ አባቱ ዘካርያስ እናቱ ኤልሳቤጥ ይባላሉ።በመላህኩ በቅዱስ ገብርኤል ብስራት መስከረም 26 ተፀንሶ ሰኔ 30 ቀን ተወለደ።አረመኔው ሄሮድስ ልጃቹሁን አምጡ ቢላቸው ኤልሳቤጥ ልጇን ይዛ ወደ በረሀ ዋሻ ገባች።ሄሮድስ በዚህ ተናዶ የዘካርያስን አንገት መስከረም 8 ቀን አስቆረጠ።ኤልሳቤጥም በየካቲት 16 ቀን አረፈች ።ስጋዋንም አንበሶች ቆፍረው ቀበሯት።ዩሐንስም በበረሃ እየኖረ ንሰሀ ግቡ እያለ ያጠምቅ ነበረ።ጌታንም በዩርዳኖስ ወንዝ ያጠመቀው ታላቅ አባት ነው።ሄሮድስም ዩሐንስን ወደ እስር ቤት አስገብቶት ነበር።በዚያን ጊዜ የሄሮድያዳ ልጅ ዘፈን ዘፈነች ንጉሱም የፈለግሽውን ላድርግልሽ ሲላት እናቷም የዩሐንስን አንገት ቆርጠህ ስጠኝ በይው አለቻት ። ንጉሱም በተናገረው እያዘነ መስከረም ሁለት ቀን የዩሐንስን አንገት ቆርጦ ሰጣት።የዩሐንስም አንገት ክንፍ አውጥታ 15 አመት እየዞረች አስተምራለች።የነብያት ቃል ኪዳን ይደርብን።
ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
አሜን አሜን አሜን "በፃድቅ ላይ የሚናገሩ የሽምገላ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ"መዝ,30፦18 .
ቅዱስ ዮሐንስ-ያልታሰበ ደስታ ያብስራቹሁ
@haymanotanednat
@haymanotanednat
785 viewsedited  03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