Get Mystery Box with random crypto!

ስምንት ጠቃሚ ምክሮች '''''''''''''''''''''''''''''''''' 1,ከሰው | Ethiopian Universities Muslim Association /Ethio-UMA/

ስምንት ጠቃሚ ምክሮች
""""""""""""""""""""""""""""""""""
1,ከሰው ጋር አትፎካከር:— ምክንያቱም ሁሉም አላህ የፈቀደለት ነውና የሚያገኘው።ደግሞም መፎካከር ወደ ቅናት ይወስድሀል፤ቅናት ወደ ጥላቻናመጥመም ይጋብዛልና
2,ያለህን ተመልከት:—ያለህ ነገር ተመልክተህ ጌታህን አመስግን፤የሌለህን ምትመኝና ሁሉም የሚያምርህ ከሆነ በሀሳብ ዋልለህ ትጠፋለህ፣ያለህንም ታጣለህ።
3,እራስህን ምሰል:—ሰዎችን አትከተል የሆነ የራስህ የሆነ አላህ የሰጠህ ጥበብ አለህና እሱን ፈልገህ ለማዳበር ሞክር እንጂ ሰዎችን ለመምሰል አትሞክር መምሰልም አትችልምና።
4,ሁሉንም ለማስደሰት አትሞክር:—አንተ ለማንም ደስታ መስጠት አትችልም ደስታ ከአላህ ነው።ሰዎችን ለማስደሰት ሰበብ ብትሆንም ሁሉንም ማስደሰት አትችልም።ምክንያቱም አንተ አስደስታቸዋለሁኝ ስትል ሊያሳምማቸው ይችላልና።
5,የውሸት ደስታን አትፈልግ:—የእውነተኛ ደስታ ሚገኝበትን መንገድ አፈላልግ እንጂ ደስታን ፍለጋ የውሸት መንገድ አትጓዝ።ደስታ ሳይሆን ሀዘን ነው የሚሆነው ትርፉ።
6,ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ቅን ሁን:—በህይወት አጋጣሚህ የምታገኛቸው ሰዎች የወደፊት የህይወት አጋርህም ሊሆኑ ይችላሉ፤ዳግም ባታገኛቸው እንኳን ጌታህ ዘንድ ቦታ ታገኝበታለህና ሁሌም ቅን አሳቢ፣ መልካም ሰሪ፣ለሰዎች የምታዝን ሁን።
7,መለወጥ ማትችላቸውን ነገራቶችን ተቀበላቸው:—ጌታህ ላንተ ያለው የሰጠህ ስጦታ አለ ያነገር ላንተ በቂ ባይሆን እንኳ መቀየር ማትችለው ነገር ከሆነ ለመቀየር አትሞክር አይቀየርምና።
8,የራስህን ትክክለኛ ወዳጅ ሁን:—ለራስህ አስብ፣ለራስህ መልካም ሁን፣እራስህን አትጣል ግን በጣም ሰዎችን የሚያስረሳ አይነት እራስ ወዳድ አትሁን።

ibnu muzemil
@amhakfelagijemaa