Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_digital_library — Ethiopian Digital Library
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ebc
Bbc
Exit
Exitexam
Арада
Result
Raya
Rayauniversity
Futureready
Skillup
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_digital_library
ምድቦች: ስራ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 66.24K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-06-02 13:43:26 የአህያዋ ጆሮ #Just_for_fun

በአንድ ወቅት ከከብቶች ጋር የምትኖር አህያ ነበረች፡፡ ከከብቶቹም ጋር ትበላና ትተኛ ስለነበረ ቀንዶቻቸውን ስታይ ትቀናባቸው ጀመር፡፡

“ቀንዶች ቢኖሩኝ ጅቦችን እከላከልባቸው ነበር፡፡” ብላም አሰበች፡፡ “እናም ወደ ገጠር ወይም ወደ ሌሎች መንደሮች ሄጄ ቀንዶች የማገኝበትን መንገድ መፈለግ አለብኝ፡፡” ብላ በማሰብ ረጅም ጉዞ ላይ እንዳለች ጀርባው ላይ ትልቅ ሸክም ተሸክሞ ይጓዝ የነበረ ነጋዴ አገኘች፡፡

ነጋዴውም “አሃ! አምላክ በጣም ስላሰበልኝ ይህንን ከባድ ሸክም ሊያቀልልኝ ይህችን አህያ ላከልኝ፡፡” ብሎ በማሰብ ሸክሙን አህያዋ ላይ ጫነው፡፡ ሸክሙም ለአህያዋ ከባድ ቢሆንም አብረው ብዙ መንገድ ከተጓዙ በኋላ አህያዋ ማረፍ ስለፈለገች ቀስ ብላ መራመድ ጀመረች፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው በያዘው ዱላ ደጋግሞ ይመታት ጀመር፡፡ ሸክሙ አሁንም እንደከበዳት ነበርና በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስላልቻለች በመጨረሻ በጉልበቷ ተንበርክካ አልሄደም አለች፡፡ ነጋዴው ቢደበድባትም ተነስታ መራመድ አልቻለችም፡፡ በዚህ ጊዜ ነጋዴው አንደኛውን ጆሮዋን ቆረጠው፡፡ አሁንም በጣም ስለደከማት መንቀሳቀስ አቃታት፡፡

ከዚያም ነጋዴው ሸክሙን አውርዶላት አህያዋን እዚያው የተኛችበት ትቷት መንገዱን ቀጠለ፡፡ አህያዋም ሸክሙ ከወረደላት በኋላ ወደቀድሞው ቦታዋ ወደከብቶቹ ተመልሳ ስትሄድ የምትፈልገውን ቀንድ ለምን እንዳላገኘች ጠየቋት፡፡

“አይይ! እናንተ ቀንድ ስለማግኘቴ ነው የምታወሩት? እንኳን ቀንድ ላገኝ የነበረኝንም ጆሮ አጥቼ መጣሁ፡፡ ዋጋዬንም አግኝቻለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡

ከዚያን እለት በኋላ አጉል ምኞት ያላቸው ሰዎች “ቦታችሁን እወቁ፡፡ ካለበለዚያ ቀንድ እፈልግ ብላ ጆሮዋን እንዳጣችው አህያ እንዳትሆኑ፡፡” እየተባባሉ ይመከሩ ጀመር ይባላል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.5K viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-02 09:48:05 የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ

የትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ(online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ መጀመሩን ገልጿል፡፡

ይህንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡

ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ስለሆነም ተፈታኞች ከዚህ በታች በሚፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ክላስተር አንድ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር፡ https://c2.exam.et 
ሲዳማ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et
ትግራይ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et

ክላስተር ሁለት
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et
ጋምቤላ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et
አማራ ብሄራዊ ክልል፡ https://c3.exam.et

