Get Mystery Box with random crypto!

#ድሬዳዋ_ከተማ_ሶስት_ወጣቶችን_ፕሮፌሽናል_ኮንትራት_አስፈረመ ባለፉት አመታት ከተስፋ ቡድን ወደ | Dire Dawa Ketema Sport Club

#ድሬዳዋ_ከተማ_ሶስት_ወጣቶችን_ፕሮፌሽናል_ኮንትራት_አስፈረመ

ባለፉት አመታት ከተስፋ ቡድን ወደ ዋና ቡድን በማደግ በልዩልዩ ኮንትራት ቡድኑን ሲያገለግሉ የነበሩት ሁለት የመሀል ተጫዋቾች እና አንድ ግብ ጠባቂ ፕሮፌሽናል ኮንትራት በመፈረም ዋናውን ቡድን መቀላቀል ችሏል፡፡

ኮንትራታቸውን ካደሱ ተጫዋቾች አንዱ ከኢትዮጵያ ወጣቶችና አካዳሚ ወደ ተስፋ ቡድን በመቀላቀል ሲጫወት የነበረው ወንደሰን ደረጀ (ኦቾ) ሲሆን ወንደሰን ባለፉት ሁለት አመታት ከዋናው ቡድን ጋር በመስራት ልምድ የቀሰመ ሲሆን ወንደሰን ቡድናችን ዘንድሮ ለማሰልጠን በተሾመው ዮርዳኖስ አባይ ሊመረጥ ችሏል፡፡
የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ወንደሰን ለቀጣይ ሁለት አመት ድሬ ከተማን ለማገልገል በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑረዋል፡፡

ሌላው ፈራሚ ቁመተ ለግላጋው አብዱልፈተህ አሊ ፖግባ ሲሆን ፖግባ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ሜዳ ውስጥ በቆየባቸው ደቂቃዎች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በማድረጉ ተጫዋቹ ቀጣይ ዋናውን ቡድን በሁለት አመት ኮንትራት ለማገለገል ተስማምቷል፡፡ ፖግባ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥም በጥሩ ሁኔታ ሊያገለግል የቻለ ተጫዋች ነው፡፡

በሶስተኝነት ወደ ዋና ቡድን የተቀላቀለው ወጣቱ ግብጠባቂ አብዩ ካሳዬ ሲሆን አብዩ ዘንድሮ ድሬዳዋ ላይ በተካሄደው ውድድር ዋናው ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁን በቀይ ካርድ ሲወጣ ተቀይሮ በመግባት ጥሩ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ወጣቱ ግብ ጠባቂ በቀጣይ ከፍሬው እና ዳንኤል ጋር ተፎካካሪ ሆኖ እንዲጫወት ቡድኑ በሁለት አመት ኮንትራት ተጫዋቹን አስፈርሟል፡፡