Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_digital_library — Ethiopian Digital Library
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ebc
Bbc
Exit
Exitexam
Арада
Result
Raya
Rayauniversity
Futureready
Skillup
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_digital_library
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 66.24K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-06-20 11:37:56
አሜሪካ - የመጽሐፍ ቅዱስ አስርቱ ትእዛዛትን የሚያሳይ ፖስተር እንዲለጠፍ

የአሜሪካዋ ሉይዚያና ግዛት በሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና የዩኒቨርሲቲዎች መማሪያ ክፍሎች ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ አስርቱ ትእዛዛትን የሚያሳይ ፖስተር እንዲለጠፍ አዘዘች።

ቴክሳስ፣ ኦክላሆማ እና ዩታን ጨምሮ ሌሎች በሪፐብሊካን የሚመሩ ግዛቶች ተመሳሳይ ህጎች በቅርቡ እንደቀረቡ ቢቢሲ ተመልክቷል።

#BBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.2K viewsedited  08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-20 11:21:44
በ87 አመታቸው ሚኒስትሪ ተፈታኙ የዕድሜ ባለጸጋ

በ87 አመታቸው የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና እየተቀበሉ ያሉት የዕድሜ ባለጸጋ ተማሪ ማሞ ጋንገርሺ መነጋገሪያ ሆነዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኣሪ ዞን ደቡብ ኣሪ ወረዳ ቲኪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን 6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ዞናዊ ፈተና እየወሰዱ የሚገኙት አባት መነጋገሪያ ሆነዋል።

ተማሪ ማሞ ጋንጋርሺ የ16 ልጆች እና 36 የልጅ ልጆች እንዲሁም 2 የልጅ ልጅ ልጆችን ያዩ ዕድሜ ጠገብ አባት መሆናቸውን ከጂንካ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለመማር ዕድሜ ያልገደባቸው ተማሪ ማሞ 87 አመት የሆናቸው ሲሆን ለትውልዱ ትምህርት ለመማር መቼም ቢሆን ጊዜው አይረፍድም የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ችለዋል። #EBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
9.0K viewsedited  08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-19 16:37:27 በአዋጁ በተጀመረው የቤት ኪራይ ውል አከራዮች ከፍተኛ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑ ተከራዮችን አስጨንቋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት ኪራይ ውል ምዝገባ በሁሉም ወረዳዎች ማካሄድ ከጀመረ በኋላ፣ አከራዮች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እያደደረጉ በመሆናቸው ተከራዮች ከአቅማቸው በላይ መሆኑንና መጨነቃቸውን እየገለጹ ነው፡፡ መንግሥት የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ መናርን ለማስተካከል በመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም. ‹‹የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር›› አዋጅ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ አዋጁ የተመዘገበ የቤት ኪራይና ውል የተፈጸመበት የኪራይ ዋጋ ለሁለት ዓመት ይፀናል ይላል፡፡

በአዋጁ መሠረት የከተማ አስተዳደሩ የውል ምዝገባ ማካሄድ የጀመረ ሲሆን፣ ምዝገባው በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተመላክቷል፡፡ ይሁንና በርካታ አከራዮች ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የኪራይ ዋጋ መጨመር አንችልም በማለት አሁን ከፍተኛ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆናቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ፡፡

ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከል ላፍቶ አካባቢ የሚገኝ ኮንዶሚኒየም ተከራይታ የምትኖርና ስሟን መግለጽ ያልፈለገች ተከራይ፣ የውል ምዝገባ ከተጀመረ በኋላ 20 ሺሕ ብር ትከፍልበት የነበረው ቤት 30 ሺሕ ብር እንድትከፍል እንደተነገራት ገልጻለች፡፡

በተመሳሳይ በፊት ይከፍሉት ከነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ በእጥፍ የተጨመረባቸው ሌላ ግለሰብ፣ ይህ የተፈጠረው በሕጉ ላይ ባለው ክፍተት ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ ‹‹አዋጁ የኪራይ ዋጋውን በካሬ ሜትር መክፈል እንዲቻል ቢደነግግ ወይም የኪራይ ውሉን ስንፈራረም አንድ ተከራይ መጨመር ያበትን ዋጋ መጠን ቢያሳውቅ አሁን የሚነሱ ቅሬታዎች አይቀርቡም፤›› ነበር ብለዋል፡፡ አሁን የተነሳው ቅሬታ ወደፊትም በአከራይና ተከራይ መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡  

‹‹የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር›› አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር መመርያ ቁጥር 7/2016 አውጥቷል፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ውል መዝጋቢ ባለሙያ አከራይና ተከራይ ውሉን በፈቃዳቸው የሚዋዋሉ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚኖርበት በመመርያው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም አከራይና ተከራይ ለምዝገባ የሚያቀርቡት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የዋጋ ጭማሪ ካለው፣ የከተማ አስተዳደሩ የቤቶች ልማትና አስተዳዳር ቢሮ በሚያወጣው የዋጋ ጭማሪ ተመን መሠረት የተደረገ መሆኑን የወረዳ ጽሕፈት ቤት እንደሚያረጋግጥ የተደነገገ ሲሆን፣ በተመዘገበው ውል ከሠፈረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በላይ ክፍያ ሲፈጸምም ለወረዳው ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ፣ በስልክ ወይም በሌላ በማናቸውም የመገናኛ ዘዴዎች ለተቆጣጣሪው አካል ቅሬታውን ሊያቀርብ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ የንጋትኮከብ አባቡ፣ የውል ምዝገባው የሚካሄደው በአከራይና በተከራይ ስምምነት ብቻ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ምዝገባው የሚካሄደው አከራይና ተከራይ በተስማሙበት ነው፣ ካልተስማሙ ምዘገባውን አናካሂድም፤›› ከማለት ባለፈ ቢሮው ሌላ መፍትሔ ይኑረው ወይም አይኑረው ያሉት ነገር የለም፡፡ ዘገባው የሪፖርተር ነው።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
10.8K viewsedited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-19 16:02:37 17 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ - ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ያሉ17 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ዩኒሴቭ (UNICEF) አስታወቀ።