ክላስተር ሶስት

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
ሀረሪ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
አፋር ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 1
• አዳማ ከተማ: https://c4.exam.et
• አጋሮ ከተማ: https://c4.exam.et
• አምቦ ከተማ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ አርሲ: https://c4.exam.et
• ምዕራብ አርሲ: https://c4.exam.et
• አሰላ ከተማ: https://c4.exam.et
• ባሌ: https://c4.exam.et
• ባቱ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቤሾፍቱ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቦረና: https://c4.exam.et
• ቡሌ ሆራ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቡኖ በደሌ: https://c4.exam.et
• ዶዶላ ከተማ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ባሌ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ቦረና: https://c4.exam.et
• ጉጂ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ሐረርጌ: https://c4.exam.et
• ምዕራብ ሐረርጌ: https://c4.exam.et
• ሆለታ ከተማ: https://c4.exam.et
• ሆሮ ጉዱሩ: https://c4.exam.et
• ኢሉባቦር: https://c4.exam.et

ክላስተር አራት
ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2
• ጅማ: https://c5.exam.et
• ጅማ ከተማ: https://c5.exam.et
• ቄለም ወለጋ: https://c5.exam.et
• ማያ ከተማ: https://c5.exam.et
• መቱ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሞጆ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሞያሌ ከተማ: https://c5.exam.et
• ነጆ ከተማ: https://c5.exam.et
• ነቀምት ከተማ: https://c5.exam.et
• ሮቤ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et
• ሰንዳፋ በኬ: https://c5.exam.et
• ሻኪሶ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሻሸመኔ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሸገር ከተማ: https://c5.exam.et
• ሸኖ ከተማ: https://c5.exam.et
• ምስራቅ ሸዋ: https://c5.exam.et
• ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ): https://c5.exam.et
• ደቡብ ምዕራብ ሸዋ: https://c5.exam.et
• መዕራብ ሸዋ፡ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ወለጋ፡ https://c5.exam.et
• መዕራብ ወለጋ፡ https://c5.exam.et
• መዕራብ ጉጂ፡ https://c5.exam.et
• ወሊሶ ከተማ፡ https://c5.exam.et

ትምህርት ሚኒስቴር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.6K viewsedited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 17:51:53
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀም!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
17.8K viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-28 10:52:08 መንግሥት ዝቅተኛ የሠራተኞችን የደመወዝ ወለል እንዲወስን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) እና የአሠሪዎች ፌደሬሽን ባካሄዱት ጉባዔ ላይ በድጋሚ ተጠይቋል

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌደሬሽን፣ መንግሥት የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን ድጋፉን እንደሰጠ ኢሠማኮ ባሠራጨው መረጃ ገልጧል።

አውሮፓ ኅብረት በቅርቡ እተገብረዋለሁ ያለው ወደ አውሮፓ ገበያ የሚገቡ ምርቶች የአመራረት ሂደታቸው ሰብዓዊ መብቶችንና የዲሞክራሲ እሴቶችን ያከበረ እንዲኾን በሚጠይቀው መመሪያ፣ አሠሪዎች ዝቅተኛ የሠራተኞች ደመወዝ ወለል መወሰን እንዳለባቸው መደንገጉን ኢሠማኮ ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌደሬሽን፣ ላኪዎች ወደፊት ምርታቸውን ያለ ስጋት ወደ አውሮፓ ኅብረት ገበያ እንዲልኩ መንግሥት የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ቀድሞ መወሰን እንዳለበት አሳስቧል ተብሏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
7.9K viewsedited  07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-28 09:55:04
የዓለማችን ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች

ዓለም አቀፉ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ መዳቢ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት ምርጥ 2 ሺህ ዩንቨርሲቲዎችን ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ምርጥ 1ኛ ዩንቨርሲቲ ሲባል ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ተብለዋል፡፡

ከአፍሪካ ከአንድ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ሲቆጣጠሩ ኬፕታወን ዩኒቨርሲቲ፣ ዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ እና ስቴለንስቦስች ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ከዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሲሆን አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ባህርዳር እ ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ተካተዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ841ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ1701ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በ1748ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ግብጽ 20 ዩኒቨርሲቲዎቿ በዓለማችን ምርጥ 2 ሺህ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሲካተቱ ናይጀሪያ 5፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዩኒቨርሲቲዎችን ያስመረጡ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ናቸው፡፡

