Get Mystery Box with random crypto!

[ ሞት ...] ስመ ጥሩ የሻፊዒይ መዝሀብ ሊቅ ኢማም አል ሙዘኒይ እንዲህ ይላሉ:– 'ኢማም አሽ ሻ | ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

[ ሞት ...]
ስመ ጥሩ የሻፊዒይ መዝሀብ ሊቅ ኢማም አል ሙዘኒይ እንዲህ ይላሉ:–
"ኢማም አሽ ሻፊዒይ ለሞት በዳረጋቸው ህመም ላይ በነበሩበት ወቅት ልጠይቃቸው ገብቼ እንዴት አነጉ?ስል ጠየቅኳቸው፤እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱልኝ
"ከቅርቢቷ ዓለም የምጓዝ፣ወንድሞቼን የምለይ፣የሞትን ፅዋ የምጎነጭ፣ወደ አላህ የምቀርብ ሆኜ አነጋሁ፤በአላህ እምላለው ሩሔ የጀነት ነች ላባስራት፣ወይስ የጀሀነም ነች ላርዳት የማውቀው ነገር የለም"
___
ይህንን መራርና በጫንቃችን ተሸክመን የምንኖረውን እውነታ መዘንጋት፣ከአላህም ጋር ሆነ ከፍጡራን ጋር ለሚኖረን መስተጋብርና ትስስር ብልሹነት ዋነኛ ምክንያት ነው፤ለዚህም ነው ሰዪዳችን (ዐለይሂ ሶለዋቱላሂ ወሰላሙህ) "ጥፍናን ቆራጭ የሆነን ሞት አስታውሱ"በማለት አበክረው አደራ ማለታቸው፤በእያንዳዱ ቅፅበት ሟች መሆንን መዘከር የእውነተኛ አማኞኝ መገለጫ ነው፤ሰው ሞትን የዘነጋ ጊዜ ሰዋዊነቱ ይላሻል፣እንስሳዊነትን ቀስ በቀስ ይላመዳል፣ሲብስም ከእንስሳ የከፋ ይሆናል፣ለስጋዊ ህይወቱ እንጂ ወደ ቀጣዩ ዓለም ተሻግራ ስለምትኖረው ነፍሱ ማሰብ ይሳነዋል፤ለስጋዊ ፍላጎቱ ሲል ህሊናውን ሸጦ መንፈሱን ኮስሶ መኖር ይጀምራል፤ከተዋጠበት የጘፍላ እንቅልፍ የዘነጋው ሞት በድንገት ሲመጣበት ያኔ ይነቃል፤የተጋረጠበት ግርዶሽ ይገፈፋል፤ያሳለፈውን ህይወት ዞር ብሎ ሲመለከት ይፀፀታል፤ግና ያኔ ፀፀቱ አይፈይድ፤ደም እንባ ያለቅሳል፣አንዲትን በጎ ስራ ልስራ ሲልም ይማፀናል፤ምን ዋጋ አለው ምላሽ የሌለው ድምፅ ......ምፅ!!!
ይህ ከመሆኑ በፊት መንቃት ያዋጣል፣ከባቢንና ተቀማማጭን መምረጥ ፍቱን መፍትሄ ነው፤መቃብር ስፍራን መጎብኘት ቀጣዩን ዓለም ያስታውሳል።
____
ያ ረብ! እዝነትህን