ዩኒሴፍ 3.5 ሚሊዮን የሚገመቱ በአንደኛ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ ሕፃናት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ሥጋት መጋለጣቸውንና ይህም ትምህርት ላይ የተጋረጠውን ቀውስ የበለጠ ማባባሱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት "ችግር ፈቺ ያልሆነ፣ የሀገሪቱን ኑሮ እና ተጨባጭ ጉዳዮች የማይመለከት መሆኑ" በውጤትም ሆነ በጥራት ማሽቆልቆል እየታየበት መሆኑን አንድ የትምህርት ባለሙያ ተናግረዋል።

በጦርነትና ግጭት ክፉኛ እየተጎዳ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ሁኔታ፤ ከዚያም ያለፉት የመንግሥት ሠራተኞች በደሞዝ ማነስ እየተፈተኑ ለትምህርት የሚሰጠውን ዋጋ እየጌዳ ስለመሆኑ ይነገራል።

ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ ከጠቅላላ ትምህርት ሰጪ 47 ሺህ ገደማ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸው የላቁት አራት ናቸው ማለቱ ባለፈው ዓመት የተሰማ አስደንጋጭ እውነታ ሆኖ አልፏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ሕፃናት ትምህርትን ለማረጋገጥ ጥረቶችን እንደሚመራ ያስታወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ ማዕከል ትናንት ባወጣው መረጃ ደግሞ 17 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንሕፃናትና ታዳጊ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
10.7K viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-19 10:15:18 #Revised

Exit Exam Schedule

የተሻሻለው የመውጫ ፈተና ፕሮግራም

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.7K viewsedited  07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 10:04:18
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/

በ2017 የትምሀርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤቶች ላይ ወጥነት ያለው የትምህርት አተገባበር በማስፈለጉ የትምሀርት የጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ይጀምራል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
6.0K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 12:31:57 ለ62 ሺህ መምህራን የክረምት ሥልጠና

በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ዙሪያ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስትር አስታውቀዋል። ሚኒስቴሩ በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
9.0K viewsedited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 12:31:14 ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር 22 ሺህ የሚደርሱ የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን አስታውቀዋል።

በተለይም ለተማሪዎች የሚሰጠው የሪሚዲያል ፈተና መጀመሩን በማስታወቅ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ፈተናውን የተሳለጠ ለማድረግ ለፈታኝ መምህራን በቂ ሥልጠና እየሰተጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑን ተከትሎ ለዚህ የሚረዳ በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.3K viewsedited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 12:29:59
የእርዳታ ጥሪ

ይህ የ18 ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሙሉጌታ ብርሃኑ ይባላል!

የጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ "የአጥንት መቅኔህ ደም ማምረት ስላቆመ ወደ ውጭ ሔደህ መታከም አለብህ" ብሎታል።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ የነበረው ተማሪ ሙሉጌታ፥ አሁን ላይ በህይወት እና ሞት መካከል ይገኛል። በሚያሳዝን ሁኔታ በየቀኑ ደም ይሰጠዋል!

ብቸኛ ወንድሙ ዘካርያስ ብርሃኑ ትምህርቱን አቋርጦ ለመድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለሟሟላት እየጣረ ቢሆንም ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት የእናንተን ድጋፍ ይጠይቃል።

በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልገው ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ስለሆነ በፀሎት እያሰባችሁት እባካችሁን ሼር በማድረግ አግዙት

"ለመልካም ሥራ ረፍዶ አያውቅም!"
አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000402392607 - ዘካርያስ ብርሀኑ (ወንድም)
ስልክ ቁ. 0961237095 - ዘካርያስ
ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት
7.6K viewsedited  09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-14 10:13:33
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ክፍፍል

የፌደራል መንግሥት ለ2017 በጀት ዓመት ከያዘው 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 39 ቢሊዮን ብር ያህሉ ከመንግሥት ግምጃ ቤት ወጪ ሆኖ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲከፋፈል መድቧል።

ለፓርላማ በቀረበ የበጀት ረቂቅ ሰነድ ላይ እንደሚታየው 13 ዩኒቨርሲቲዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸዋል።

ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግሥት መደበኛ በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ባህርዳር ዩኒቨርስቲ 1.8 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል።

ከመንግሥት ግምጃ ቤት 1.7 ቢሊዮን ብር የሚሰጠው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በክፍፍሉ ሦስተኛውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የሚያገኝ ይሆናል። ጅማ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በአራተኛ እና በአምስተኛነት ይከተላሉ።

የፌደራል መንግሥት በጀትን የሚያዘጋጀው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ባካሄደው የበጀት ስሚ መርሐግብር ዩኒቨርሲቲዎች “በተቀመጠላቸው ጣሪያ መሰረት” የበጀት ዕቅዳቸውን አስተካክለው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር አይዘነጋም። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
7.4K viewsedited  07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