Get Mystery Box with random crypto!

ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamidabuhamid — ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamidabuhamid — ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)
የሰርጥ አድራሻ: @hamidabuhamid
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 588
የሰርጥ መግለጫ

ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
"ﺍﻗْﺮَﺃْ ﺑِﺎﺳْﻢِ ﺭَﺑِّﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻖَ"
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታ ስም"
አል ዐለቅ ምእራፍ/1
ውድ የ"አንብብ"ህዝቦች ሆይ!ይህ የኡስታዝ ዐብዱል ሀሚድ አማን የቴሌግራም ገፅ ሲሆን:በዚህ ገፅ ላይ የተለያዩ ኢስላማዊ መልእክቶች:በተለያየ ዘርፍ የሚሰጡ ተከታታይ ት/ቶችን በድምፅና በቪዲዮ የሚያገኙበት ነው።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-07 10:42:17 "ለተክፊር መቻኮል መሀይምነት በገዘፈባቸው ሰዎች ላይ ነው የሚበዛው"
---ኢማም አል ጘዛሊይ(ረሒመሁላህ)
329 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 19:52:17
ስስታም ፍቅርን ሲሰጥ አላየሁም!
ሁሌም ቢሆን ፍቅር የሚበቅለው በለጋሶች መዳፍ ነው!!!
_ሸምሱ ተብሪዝ
376 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 18:49:54
በብዙ ሰርጎ ገብና መጤ አስተሳሰቦች ምክንያት በተርታው ማህበረሰብ ክፍላችን ላይ ዐቂዳዊም ሆነ ፊቅሂያዊ ብዥታዎች ተበትነዋል፣ከፊሉ ከመስመሩ ወጥቷል ውስኑ በጥርጣሬ ማእበል አቋም አልባ ሆኖ እንዲወላውል ተገዷል!!!
የመረጃን ምንጭ ሳይመርጡ ከነፈሰበት መውሰድ ከዚህም በላይ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፤በዲን ስም የሰበከ ሁላ ዓሊም አይደለም፤ከማን ተረከበ? በማን ላይ ቀራ? ብሎ የእውቀት ሰንሰለቱን(ሰነድ)መጠየቅ ከዲን ነው፤
ያ ባይሆንማ የሻው ተነስቶ ያሻውን ባለ ነበር፤እንግዲ ይህን መስመር ነበር ሰለፎች የዘረጉልን፤እውቀት ከማንም ሲወሰድ፣ማንም እንደ ኡስታዝ ሲታይ አደጋው ከባድ ነው
ግንዛቤዎች ይጥሩ፤ብዥታዎች ይታረሙ፤በጭፍን የመነዳት ወቅት ይገታ!!!
_____
ኡስታዝ ሸምሱዲንን(ሐፊዘሁሏህ)በሐሪማ tv ተከታተሉዋቸው፤ታተርፋላችሁ
347 views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 18:16:50
በኡስታዝ ሸምሰዲን ሐምዛ የሚቀርበው መፋሂም የተሰኘው ትምህርታዊ መሰናዶ ስለአህሉሱና ወልጀምዓ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዞልን ይቀርባል።