ማዕከሉ የዩኒቨርሲቲዎቹን ደረጃ ያወጣው ዩኒቨርሲቲዎች በሚያካሂዷቸው ጥናት እና ምርምሮች፣ ትምህርት አሰጣጥ ጥራት፣ የፋኩልቲ አወቃቀሮች እና የሰው ሀይል ጥራት ዋነኛ መስፈርቶች ናቸው፡፡ #ALAIN

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
7.7K viewsedited  06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-27 19:20:58
በነፃ ዱባይ ሄደው መዝናናት ይፈልጋሉ?

ቀላል ነው! ከግንቦት 7- ሰኔ 7 የYangoን መተግበሪያ ከAppstroe ወይም Playstore አውርደው፣ የመጀመሪያ ጉዞዎን ያድርጉ።

አሸናፊው በዕጣ ይመረጣል፤ ውድድሩ እንደተጠናቀቀ አሸናፊውን እናሳውቃለን። መልካም ዕድል!
8.7K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-27 17:49:19
መረጃ አይናቅም

ህንድ ቻይናን በህዝብ ብዛት እንደቀደመቻት ስንቶቻቸሁ ታውቃላችሁ?

1. ህንድ
2. ቻይና
3. USA
.
.
.
11. Ethiopia

Source: www.statista.com

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.8K viewsedited  14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-27 15:18:48 የሎተሪ ቲኬቱ #Just_for_fun

ከረጅም ጊዜ በፊት በጣም ደሃ የነበሩ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ብዙ ችግሮችንም በጋራ በመጋፈጥ አብረው አደጉ፡፡ በርግጥ አብዛኛውን ጊዜአቸውን የሚያጠፉት እንጨት በመልቀም ነበር፡፡ ትንሽ ገንዘብ ሲያገኙ ለምግባቸው ብቻ ስለሚያውሉት ህይወት ለእነርሱ በጣም ከባድ ነበረች፡፡

ታዲያ አንድ ቀን አንደኛው “እንደዚህ አይነት ተስፋ ቢስ ኑሮን እስከ መቼ ነው የምንገፋው? ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት ተርበን ሎተሪ እንግዛ፡፡ ትልቁን እጣ እናሸንፍ ይሆናል፡፡” አለ፡፡

ጓደኛውም “አይሆንም እኔ መራብ አልፈልግም፡፡ ድርሻዬን እበላለሁ፡፡” አለ፡፡
እናም አንደኛው ጓደኛ ተርቦ ቲኬት ገዛ፡፡ ምግቡን የወሰደው ጓደኛ ግን “ቲኬቱን እኔ ልቁረጥልህ” ብሎ ቆረጠለት፡፡

ዕጣው የሚወጣበት ቀን ሲደርስ ያቺ ቲኬት የትልቁ ሽልማት አሸናፊ ሆነች፡፡

ቲኬቱን የገዛው ጓደኛም እጣው ስለወጣለት በጣም በመደሰት ወደ ጓደኛው እየሮጠ ሲሄድ ጓደኛው ገንዘቡን ተቀብሎ ስለነበር “ማንነትህን እንኳን አላውቀውም፡፡ የማላውቅህ ሰው ነህ፡፡” ብሎ አባረረው፡፡

ከዚያ በገንዘቡ ትልቅ ቪላ ቤትና መኪና ገዝቶ ሚስት አገባ፡፡ ሌላኛው ጓደኛ ግን ወደ ድሮው ህይወቱ ተመልሶ እንጨት በመልቀም ወደ ገበያ ወስዶ መሸጡን ቀጠለ፡፡

