Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_digital_library — Ethiopian Digital Library
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ebc
Bbc
Exit
Exitexam
Арада
Result
Raya
Rayauniversity
Futureready
Skillup
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_digital_library
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 66.24K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-05-26 14:03:28
ንቦች ነን! አዎ ንቦች ነን!

ስራችን መለያችን!

አንድነታችን ጉልበታችን!

ፍታዊነትና ግልጸኝነታችን መለያችን!

ቦታንና አካባቢን ሳንመርጥ!

ለደንበኞች እድገት በአብሮነት በሁሉም ቦታ በመገኘት ቀዳሚ ነን!

ይምጡ ቤተሰብ ይሁኑ!!!

የቴሌግራም ትስስር ገጻችንን ይከታተሉ!

አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት መተግበሪያዎን ይጫኑ!

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!
10.3K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-26 11:08:59 ለ5 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት እና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚንስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት የወላይታሶዶ፣ጋምቤላ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ከሃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፤ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፌድራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መስሪያ ቤቶች ውስጥ እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት ውስጥ ተካተዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
11.7K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-25 15:39:37 ኤች አይ ቪ ቫይረስ

በህብረተሰቡ መዘናጋት ምክንያት በከፍትኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ የሚነገርለት ኤች አይ ቪ ኤድስ በተለይም በተለያዩ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ በሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን በከፍትኛ ሁኔታ እያጠቃ እንደሚገኝ በጤና ሚኒስትር የኤች አይ ቪ ቫይረስ ሚዲያ ፎረም ጉባኤ ላይ  የጤና ሚኒስትር ተወካይ አቶ ሀብታሙ ካሳ ገልፀዋል።

ብስራት ሬድዮ ከዚህ ቀደም እንደዘገበዉ ባለፉት 9 ወራት ብቻ በኢትዮጵያ ወደ 10 ሺ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በሀገሪቱ የተፈጠሩ የተለያዩ ማህበራዊ ቀዉሶች ህብረተሰቡ ቫይረሱን እንዲዘነጋና በሌሎች ጉዳዮች እንዲጠመድ መሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱ እንዲያንሰራራ ማድረጉ ተነስቷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በተደርገ ጥናት ሶስት የማህብረሰቡ ክፍሎች ማለትም መለዮ ለባሾች፣ የረጅም ርቀት ከባድ መኪና አሽክርካሪዎች እና የቤት ሰራተኞች በቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቁ እንደሚገኙም ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በፎረሙ ላይ ተገኝተዉ ገለፃ ያደረጉት የጤና ሚኒስተር ተወካይ አቶ ሀብታሙ ካሳ ህብረተሰቡ ካለበት መዘናጋት ወጥቶ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ሲጠቀስ በተለየም ለወጣቱና ለታዳጊዉ  አስፈላጊዉን ግንዛቤ ማስጨበት ስራ ካልተሰራ አሳሳቢ መሆኑን ለብስራት ሬድዮ ገልፀዋል። #ብስራት_ሬድዮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
11.5K viewsedited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-25 13:18:47 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሳይበር ጥቃት እንዳይሰረቅ ዝግጅት ተደርጓል 

በበይነ መረብ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሳይበር ጥቃት እንዳይሰረቅ ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ " በዚህ ዓለም ምንም አይነት ችግር የሌለበት ነገር የለም። ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ ችግር / ጉድለት ይኖረዋል ያለን ምርጫች ግን ችግሩን የመከላከል አቅም ጎን ለጎን መገንባት ነው " ብለዋል።

