Get Mystery Box with random crypto!

Dire Dawa Ketema Sport Club

የቴሌግራም ቻናል አርማ diredawaketemasportclub — Dire Dawa Ketema Sport Club D
የቴሌግራም ቻናል አርማ diredawaketemasportclub — Dire Dawa Ketema Sport Club
የሰርጥ አድራሻ: @diredawaketemasportclub
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 372

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-18 22:14:12
#እግር_ኳስን_ከትምህርት_ቤቶች_እስከ_ሀገሪቱ_ትልቁ_ሊግ_ድረስ_በማስተሳሰር_ተተኪ_ስፖርተኞችና_ባለሙያዎች_እንዲወጡ_ጠንክሬ_እሰራለሁ!"
196 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:13:55
#ሀገሬ_ኢትዮጲያ_ወደ_መሰረተችው_የአፍሪካ_እግር_ኳስ_ማህበር_አመራርነት_እንድትመለስ_ጠንክሬ_እሰራለሁ!"
169 views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:13:24
#የሀገራችን_ስታዲዮሞች_ዘመናዊ_ስታንዳርዳቸውን_እንዲጠብቁ_በማስቻል_ብሔራዊ__ድናችንን_ከስደት_እታደጋለሁ!!"

ነሃሴ 22/2014 ዓ.ም በታሪካዊቷ ጎንደር ለሚካሄደው የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 3 የመጨረሻ እጩዎች ይፋ መሆናቸው ሰሞኑን ታውቋል!
በዚህ ምርጫ ከፍተኛ የማሸነፍ እድል እንዳለው እየተነገረ የሚገኘው የክለባችን ዋነኛ ስፖንሰር አድራጊና የኤልኔት ቢዝነስ ግሩፕ መስራችና ፕሬዝዳንት ወጣቱ ቶኪቻ አለማየሁ ከተማ ነው!

ቶኪ እንደ CAF ፕሬዝዳንቱ ፓትሪስ ሞትሴፔ፣እንደ CONMEBOLሉ አሊሃንድሮ ዶምኒጌዝ፣እንደ CONCACAF ዞኑ ቪክቶር ሞንታግሊያኒ እና እንደ Asian እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሰልማን ቢን ኢብራሂም አል ከሊፋ በስራ ፈጠራ ስኬት ከፍተኛ የሃብት መጠን ላይ በመድረስ ወደ እግር ኳሱ እየመጣ ያለ ወጣት ነው!

፦ቶኪን መምረጥ እግር ኳስን መምረጥ ነው!
፦ቶኪን መምረጥ ትኩስ ሀይልን መምረጥ ነው!
፦ቶኪን መምረጥ ስኬትን መምረጥ ነው!
፦ቶኪን መምረጥ ድሬደዋዊነትንና ኢትዮጲያዊነትን መምረጥ ነው!!

መልካም እድል ለቶኪቻ አለማየሁ ከተማ!!
የድሬደዋ ከተማ ስፖርት ክለብ!!
158 views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:04:00
ቡድናችን የ2015 ውድድር ዘመን ዝግጅቱን ሐሙስ ነሃሴ 5/2014 ዓ.ም መዘገባችን ይታወሳል ቡድኑ ከአርብ ነሃሴ 6/2014 ጀምሮ የህክምና ምርመራ ካደረገ ቡኃላ ቀጥታ ወደ ዝግጅት ስለሚገባ ሁሉም ተጫዋቾች በእለቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ክለባችን አሳውቀዋል።
104 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 16:18:16
#የድሬዳዋ_ከተማ_ዋና_ቡድን_ዝግጅት_የሚጀምርበትን_ቀን_አሳወቀ።
ዮርዳኖስ አባይን አሰልጣኝ አድርጎ ወደ ተጫዋቾች ምልመላ የገባው ድሬዳዋ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምርበትን ቀን አሳወቀ።
ቡድኑ ቅድመ ዝግጅቱን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመር ቀደም ብሎ ወደ ስፍራው አምርቶ የነበረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አመራር ጥሩ አቀባበል ለክለቡ በማድረግ ጥሩ አቀባበል ሊያደርግላቸው ችሏል።
ቡድኑ ዝግጅቱን ሐሙስ የሚጀምር ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች የፊታችን ሐሙስ ነሃሴ 5 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት በኪሊዮፓትራ ሆቴል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳውቋል።

የክለቡ አመራሮች የዝግጅት ስፍራ ምልከታ እና ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሲወያዩ የሚያሳይ በፎቶ ከስር ተለቋል።
86 viewsedited  13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 16:18:15
83 views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:24:49
#ድሬዳዋ_ከተማ_ሶስት_ወጣቶችን_ፕሮፌሽናል_ኮንትራት_አስፈረመ

ባለፉት አመታት ከተስፋ ቡድን ወደ ዋና ቡድን በማደግ በልዩልዩ ኮንትራት ቡድኑን ሲያገለግሉ የነበሩት ሁለት የመሀል ተጫዋቾች እና አንድ ግብ ጠባቂ ፕሮፌሽናል ኮንትራት በመፈረም ዋናውን ቡድን መቀላቀል ችሏል፡፡

ኮንትራታቸውን ካደሱ ተጫዋቾች አንዱ ከኢትዮጵያ ወጣቶችና አካዳሚ ወደ ተስፋ ቡድን በመቀላቀል ሲጫወት የነበረው ወንደሰን ደረጀ (ኦቾ) ሲሆን ወንደሰን ባለፉት ሁለት አመታት ከዋናው ቡድን ጋር በመስራት ልምድ የቀሰመ ሲሆን ወንደሰን ቡድናችን ዘንድሮ ለማሰልጠን በተሾመው ዮርዳኖስ አባይ ሊመረጥ ችሏል፡፡
የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ወንደሰን ለቀጣይ ሁለት አመት ድሬ ከተማን ለማገልገል በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑረዋል፡፡

