Get Mystery Box with random crypto!

#የድሬዳዋ_ከተማ_ዋና_ቡድን_ዝግጅት_የሚጀምርበትን_ቀን_አሳወቀ። ዮርዳኖስ አባይን አሰልጣኝ አድርጎ | Dire Dawa Ketema Sport Club

#የድሬዳዋ_ከተማ_ዋና_ቡድን_ዝግጅት_የሚጀምርበትን_ቀን_አሳወቀ።
ዮርዳኖስ አባይን አሰልጣኝ አድርጎ ወደ ተጫዋቾች ምልመላ የገባው ድሬዳዋ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምርበትን ቀን አሳወቀ።
ቡድኑ ቅድመ ዝግጅቱን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመር ቀደም ብሎ ወደ ስፍራው አምርቶ የነበረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አመራር ጥሩ አቀባበል ለክለቡ በማድረግ ጥሩ አቀባበል ሊያደርግላቸው ችሏል።
ቡድኑ ዝግጅቱን ሐሙስ የሚጀምር ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች የፊታችን ሐሙስ ነሃሴ 5 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት በኪሊዮፓትራ ሆቴል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳውቋል።

የክለቡ አመራሮች የዝግጅት ስፍራ ምልከታ እና ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሲወያዩ የሚያሳይ በፎቶ ከስር ተለቋል።