Get Mystery Box with random crypto!

#የሀገራችን_ስታዲዮሞች_ዘመናዊ_ስታንዳርዳቸውን_እንዲጠብቁ_በማስቻል_ብሔራዊ__ድናችንን_ከስደት_እታ | Dire Dawa Ketema Sport Club

#የሀገራችን_ስታዲዮሞች_ዘመናዊ_ስታንዳርዳቸውን_እንዲጠብቁ_በማስቻል_ብሔራዊ__ድናችንን_ከስደት_እታደጋለሁ!!"

ነሃሴ 22/2014 ዓ.ም በታሪካዊቷ ጎንደር ለሚካሄደው የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 3 የመጨረሻ እጩዎች ይፋ መሆናቸው ሰሞኑን ታውቋል!
በዚህ ምርጫ ከፍተኛ የማሸነፍ እድል እንዳለው እየተነገረ የሚገኘው የክለባችን ዋነኛ ስፖንሰር አድራጊና የኤልኔት ቢዝነስ ግሩፕ መስራችና ፕሬዝዳንት ወጣቱ ቶኪቻ አለማየሁ ከተማ ነው!

ቶኪ እንደ CAF ፕሬዝዳንቱ ፓትሪስ ሞትሴፔ፣እንደ CONMEBOLሉ አሊሃንድሮ ዶምኒጌዝ፣እንደ CONCACAF ዞኑ ቪክቶር ሞንታግሊያኒ እና እንደ Asian እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሰልማን ቢን ኢብራሂም አል ከሊፋ በስራ ፈጠራ ስኬት ከፍተኛ የሃብት መጠን ላይ በመድረስ ወደ እግር ኳሱ እየመጣ ያለ ወጣት ነው!

፦ቶኪን መምረጥ እግር ኳስን መምረጥ ነው!
፦ቶኪን መምረጥ ትኩስ ሀይልን መምረጥ ነው!
፦ቶኪን መምረጥ ስኬትን መምረጥ ነው!
፦ቶኪን መምረጥ ድሬደዋዊነትንና ኢትዮጲያዊነትን መምረጥ ነው!!

መልካም እድል ለቶኪቻ አለማየሁ ከተማ!!
የድሬደዋ ከተማ ስፖርት ክለብ!!