Get Mystery Box with random crypto!

#ከአዳመጥኩት_ትምህርት _ላካፍላችሁ አንዱ እግዚአብሔር የለም አለ አንዱ ደግሞ እሴብሆ/2/ | ሃይማኖት አንድ ናት

#ከአዳመጥኩት_ትምህርት _ላካፍላችሁ

አንዱ እግዚአብሔር የለም አለ
አንዱ ደግሞ እሴብሆ/2/
ለእግዚአብሔር ባህሩን ተሻግረን /2/ ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የእኛ ሆነ
እያለ ከበሮ እየመታ ይዘምራል እግዚአብሔር የለም የሚለዉ መጣ ምን እያልክ ነዉ አለዉ ለእግዚአብሔር እየዘመርኩ አለ እንዴ እግዚአብሔር ምትለዉ እኮ ቀይ ባህር ከፈለ ምትለዉ ቀይ ባህር ትልቅ ባህር መስሎህ ነዉ አለዉ እንዴ እና ምን አይነት ነዉ አለዉ በር ላይ ያለችዉ ትንሽየ ቦይ የለችም በአንድ እግርህ ምትሻገራት እንደሷ እኮነች ለሱ ነዉ እንዴ ምትዘምረዉ እሱንማ እኔም እችላለሁ አለዉ ነዉ እንዴ አለዉ ያኛዉ ከበሮ አንስቶ እግዚአብሔር ይመስገን ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ ሲል ነገርኩህ አይደል ትንሽየ ናት አያዘምርም አታመስግነዉ አለዉ አሁን ነዉ እንጅ ማመስገን እንዴት አሁን ነዉ እንጅ እልልታ እንዴት አሁን ነዉ እንጅ ከበሮ እንዴት በዛ በትንሿ ቦይ ዉስጥ ያን ሁሉ የፈርኦንን ሰራዊት አፍኖ መግደሉ ገርሞኝ ነዉ እንጅ አለዉ። ላመስግን ካልን እንችላለን ለማመስገኛ ብዙ ምክንያት ሲኖረን ለማጉረምረም ምንም ምክንያት አይኖረንም ።

መምህር ምህረት አብ አሰፋ
ምንጭ ያለ ጭንቀት መኖር ከሚለዉ ስብከት

መምህራችን በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን

በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤ መዝሙረ ዳዊት 95:2

ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 4:2

ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤ መዝሙረ ዳዊት 147:7

በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር የሐዋርያት ሥራ 16:25

ባለን በለለን ነገር በደስታችንም በሀዘናችንም ጊዜ እግዚአብሔርን እድናመሰግነዉ እርሱ ይርዳን አሜን
@haymanotanednat
@haymanotanednat