Get Mystery Box with random crypto!

የአምልኮ አምላኪ ....!!! _____\\\__\\\\_____ ፍቅርን ኖረው ካስተማሩ፤አላህን አው | ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

የአምልኮ አምላኪ ....!!!
_____\\\__\\\\_____
ፍቅርን ኖረው ካስተማሩ፤አላህን አውቀው ካሳወቁ አያሌ ድንቅ ባሮቹ ውስጥ አንዱ የሆኑት አቡ የዚድ አል ቡስጣሚ(ረሕመቱላሂ ዐለይህ) ዘንድ ውስን ሰዎች መጥተው
[አላህን እንገዛለን፤ግን እንደው የአምልኮውን ለዛ(እርካታ) ለምን ይሆን የማናገኘው? ]ሲሉ ይጠይቋቸዋል፤አቡ የዚድም በመንገዱ ብዙ የለፉ፣ባለፉበት ያለፉ፣የጉዞውን እንከንና ፈውስ አብጠርጥረው የተረዱ ዓሪፍ ስለነበሩ ክፍተቱ ምን ጋር እንዳለ ነገሯቸው
" የዒባዳዎችን ጥፍጥና ማታገኙበት ምክንያትማ እናንተ አምልኮዎችን እንጂ አላህን አልተገዛችሁም፤በዛ ላይ ከፍቅሩ በተነጠለች ልብ ነው የተገዛችሁት፤ለሱ ቀረቤታ፣ትስስርና ውዴታ ብላችሁ አልሰራችሁም፤ሶላታችሁ ትእዛዙን ለመፈፀም ብቻ የሚደረግ እንቅስቃሴ አታድርጉ፤ሶላት ማለት ከሱ ጋር መገናኛ መስመራችሁ፣የሩሓችሁ መሰላልና ወደሱ መላቂያዋ ነው"በማለት መለሱላቸው።
_____
መደድ ያ ረብ!!!