Get Mystery Box with random crypto!

በብዙ ሰርጎ ገብና መጤ አስተሳሰቦች ምክንያት በተርታው ማህበረሰብ ክፍላችን ላይ ዐቂዳዊም ሆነ ፊቅ | ዐብዱል ሀሚድ አማን(አቡ ሱሀይል)

በብዙ ሰርጎ ገብና መጤ አስተሳሰቦች ምክንያት በተርታው ማህበረሰብ ክፍላችን ላይ ዐቂዳዊም ሆነ ፊቅሂያዊ ብዥታዎች ተበትነዋል፣ከፊሉ ከመስመሩ ወጥቷል ውስኑ በጥርጣሬ ማእበል አቋም አልባ ሆኖ እንዲወላውል ተገዷል!!!
የመረጃን ምንጭ ሳይመርጡ ከነፈሰበት መውሰድ ከዚህም በላይ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፤በዲን ስም የሰበከ ሁላ ዓሊም አይደለም፤ከማን ተረከበ? በማን ላይ ቀራ? ብሎ የእውቀት ሰንሰለቱን(ሰነድ)መጠየቅ ከዲን ነው፤
ያ ባይሆንማ የሻው ተነስቶ ያሻውን ባለ ነበር፤እንግዲ ይህን መስመር ነበር ሰለፎች የዘረጉልን፤እውቀት ከማንም ሲወሰድ፣ማንም እንደ ኡስታዝ ሲታይ አደጋው ከባድ ነው
ግንዛቤዎች ይጥሩ፤ብዥታዎች ይታረሙ፤በጭፍን የመነዳት ወቅት ይገታ!!!
_____
ኡስታዝ ሸምሱዲንን(ሐፊዘሁሏህ)በሐሪማ tv ተከታተሉዋቸው፤ታተርፋላችሁ