Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌም ውብ ነሽ እማ እናት ምን ብታረጅ ብትሆንም ጎስቋላ፣ ቤቷ ያልተዋበ ቢሆንም ሰቃላ፣ ምግቧም | Ethiopian Universities Muslim Association /Ethio-UMA/

ሁሌም ውብ ነሽ እማ

እናት ምን ብታረጅ ብትሆንም ጎስቋላ፣
ቤቷ ያልተዋበ ቢሆንም ሰቃላ፣
ምግቧም የታጨቀ ሆኖ ባይበላ፤
እናት ግን እናት ነች ፍቅሯ ብቻ በቂ፣
ጠረን፣መዓዛዋ ሁሌም ተናፋቂ።
እናት እናት የሚል ጠረን መዓዛዋ፣
ከአንገቷ ስር አለ ቢያረጅም ገላዋ።
ፊቷ ቢሸበሸብ፣ቢያጥር ፀጉሯ፣
እጇ ቢኮማተር፣ቢያነክስ እግሯ፣
እይታው ቢገደብ፣አይኗ ቢያነባ፣
መቀነት ቢያሻው፣ቢጎብጥም ወገቧ፣
መስማት ቢያዳግተው፣ጆሮዋ ቢደክም፣
ምላሷ ተሳስሮ፣ድምፇ ምን ቢያዘግምም።
ይሄ ሁሉ ሆኖ እርሷን ለታደለ፣
እናት እናት የሚል ጠረን መአዛዋ ከላዯ ላይ አለ፣
ክብሯን ለተረዳ፣በፍቅሯ ተለክፎ ሩ~ቅ ለዋለለ


ibnu muzemil
https://t.me/amhakfelagijemaa