አንድ ቀን ታዲያ የሃብታሙ ሰው ሚስት ድሃውን ጓደኛ ገበያ ቦታ አየችው፡፡ የባሏ ጓደኛም እንደነበረ ስለምታውቅ እቃዋን ተሸክሞ ቤት እንዲያደርስላት ሰጠችው፡፡ ከቤት ሲደርሱም ወደ ቤት አስገብታ ምግብ ሰጠችው፡፡ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ሁልጊዜ እቃዋን ከገበያ ተሸክሞ እንዲያደርስላት በማድረግ ምግብ ትሰጠው ጀመር፡፡ ስለየራሳቸው ማውራትም ጀመሩ፡፡ እርሱም ስላለፈው ሁሉ እያነሳ ባሏ እንዴት እንደካደው ነገራት፡፡

ሚስትየውም በጣም ስለተበሳጨች ሳጥኑ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በሙሉ አውጥታ ከሰጠችው በኋላ “ይህ ያንተ ገንዘብ ነው፡፡” አለችው፡፡ ባሏም ተመልሶ በመጣ ጊዜ ገንዘቡን ከቦታው ስላጣው በጣም ተናደደ፡፡ ሚስቱም “ምናልባት ሌባ መጥቶ ሰርቆት ይሆናል::” አለችው፡፡ ሆኖም በጣም ተበሳጭቶ ስለነበረ ሚስቱን ከቤት አባሮ ቤቱን አቃጠለው፡፡

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ንብረቱን እየሸጠ ደሃ እየሆነ ሄደ፡፡ ከዚያም አንድ ቀን በመንገድ እየሄደ ሳለ ጓደኛውን አገኘው፡፡ ጓደኛውም በጣም ሃብታም ሆኗል የሚል ወሬም ሰምቶ ነበርና ጓደኛውን “በጣም ሃብታም ሆነሃል አሉ፡፡ ወደቤትህ መጥቼ ለምን አልጠይቅህም?” አለው፡፡

ጓደኛውም “እሺ” ብሎ ጥሩ ቤቱን መኪናውንና ሃብቱን ካሳየው በኋላ “አሁን ያለኝን ነገር ሁሉ አይተሃል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን አንተን ላይህ አልፈልግም፡፡” አለው፡፡

የአገር ሽማግሌዎችም ጠርቶ “ይህ ሰው ከረጅም ጊዜ በፊት አታሎኝ ሲያበቃ በድህነት ዘመኔ ያልጠየቀኝ አሁን ሃብታም መሆኔን ሲያይ መጥቶ ሊጎበኘኝ ይፈልጋልና እናንተ ያገር ሽማግሌዎች ሁለተኛ ወደቤቴ እንዳይመጣ ከልክሉልኝ፡፡” አላቸው፡፡

ሽማግሌዎቹም ታሪኩን ሰምተው ሰውየው በሎተሪ ቲኬቱ የተታለለ መሆኑን በመረዳት ሁለቱ ጓደኛማቾች ሁለተኛ እንዳይተያዩ በሚል ፍርዳቸውን ሰጡ ይባላል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.3K viewsedited  12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-27 14:06:51
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር አሸነፉ

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሦስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡድኖች ጋር ተጋርተዋል።

ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሦስት የውድድር ትራኮች ተከፋፍሎ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡በውድድሩ ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስቴሩ የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎውን በማሳደግ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ÷ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.4K viewsedited  11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-26 18:29:13 የ2016 ዓ.ም ክረምት ትምህርት ፕሮግራም ጉዳይ

በ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ፕሮግራም እንደማይኖር ባለፈው አመት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆ ነበር። ሚኒስቴሩ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ፤ የ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ፕሮግራም እንደማይኖር ገልጾ ነበር ።

"በተለያዩ ምክንያቶች ባለፉት ዓመታት የተዛነፈውን የትምህርት ካሌንደር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማስተካከል እየሠራ እንደሚገኝ" ሚኒስቴሩ ባለፈው አመት አስታውሷል፡፡ ነገር ግን የ 2016 ዓ.ም ክረምት ትምህርት ፕሮግራም መኖር አለመኖሩ እስካሁን አልታወቀም!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
10.3K viewsedited  15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