በበይነ መረብ የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም " ያሉት ዋና ዳይሬክቲ ፥ " የሳይበር ደህንነት (ሴክዩሪቲ) ስራዎች ሞያው መሳሪያዎች አቅም ባላቸው ተቋማት በኩል ተገቢ የሆነ ዝግጅት አድርገን እየሰራን ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ፈተናው ብዥታ ለመፍጠር የሚፈልጉ ፣ ፈተናው ላይ ጥቃት ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ማወቅ ያለባቸው ይሄ የፖለቲካ ፣ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ማንም ወላጅ ልጁን አስተምሮ የሚያደርስበት ስለሆነ ሁለት ሶስቴ ማሰብ አለባቸው ፤ ተማሪዎቹ ነገ ለሀገር እዳ እንዳይሆኑ ማሰብ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ከኦንላይን ፈተናው ጋር በተያያዘ ማንም አካል ወላጆችን " ኮምፒዩተር አቅርቡ " አላለም ፤ ሊጠየቁም አይገባም ከተጠየቅም ስህተት ነው ተብሏል። ፈተና የሚሰጠው መንግሥት በሚያቀርበው አቅርቦት / ኮምፒየተር እንደሆነ ተመላክቷል። ይህ ማለት የኮምፒዩተር አቅም ኖሯቸው ት/ቤታቸውን ማገዝ የሚፈልጉ ዜጎችን አይችሉም ማለት አይደለም ተብሏል።

የወረቅት ፈተናን በተመለከተ አሁን ላይ ህትመት ወደ መጠናቀቁ ሲሆን ፈተናው ልክ እንዳለፉት ፈተናዎች ደህንነቱ እንዲጠበቅ በቂ ዝግጅት መደረጉ፣ በክፍል ውስጥም ኩረጃ እንዳይኖርና ተማሪዎች በራሳቸውን ሰርተው እንዲያልፉ ካለፈው በጠነከረ ሁኔታ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

Credit: Tikvah

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
5.5K viewsedited  10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-25 12:21:41 በዓለም ላይ በከፍተኛ መጠን ዓይነ-ስውርነቶች ከሚያስከትሉ ምክንያቶች ሁለቱ ቀዳሚዎቹ ነጩ እና ጥቁሩ ዓይነ-ስውርነቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡

ነጩ - ሞራ ግርዶሽ

ሌንስ፡- የዓይን ፊተኛዉ ክፍል ዉስጥ ያለ ንዑስ-ዓይን አካል ሲሆን - በተፈጥሮዉ ጥርት ያለ ነዉ፡፡ ስራዉ ብርሃንን ወደ ኃለኛዉ የዓይን ክፍል - የብርሃን ግድግዳ(ረቲና) - መርቶ ማሰተላለፍ አንዱ ነዉ፡፡

ሞራ ግርዶሽ፡- ሌንስ ጥራቱን በተለያዩ ምክንያት ሲያጣ - በተለያየ መጠን ወደ ነጭነት ሲቀየር እና ዋናዉ አገልግሎቱ ሲታወክ - ሞራ ግርዶሽ ተከሰተ ይባላል፡፡ ይህ ዓይነ-ስዎርነትን ከሚያመጡ ምክንያቶች በዓለም ላይ በአንደኛ ደረጃ ይቀመጣል ፡ ይህም ከግማሽ በላይ ይይዛል፡፡ ሞራ ግርዶሽ አብዛኛዉ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚክሰት ሲሆን ሌላው ደግሞ ከእድሜ መግፋት ጋር ያልተያያዘ ነዉ፤ በብዙ ምክንያት ሊመጣ ይችላል ፡ ለምሳሌ .. ከግርዶሹ ጋር አብሮ በመወለድ(ብዙ ምክንያቶች አሉት)፣ በምት ፣ እስቴሮይድ መድሃኒት ከመጠቀም ጋር የተየያዘ፣ በዉስጣዊ የዓይን ቁጣ፣… ወዘተ

ሆኖም ይህ የሞራ ግርዶሽ በቀዶ-ጥገና የሚግላገሉት የዓይነ-ስዉርነት ምክንያት ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቁሩ - ግላኮማ ይልቅ ነጩ-ሞራ ግርዶሽ ለታማሚዉም ለሀኪሙም ቀዶ-ጥገና ከተከናወነ በኃላ ትልቅ የእርካታ እና የደስታ ምንጭ ነዉ፡፡ የሀዘን እና የብስጭት ምንጭ የሚሆነዉ ሞራ-ግርዶሹ ተጉዳኝ የዓይነ-ስዉርንት የሚያመጣ ምክንያት ካለዉ/ካሉት ነዉ….አንዱም ያ..ጥቁር-ግላኮማ ሊሆን ይችላል፡፡

