Get Mystery Box with random crypto!

አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ በታዳጊ ቡድን ወርዶ እንዲሰሩ ተወሰነ አሰልጣኝ ዘማሪያም አምና በሁ | Dire Dawa Ketema Sport Club

አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ በታዳጊ ቡድን ወርዶ እንዲሰሩ ተወሰነ
አሰልጣኝ ዘማሪያም አምና በሁለተኛ አጋማሽ ላይ ክለባችን የተቀላቀለ ሲሆን በወቀቱ ቡድኑን በሊጉ እንዲያቆይ የተሰጠውን ተልዕኮ በማሳካቱ ክለቡ አሰልጣኙን ለሁለት አመት አስፈርሞ ቡድኑን እንዲገነባ የሚፈልጋቸውን ተጫዋቾች እንዲያስፈርም ሙሉ መብት ተሰጥቶት ወደ ዝውውር ገበያ በመግባት ክለቡ ያስቀመጠለትን እቅድ ባለማሳካቱ ክለቡ ከሀዋሳ ጨወታ መልስ ባደረገው ግምገማ አሰልጣኙ ከዉጤት ባሻገር በተለያዩ ጉዳዮች ተጠርጥረው ጉዳዩ በህግ እስኪጣራ አሰልጣኙ ከስራቸው እንዲታገድ ማድረጉ ይታወሳል ፡ ይሁንና ክለቡ በዛሬው ዕለት የተጀመረው የህግ ማጣረት እስከጠናቀቅ የአሰልጣኙን እግድ በማንሳት አሰልጣኙ በታዳጊ ቡድን እንዲሰራ ወስኗል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ ታዳጊ ቡድን ጎንደር በሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ቡድኑ የካቲት 12 ለሚጀመረው ዉድድር በቅርቡ ወደ ዉድድር ስፍራ የሚያመራ ሲሆን አሰልጣኝ ዘማሪያምም ካሉት ሁለት አሰልጣኞች ጋር በመሆን ዉጤታማ የውድድር ጊዜ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