2021-09-10 06:17:13
ይህ ነው እውነታው ክፍል 1 ካፊሮች(አይሁዶች እና ክርስቲያኖች) እስምልናን ለማጠልሸት እና የእነርሱን ሃይማኖት እውነት ለማስመሰል ሲጥሩ፣ ከመፅሃፎቻቸው ተወጣጥቶ ሃይማኖታቸው ውድቅ መሆኑ ሲነገራቸው፤ እስልምናም ክርስትናን እንደሚደግፍ፣እየሱስ ጌታ መሆኑን የሚገልፅ አንቀፅ በቁርአን ውስጥ አለ ብለው ይቀጥፋሉ፣ ሙስሊሞችን ለማደናገር እና ክርስቲያኖችም የልብ ልብ እንዲሰማቸው ለማድረግ ይሞክራሉ። ከነዚህም መሀከል: በሱራ አንቢያእ 21:91 ላይ ያለውን ስለ ዒሳ (እየሱስ) የአላህ ሰላም በእርሱ ላይ ይሁንና የተጠቀሰው አንዱ ነው።
﴿وَالَّتي أَحصَنَت فَرجَها فَنَفَخنا فيها مِن روحِنا وَجَعَلناها وَابنَها آيَةً لِلعالَمينَ﴾
[Al-Anbiyâ': 91]
ትርጉም: <<ያቺንም ብልቷን ከዝሙት የጠበቀችውና በእርሷም ውስጥ
ከነፍሳች የነፋንባት ከዛም እርሷንም ልጇንም ለአለማት ተአምር ያደረግናቸውን መርየምን አስታውስ>>
ይህን አንቀፅ ይዘው ከእራሱ ነፍስ ዘራበት ብርቅዬ ልጁ መሆኑን አላህ መስክሯል በቁርአኑ ብለው ይሞግታሉ።
ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ እንዲህ የሚሉ ተመሳሳይ አንቀፆች አሉ። ለምሳሌ በሱረቱ ሷድ 38:72 ላይ ስለ አባታችን አደም ሲገልፅ እንዲህ ይላል:
﴿فَإِذا سَوَّيتُهُ وَنَفَختُ فيهِ مِن روحي فَقَعوا لَهُ ساجِدينَ﴾
[ص:72]
ትርጉም: <<አፈጣጠሩን አሳምሬ በፈጠርኩት እና
ከመንፈሴም በነፋሁበት ጊዜ፣ለእርሱ ሰጋጆች ስትሆኑ ተዋደቁለት አልኩ>> ቁርአን 38:7
በሌላ ቦታም ለእየሱስ ብቻ ሳይሆን ለአደምም ከመንፈሴ ነፋሁበት ይላል:
ቁርአን 15/29፣ 32/9 ይመልከቱ። ታድያ እየሱስም አዳምም የፈጣሪ ልጆች፣አንድ ሶስተኞች (ስላሴ ውስጥ የሚካተቱ)ናቸውን? በጭራሽ! ታድያ ምንድ ነው የተፈለገበት? ይህ የተፈለገበት እየሱስን ለማላቅ ጅብሪልን አዘን በእርሷ ላይ ዒሳ እንዲረገዝ አደረግን ማለት ነው የተፈለገነት(ተፍሲር በገዊን ይመልከቱ)። ደግሞ እኛ አለ እነ ማንን ነው እኛ ያለው አላህ? የሚል አይጠፋም። ይህ ከዚ በፊት ብዙ የተብራራበት ስለሆነ ልለፈው። ግራ የገባው ካለ ያሳውቀን።
ሌላው ማምቻቻው:
﴿إِذ قالَتِ المَلائِكَةُ يا مَريَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِنهُ اسمُهُ المَسيحُ عيسَى ابنُ مَريَمَ وَجيهًا فِي الدُّنيا وَالآخِرَةِ وَمِنَ المُقَرَّبينَ﴾ [الإمران: 45]
ትርጉም: መልአክቶችም መርየም ሆይ አላህ ከእርሱ በሆነ ቃል ስሙም አልመሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በሆነ በዚህ አለምና
በመጨረሻውም አለም የተከበረና ከባለመዋሎችም በሆነ ልጅ ያበስርሻል ባሏት ጊዜ አስታውስ(ቁርአን 2/45)
ይህ አንቀፅ ግልፅ ቢሆንም ለማምታታት ይጠቀሙበታል። ግና ግልፅ ነበር የትኞችም ነብያት፣ደጋግ የአላህ ባሮች እንደየ ደረጃቸው በሁለቱም ሃገር የተከበሩ እና የላቁ ናቸውና በእየሱስ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሙሳንም በዚሁ ቃል እንዲህ ሲል ገልፆታል:
﴿يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا لا تَكونوا كَالَّذينَ آذَوا موسى فَبَرَّأَهُ اللَّهُ مِمّا قالوا وَكانَ عِندَ اللَّهِ وَجيهًا﴾
[احزاب: 69]
ትርጉም: እናንተ ያመናችሁ ሆይ ሙሳን እንዳሰቃዩት ሰዎች አትሁኑ። አላህም ካሉት ነገር ሁሉ አጠራው።
አላህም ዘንድ ባለ ሞገስ ነበር። ሌሎችም በርካታ ማስረጃዎች አሉ። (ቁርአን 4:98፣17:70 ይመልከቱ)
ሌላው አደራ የምለው ብዙ ጊዜ ሙስሊም ነበርን፣ክርስትያን ሆነን ነው እያሉ የሚያስተምሩ ሰዎች ዝም ብለው ጥቅስ እየጠቀሱ፣ ወይ ግማሹን ቆርጠው ይሰጧቹዋል። ብርቅ አይደለም እነ ቢኒያም ፍሬው ሌሎችም ቆራርጠው ሲያስተምሩ ያየነው ነገር ነው። ካምፓስ እያለሁ እንዲህ ያሉ ውሸቶች ፔንጤ ጓደኞቼ ያመጡልኝ ነበር። ግን አንቀፁን ሳሳያቸውና ጭራሽ የማይገናኝ አንቀፅ ሲሆን ይገረሙም ነበር። ስለዚህ ቁርአንም ሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲነገረን ከመፅሃፎቹ እናረጋግጥ፣አንድ አንቀፅ ብቻ ይዘን ከፊት እና ከኋላው ያለውን ሳናረጋግጥ አንወስን። ያልገባን ነገር ከሆነ እንጠይቅ። በጭፍን አንከተል።
@amhakfelagijemaa
ለሃሳብ አስተያየቶ
@Dsiaunivbot
192 viewsحيدر مزمل, 03:17