ጥቁሩ - ግላኮማ

የዓይን ነርቭ፡- የዓይን ህዋሳት ከብርሀን ግድግዳ (ረቲና) ተሰባስበዉ ህብረ-ህዋስ ፈጥረዉ በኃለኛዉ የዓይን ክፍል ወደ አንጎል የሚጉሀዙበት ገመድ ነዉ፡፡ ስራዉም ብርሃንን እና ያየነዉን ምስል/እንቅስቃሴ በነርቭኛ ተርጉሞ ወደ እይታ-አንጎል ክፍል መማስተላላፍ ነዉ፡፡

ግላኮማ፡- የአይን ነርቭ መጎዳት ሲሆን ፤ የዓይናችን ነርቭ ጉዳት ለመገንዝብ ያህል በግላኮማ ምክንያት እና በሌላ ምክንያት ብለን መክፈል እንችላልን፡፡ ግላኮማ - በጊዜ ሂደት ጉዳቱ የሚጨምር ፣ የማይድን ግን የሚታከም የራሱ አይነተኛ አጎዳድ ያለዉ፤ የራሱ አይነተኛ የዓይን -አድማስ እክል የሚያምጣ ነዉ፡፡ ለግላኮማ አጋላጭ ከሆኑት ዉስጥ ዋናው ከፍተኛ የዓይን ግፊት (ከ 21 ሚሜ.ሜር በላይ) ሲሆን ፤ ነገር ግን የግድ ከፍተኛ ግፊት ላይኖር ይችላል፡፡

ብዙ አይነት ግላኮማ አለ… በመንስኤዉ - የሚታወቅ እና የማይታወቅ፣ በእድሜ - የህጻናት ፡ የወጣቶች እና የአዋቂዎቸ፤ በማዕዘኑ(የዓይን ፈሳሽ የሚፈስበት ቦይ)- ማዕዘነ ክፍት እና ማዕዘነ-ዝግ… ተብሎ በዋናነት ይከፍላል፡፡

የህጻናት ገላኮማ፡- ከ4 ዓመት በታች ያለዉን እድሜ ክልል የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ከሌላዉ ዕድሜ የሚለየው አልፎ አልፎ የሚከሰት መሆኑ፤ ሁሌም ክፍተኛ የዓይን ግፊት መኖሩ፣ ጉዳቱ የዓይን ነርቭ ላይ ብቻ ሳሆን ሁሉም እድገታቸዉን ያልጨረሱ የዓይን ክፍሎች ላይ መሆኑ፤ ጠቁሮ ያልጠቆረ…የሚታይ ምልክቶች ማለትም ሶስትዮሽ መገለጫ ያለዉ …ማንባት፡ ብርሃን መፍራት እና የዓይን ቆብን መጭመቅ፡፡ ህክማናዉም የዓይኑን ግፊት በቀዶ-ጥግና መቀነስ ነዉ፡፡ ጉዳቱ እንዳይቀጥል ማድረግ ነዉ ህክምናዉ….የደረሰዉ ተጎዳ አይምለስም፡፡

የወጣቶች እና አዋቂዎች ግላኮማ፡- እነዚህ በጥቁር የሚመሰሉት … ሲጀመሩ ምንም ምልክት የማያሳዩ፤ በጭለማ እንደሚዘርፍ ልባ … ከፍተኛ ጉዳት ካመጡ በኃላ ነዉ የሚታወቁት ምክንቱም የዓይን እይታን መጀመርያ ኣከባቢ ምንም አቀንሱም፡፡ የአይን አድማስ በከፍተኛ ሁኔታ ጠቦ ከነገሮች ጋር ስንጋጭ ወይም ዓይነ-ስዉርት ሲክስተ ነዉ የሚታወቀዉ… ይህ እንግዲህ በዓለም ከነጩ-ሞራ ግርዶሽ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ዓይን-ስዉርነትን ከሚያመጣዉ የማዕዘነ-ክፍት ግላኮማ አይነት መገለጫ ነዉ፡፡

