Get Mystery Box with random crypto!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተናጠል በኢማም አበል ሐሰን አል አሽዐሪይ ላይ፤በጥቅሉ ደግሞ በአሽዐሪይያ መዝ | ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተናጠል በኢማም አበል ሐሰን አል አሽዐሪይ ላይ፤በጥቅሉ ደግሞ በአሽዐሪይያ መዝሀብ ላይ የሚቀጠፉ ብዥታዎች መንስኤ መዝሀቡን ጠንቅቆ ካለማወቅ፣አልያም ሐቁን እያወቁ በነፍሲያ ህመም ታውረው ከመሆን አይወጡም፤ምክንያቱም ይህን እንደ ፀሀይ ፈንጥቆ የወጣና ለስንት ዘመናት ለኡመተል ኢስላም እያበራ የነበረ የዐቂዳ መስመርን በስህተት መፈረጅ በጣሙን የሚገርምና የሚያስደነግጥ ጉዳይ ነው።
እሙን ነው! ብዙሃኑ ማህበረሰባችን እውነትን የሚመዝንበትና የሚቀበልበት መስፈር አሁን አሁን ላይ ተዛብቷል፤ለምሳሌ ቀድሞ የሰማው፣ለመረዳት የቀለለው፣በጣፋጭ አንደበት የተነገረው ነገር ሁላ በልቡ ላይ ሰፊ ቦታን ይዞ ነው የሚደላደለው፤በሌላ መልኩ ደግሞ ከአንድ ወገን ብቻ የሰማውን አድምጦ አቋሙን የሚመርጥም ፍርደ ገምድል ልክ እንደዛው ተበራክቷል፤እውነታው ግን ይህ ሁላ አካሄድ ወደ ሐቅ ለማድረስ ፍፁም አስተማማኝ ያልሆነ መሆኑ ነው!!!
ጉዳዩ የዐቂዳ ሲሆን ደግሞ ክፍተቱና ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል እሰቡት!
____
ማታ 2:30 በ ይጠብቁ