Get Mystery Box with random crypto!

#እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዪሐንስ የልደት ክብረ በአል በሰላም አደረሳቹሁ ።ቅዱስ ዩሐንስ | ሃይማኖት አንድ ናት

#እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዪሐንስ የልደት ክብረ በአል በሰላም አደረሳቹሁ ።ቅዱስ ዩሐንስ አባቱ ዘካርያስ እናቱ ኤልሳቤጥ ይባላሉ።በመላህኩ በቅዱስ ገብርኤል ብስራት መስከረም 26 ተፀንሶ ሰኔ 30 ቀን ተወለደ።አረመኔው ሄሮድስ ልጃቹሁን አምጡ ቢላቸው ኤልሳቤጥ ልጇን ይዛ ወደ በረሀ ዋሻ ገባች።ሄሮድስ በዚህ ተናዶ የዘካርያስን አንገት መስከረም 8 ቀን አስቆረጠ።ኤልሳቤጥም በየካቲት 16 ቀን አረፈች ።ስጋዋንም አንበሶች ቆፍረው ቀበሯት።ዩሐንስም በበረሃ እየኖረ ንሰሀ ግቡ እያለ ያጠምቅ ነበረ።ጌታንም በዩርዳኖስ ወንዝ ያጠመቀው ታላቅ አባት ነው።ሄሮድስም ዩሐንስን ወደ እስር ቤት አስገብቶት ነበር።በዚያን ጊዜ የሄሮድያዳ ልጅ ዘፈን ዘፈነች ንጉሱም የፈለግሽውን ላድርግልሽ ሲላት እናቷም የዩሐንስን አንገት ቆርጠህ ስጠኝ በይው አለቻት ። ንጉሱም በተናገረው እያዘነ መስከረም ሁለት ቀን የዩሐንስን አንገት ቆርጦ ሰጣት።የዩሐንስም አንገት ክንፍ አውጥታ 15 አመት እየዞረች አስተምራለች።የነብያት ቃል ኪዳን ይደርብን።
ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
አሜን አሜን አሜን "በፃድቅ ላይ የሚናገሩ የሽምገላ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ"መዝ,30፦18 .
ቅዱስ ዮሐንስ-ያልታሰበ ደስታ ያብስራቹሁ
@haymanotanednat
@haymanotanednat