ይህም ዕድሜያቸዉ ከ40 ዓመት በላይ ተጋላጭ ሲሆኑ….ዕድሜ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነትም ይጭምራል፡፡ ለዚህም ሲባል በዚህ ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያለ ሰዉ ቢያንስ አንዴ የዓይን ምርመራ ማድረግ ይመከራል፡፡ ተጨማሪ ተጋላጭነት ያላቸዉ ሰዎች ለምሳሌ የቅርብ ቤተሰብ አባል በግላኮማ የተጠቃ ካለ….የቅርብ ክትትል ያሰፈልጋቸዋል፡፡ ወደ ህክምናዉ ስንመጣ ብቸኛዉ ማከሚያዉ (የማይድን ነዉ ብለናል) መንገድ የዓይን ግፊቱን ካለበት መነሻ መቀነስ ነዉ፡፡ ይህም ጉዳቱን ባለበት ማቆም ወይም ዓይነ-ስውርነትን እንዳይከሰት ማቆየት ነው፡፡ ግፊቱን ካለበት ለማዉረድ ሶስት ዓይነት ህክመና አማራጮች አሉት….እናሱም የአይን ጠብታ፣ ጨረር እና ቀዶ-ህክምና ናቸዉ፡፡ #addisadmassnews

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
5.1K viewsedited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-25 09:25:52
ባንክ ለምን ይሰለፋሉ

ባለንበት ዘመን ትጋት ብቻ ሳይሆን ዘመናዊነትም ግድ ይላል! እናስ?

ለወዳጆዎ ከቤትዎ ሆነው በተቀላጠፈው ሞባይል ባንካችን *617# በመደወል ገንዘብ መላክና መለወጥ! የበረራ አየር ትኬት መቁረጥ! የሞባይል ካርድ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ፣ ሌሎችንም በርካታ አገልግሎቶችን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችል!

ድንገት ሳያስቡ ገንዘብ ጎሎ ተጨነቁ ፣ አያስቡ ኤቲኤማችን 24 ሰዓት ያለማቋረጥ አገልግሎት ይሰጣል!

ያለ ወለድ መቆጠብ እና ሌሎቹም!

የነበሩትን አሻሽለን፣ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን አካተን፣ ለአጠቃቀም ቀላል፣ ፍጥነት እና ምቾት ጨምረን፣ ከናንተ ወደ እናንተ ከተፍ!

እኛ ጋር የሌለው የለም ብቻ ነው!

ስራችን እንደ ንብ ትርፋችን እንደ ማር

የንብ ባንክ ትክክለኛ የቴሌግራም ትስስር ገጻችንን ይከታትሉ ሁሉንም መረጃ ያግኙ!

አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት መተግበሪያዎን ይጫኑ!!!

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!
5.6K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-24 14:34:40 Notcoin ያመለጣቹ May 30 የሚዘጋው የ Tap Swap  እድል እንዳያመልጣቹ አሁኑኑ ጀምሩ እንደቀልድ ስክሪናችንን tap በማድረግ ምናልባትም ጥሩ ክፍያ ልናገኝ እንችል ይሆናል May 30 ድረስ ብቻ ስለሆነ ሳይዘጋ ፍጠኑ ::

https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_812359129 +2.5k Shares as a first-time gift

https://t.me/tapswap_mirror_1_bot?start=r_812359129 +2.5k Shares as a first-time gift

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
7.9K viewsedited  11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-24 09:37:12
AI Teacher Robot in Kerala, India

AI መምህርት ሮቦት በኬረላ፣ ሕንድ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.1K viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-24 09:10:51
8.1K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-24 09:10:36 የዕጩ ዶክተሩ የመጨረሻ ማስታወሻ !!!