ከ3፡00 ጀምሮ በሐሪማ ቲቪ ይጠብቁን
________________________
በኢትዮ-ሳት
Frequency - 11545
Symbol rate - 30000
Polarization - H እንዲታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን
________________________
በስልክ ቁጥራችን
+251 953 68 68 68
+251 954 68 68 68 ያግኙን
ሐሪማ ቲቪ
"የምጥቀት መሠላል!"
318 views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 18:07:59 የቀልብ በሽታ መንስኤዎች ስድስት ናቸው:–
–በንሰሃ ተስፋ...ይወነጅላሉ
–እውቀት ይቀስማሉ....አይተገብሩበትም
–ከተገበሩም ....ለአላህ ብለው አይሰሩም
–የአላህን ሲሳይ ይመገባሉ.... አያመሰግኑም
–አላህ በሰጣቸው ድርሻ....አይደሰቱም
–ሙታኖቻቸውን ይቀብራሉ.... አይገሰፁባቸውም
__
ኢማም አል ሐሰን አል በስሪይ(ረህመቱላሂ ዐለይህ)
https://t.me/HamidAbuhamid
311 viewsedited  15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 20:03:41
[ ሞት ...]
ስመ ጥሩ የሻፊዒይ መዝሀብ ሊቅ ኢማም አል ሙዘኒይ እንዲህ ይላሉ:–
"ኢማም አሽ ሻፊዒይ ለሞት በዳረጋቸው ህመም ላይ በነበሩበት ወቅት ልጠይቃቸው ገብቼ እንዴት አነጉ?ስል ጠየቅኳቸው፤እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱልኝ
"ከቅርቢቷ ዓለም የምጓዝ፣ወንድሞቼን የምለይ፣የሞትን ፅዋ የምጎነጭ፣ወደ አላህ የምቀርብ ሆኜ አነጋሁ፤በአላህ እምላለው ሩሔ የጀነት ነች ላባስራት፣ወይስ የጀሀነም ነች ላርዳት የማውቀው ነገር የለም"
___
ይህንን መራርና በጫንቃችን ተሸክመን የምንኖረውን እውነታ መዘንጋት፣ከአላህም ጋር ሆነ ከፍጡራን ጋር ለሚኖረን መስተጋብርና ትስስር ብልሹነት ዋነኛ ምክንያት ነው፤ለዚህም ነው ሰዪዳችን (ዐለይሂ ሶለዋቱላሂ ወሰላሙህ) "ጥፍናን ቆራጭ የሆነን ሞት አስታውሱ"በማለት አበክረው አደራ ማለታቸው፤በእያንዳዱ ቅፅበት ሟች መሆንን መዘከር የእውነተኛ አማኞኝ መገለጫ ነው፤ሰው ሞትን የዘነጋ ጊዜ ሰዋዊነቱ ይላሻል፣እንስሳዊነትን ቀስ በቀስ ይላመዳል፣ሲብስም ከእንስሳ የከፋ ይሆናል፣ለስጋዊ ህይወቱ እንጂ ወደ ቀጣዩ ዓለም ተሻግራ ስለምትኖረው ነፍሱ ማሰብ ይሳነዋል፤ለስጋዊ ፍላጎቱ ሲል ህሊናውን ሸጦ መንፈሱን ኮስሶ መኖር ይጀምራል፤ከተዋጠበት የጘፍላ እንቅልፍ የዘነጋው ሞት በድንገት ሲመጣበት ያኔ ይነቃል፤የተጋረጠበት ግርዶሽ ይገፈፋል፤ያሳለፈውን ህይወት ዞር ብሎ ሲመለከት ይፀፀታል፤ግና ያኔ ፀፀቱ አይፈይድ፤ደም እንባ ያለቅሳል፣አንዲትን በጎ ስራ ልስራ ሲልም ይማፀናል፤ምን ዋጋ አለው ምላሽ የሌለው ድምፅ ......ምፅ!!!
ይህ ከመሆኑ በፊት መንቃት ያዋጣል፣ከባቢንና ተቀማማጭን መምረጥ ፍቱን መፍትሄ ነው፤መቃብር ስፍራን መጎብኘት ቀጣዩን ዓለም ያስታውሳል።
____
ያ ረብ! እዝነትህን
379 viewsedited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 17:24:19
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተናጠል በኢማም አበል ሐሰን አል አሽዐሪይ ላይ፤በጥቅሉ ደግሞ በአሽዐሪይያ መዝሀብ ላይ የሚቀጠፉ ብዥታዎች መንስኤ መዝሀቡን ጠንቅቆ ካለማወቅ፣አልያም ሐቁን እያወቁ በነፍሲያ ህመም ታውረው ከመሆን አይወጡም፤ምክንያቱም ይህን እንደ ፀሀይ ፈንጥቆ የወጣና ለስንት ዘመናት ለኡመተል ኢስላም እያበራ የነበረ የዐቂዳ መስመርን በስህተት መፈረጅ በጣሙን የሚገርምና የሚያስደነግጥ ጉዳይ ነው።
እሙን ነው! ብዙሃኑ ማህበረሰባችን እውነትን የሚመዝንበትና የሚቀበልበት መስፈር አሁን አሁን ላይ ተዛብቷል፤ለምሳሌ ቀድሞ የሰማው፣ለመረዳት የቀለለው፣በጣፋጭ አንደበት የተነገረው ነገር ሁላ በልቡ ላይ ሰፊ ቦታን ይዞ ነው የሚደላደለው፤በሌላ መልኩ ደግሞ ከአንድ ወገን ብቻ የሰማውን አድምጦ አቋሙን የሚመርጥም ፍርደ ገምድል ልክ እንደዛው ተበራክቷል፤እውነታው ግን ይህ ሁላ አካሄድ ወደ ሐቅ ለማድረስ ፍፁም አስተማማኝ ያልሆነ መሆኑ ነው!!!
ጉዳዩ የዐቂዳ ሲሆን ደግሞ ክፍተቱና ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል እሰቡት!
____
ማታ 2:30 በ ይጠብቁ
330 viewsedited  14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 21:09:06 ◆ሹክር ማለት:–
"በፀጋው ታግዘህ እሱን አለማመፅ ነው"
–ኢማም ጁነይድ(ረሕመቱሏሂ ዐለይህ)
314 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 20:10:59 Live stream finished (85 days)
17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 19:49:27
የአምልኮ አምላኪ ....!!!
_____\\\__\\\\_____
ፍቅርን ኖረው ካስተማሩ፤አላህን አውቀው ካሳወቁ አያሌ ድንቅ ባሮቹ ውስጥ አንዱ የሆኑት አቡ የዚድ አል ቡስጣሚ(ረሕመቱላሂ ዐለይህ) ዘንድ ውስን ሰዎች መጥተው
[አላህን እንገዛለን፤ግን እንደው የአምልኮውን ለዛ(እርካታ) ለምን ይሆን የማናገኘው? ]ሲሉ ይጠይቋቸዋል፤አቡ የዚድም በመንገዱ ብዙ የለፉ፣ባለፉበት ያለፉ፣የጉዞውን እንከንና ፈውስ አብጠርጥረው የተረዱ ዓሪፍ ስለነበሩ ክፍተቱ ምን ጋር እንዳለ ነገሯቸው
" የዒባዳዎችን ጥፍጥና ማታገኙበት ምክንያትማ እናንተ አምልኮዎችን እንጂ አላህን አልተገዛችሁም፤በዛ ላይ ከፍቅሩ በተነጠለች ልብ ነው የተገዛችሁት፤ለሱ ቀረቤታ፣ትስስርና ውዴታ ብላችሁ አልሰራችሁም፤ሶላታችሁ ትእዛዙን ለመፈፀም ብቻ የሚደረግ እንቅስቃሴ አታድርጉ፤ሶላት ማለት ከሱ ጋር መገናኛ መስመራችሁ፣የሩሓችሁ መሰላልና ወደሱ መላቂያዋ ነው"በማለት መለሱላቸው።
_____
መደድ ያ ረብ!!!
403 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