ሌላው ፈራሚ ቁመተ ለግላጋው አብዱልፈተህ አሊ ፖግባ ሲሆን ፖግባ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ሜዳ ውስጥ በቆየባቸው ደቂቃዎች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በማድረጉ ተጫዋቹ ቀጣይ ዋናውን ቡድን በሁለት አመት ኮንትራት ለማገለገል ተስማምቷል፡፡ ፖግባ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥም በጥሩ ሁኔታ ሊያገለግል የቻለ ተጫዋች ነው፡፡

በሶስተኝነት ወደ ዋና ቡድን የተቀላቀለው ወጣቱ ግብጠባቂ አብዩ ካሳዬ ሲሆን አብዩ ዘንድሮ ድሬዳዋ ላይ በተካሄደው ውድድር ዋናው ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁን በቀይ ካርድ ሲወጣ ተቀይሮ በመግባት ጥሩ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ወጣቱ ግብ ጠባቂ በቀጣይ ከፍሬው እና ዳንኤል ጋር ተፎካካሪ ሆኖ እንዲጫወት ቡድኑ በሁለት አመት ኮንትራት ተጫዋቹን አስፈርሟል፡፡
73 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 17:02:57
የ2015 የዝውውር ሂደት አስመልክቶ ከአዲሱ የክለባችን አሰልጣኝ ዮርካኖስ አባይ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በሚከተለው መልኩ አቅርበናል ተከታተሉ፡፡
ለተፈጠረው የድምጽ ጥራት ይቅርታ እንጠይቃለን
101 views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 16:04:32
አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ በታዳጊ ቡድን ወርዶ እንዲሰሩ ተወሰነ
አሰልጣኝ ዘማሪያም አምና በሁለተኛ አጋማሽ ላይ ክለባችን የተቀላቀለ ሲሆን በወቀቱ ቡድኑን በሊጉ እንዲያቆይ የተሰጠውን ተልዕኮ በማሳካቱ ክለቡ አሰልጣኙን ለሁለት አመት አስፈርሞ ቡድኑን እንዲገነባ የሚፈልጋቸውን ተጫዋቾች እንዲያስፈርም ሙሉ መብት ተሰጥቶት ወደ ዝውውር ገበያ በመግባት ክለቡ ያስቀመጠለትን እቅድ ባለማሳካቱ ክለቡ ከሀዋሳ ጨወታ መልስ ባደረገው ግምገማ አሰልጣኙ ከዉጤት ባሻገር በተለያዩ ጉዳዮች ተጠርጥረው ጉዳዩ በህግ እስኪጣራ አሰልጣኙ ከስራቸው እንዲታገድ ማድረጉ ይታወሳል ፡ ይሁንና ክለቡ በዛሬው ዕለት የተጀመረው የህግ ማጣረት እስከጠናቀቅ የአሰልጣኙን እግድ በማንሳት አሰልጣኙ በታዳጊ ቡድን እንዲሰራ ወስኗል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ ታዳጊ ቡድን ጎንደር በሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ቡድኑ የካቲት 12 ለሚጀመረው ዉድድር በቅርቡ ወደ ዉድድር ስፍራ የሚያመራ ሲሆን አሰልጣኝ ዘማሪያምም ካሉት ሁለት አሰልጣኞች ጋር በመሆን ዉጤታማ የውድድር ጊዜ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
641 views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 07:36:01 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 10ኛ ሳምንት በድሬደዋ፨

የ1ዐኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 በድሬደዋ ስታዲየም ከጥር 2ዐ እስከ ጥር 23/2014 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ሰባት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ 19 ግቦች በ17 ተጫዋቾች ተመዝግበዋል። 3ዐ በቢጫ ካርድ የተገሰፁ ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች ሲሆኑ የታየ ቀይ ካርድ የለም። ውጤት ማፅደቅን ተከትሎ ከፀጥታውም ሆነ ከዳኝነት አንፃር ውጤታማ ሳምንት መሆኑ በሊጉ ውድድርና ስነስርዓት ኮሜቴ ዛሬ ተገምግሟል።

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች፨ በሳምንቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 24 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል። በተጫዋቾች ፍሬዘር ካሳ(ሀዲያ ሆሳዕና) ፣ አናጋው ባደግ(ወላይታ ድቻ) እና ዊሊያም ሰለሞን(ኢትዮጵያ ቡና) 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክተዋል። በመሆኑም ተጫዋቾቹ እያንዳንዳቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ. እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 150ዐ /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል። በክለብ ደረጃ ጅማ አባ ጅፋር እግርኳስ ክለብ ክለቡ እሁድ ጥር 22 2014 ዓ ም ከአበባ ከተማ ባደረገው የ1ዐ ኛ ሳምንት መርሃግብር ጨዋታው 5/አምስት/ ደቂቃ ዘግይቶ አንዲጀመር ምክንያት ስለመሆኑ ከጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ስለቀረበበት ክለቡ ለፈፀመው ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 15,00ዐ /አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

የኮቪድ የምርመራ ውጤት፨ በአንድ ማዕከል የኮቪድ ምርመራ ለተጫዋቾች፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ዳኞች ተደርጓል። በሳምንቱ አጠቃላይ 561 ምርመራ ተደርጎ የተገኘ ፓዘቲቨ ውጤት የለም፡፡
ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር
610 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