ሞት የማይቀር ዕዳ መሆኑን ባውቅም ቀጠሮ ተሰጥቶት ቀን ሲቆረጥ ግን ያስፈራል! ይገርማል! ሞት እንዲህ ያስፈራል ? በጣም ፈራሁ !መኖር ለካ እንዲ ያጓጓል ? በእውነት ጓጓሁ ! ፤ ልጆቼ አሳሱኝ! እንደ አዲስ ናፈቁኝ ! ትንሹ ወንድ ልጄ ! እህቶቹ ፤ ውዴ ፣ ጓደኞቼ ፣ዘመዶቼ ፣ የልጅነት አብሮ አደጎቼ ፤ባልደረቦቼ ፣የሀገሬ ልጆች ያደኩበት መንደር ሁሉም ናፈቁኝ ! እጣፈንታዬን ረገምኩት !

ወንድሞቼ ሆይ ዛሬ ጭላንጭል የመኖር ዕድል እና ዘላለማዊ እንቅልፍ በህይወቴ ተፋጠዋል ። ሁለት ምርጫ ይባል እንጂ ነገሩስ ምርጫ አይደለም ። ለአንድ ተራ አስተማሪ ሚሊዮን ብር ከፍሎ ህይወቱን ማዳን እንዴት ይቻለዋል ? ከፍቶኛል! ሆድ ብሶኛል ! ! ወንድማችሁ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነኝ ።

ግን ሀዘኔን ለማን ልስጥ ? ሰው ተቸግሯል ! የቸገረውን ሰውስ ምን ብዬ ላስቸገር ? ግን ነብስናትና ጨነቀኝ !! ያለኝን ሀብትና ንብረት በመሸጥ የኩላሊት እጠበት በሳምንት ሦስቴ እያደረኩ ከልጆቼ ጋር ያለኝን እድሜ ላማራዝምና ህይወቴን ለማቆየት ሞከርኩ ጣርኩ ! ወዳጆቼን ፣ ጓደኞቼን አስቸገርኩ ያው ትርፉ መከራን በቤተሰቤና ወዳጆቼ ላይ ማዝነብ ሆነ ፤ የእውነት !አሁን ደከመኝ ! አልቻልኩም ! የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልም ከንግዲህ በዲያሊስስ መቆየት አትችልም አቅሙ ካለህ ወደ ውጪ ሄደክ... አለኝ ። ወይ አቀም ! እቅሜና ተስፋዬ አምላኬና ወገኖቼ ብቻ ናቸው ። ዝም ካላችሁኝ በዝምታ አንቀላፋለሁ ከራራላችሁልኝ ደግሞ በእናንተ በኩል ይሰራል !

የሆነ ጊዜ ያነበብኩት አንድ የመቃብር ላይ ጽሁፍ ትዝ አለኝ ጽሁፉ " አሞኛል ብዬ ነግሪያችሁ ነበር " ይላል

ያው እኔም ቢቀለኝ ብዬ ነው የነገርኳችሁ ።

ወንድሞቼ ሆይ አሞኛል !

ከፉ ደዌ ከምወዳቸው ልጆቼ ሊለየኝ ነውና እርዳታችሁ ያስፈልገኛል ! በፍጹም ተስፋ አልቆርጥም ህይወቴ እስካለች ተስፋ አደርጋለሁ ግን
አ ሞ ኛ ል ቢሆንም ከህመሜ ድኜ ዶክትሬቴን ተቀብዬ ለምስጋና በዚሁ እመለስ ይሆናል !?

እሱ ካለ ?
ሀብት ንብረት የለኝም ያፈራሁት ሀብት ልጆቼ ተማሪዎቼ ብቻ ናቸው !
ወንድማችሁ እጩ ዶ/ር መ/ር አዲሱ ዳንኤል
ከአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ !
ስልክ+251916881107

አዲሱ ዳንኤል ሻሎ
የባንክ አካዉንት
1. ንግድ ባንክ
1000032842392
2. አቢስንያ ባንክ
S/A 5442672
3. ቡና ባንክ
1869501007218
7.8K viewsedited  06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