Get Mystery Box with random crypto!

Emir consult

የቴሌግራም ቻናል አርማ consult_emir — Emir consult E
የቴሌግራም ቻናል አርማ consult_emir — Emir consult
የሰርጥ አድራሻ: @consult_emir
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-25 15:50:01 ማወቅ የማይጠበቅብንን ወይም የማይጠቅመንን ነገር ማወቅ በራሱ አንዱ አለማወቅ ነው፡፡

https://t.me/consult_emir
82 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 09:14:54 በመልካምነት አሸንፍ !

በተቻለህ አቅም ሁሉ ለሰዎች መልካም ሁን ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ አታውቅም እና አትክፋባቸው!
ክፋ ለመሆን የተፈጠረ ሰው የለም ሁኔታዎች ግን ሰዎችን ይቀያይሯቸዋል ! የእኛ ጥሩ መሆን ግን በእነዚያ ሰዎች ህይወት ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም !
ስለዚህ በተገኘህበት ቦታ ሁሉ የጥሩነት ምሳሌ ሁን ፤ ሁኔታዎች አይገድቡህ የበላያቸው ሆነህ አስደንግጣቸው !

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
83 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 21:19:29 «ህይወት 3 ቀን ናት ትላንት ዛሬ እና ነገ ከትናንት ተማሩ ዛሬን ኑሩ ነገን አቅዱ!!!»ሁሌ ከአንደበታችን መልካም ነገር ይውጣ መልካምነት ለራስ ነው

#ደስ_ምሽት_ይሁንላችሁ

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
84 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 21:13:50 ደስ የሚል በቀል!

እልህ ይዞህ ያውቃል? የሚንቁህና የበታችነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሰዎች ህይወትህን የቀን ጨለማ አድርገውት ያውቃሉ አይደል?

እሳትን ስትፈልግ ንብረት ለማውደም ትጠቀምበታለህ ስትፈልግ ደግሞ ምግብ ታበስልበታለህ፤ ታዲያ ለናቁህ ሰዎች ማንነትህን ለማሳየት ጠንክረህ ሰርተህ ራስህን ለውጠህ በስኬትህ የያዘህን እልህ ለምን አትወጣም?! የምድራችን ጣፋጭ በቀል በናቁህ ፊት የሚያስከብር ስኬት መጎናፀፍ ነው!

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
80 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 16:59:58 እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል" የሚባል አባባል አለ፤ መጀመሪያ ራስህን አድን፣ ራስህ ላይ አተኩር! እንዲህ ባደርግ ሰዎች ይደሰቱብኛል ማለቱን ተወውና 'እኔን ደስተኛ የሚያደርገኝ ምን ባደርግ ነው?' በል።

አንተ ደስተኛ ስትሆን አለም አብራህ ትስቃለች፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ አየህ ራስህ ላይ ስታተኩር ሰዎች ደግሞ አንተ ላይ ማተኮራቸው ግድ ነው። ወዳጄ ደስ የሚለው ነገር አንተ ለራስህ ደስታ አታንስም!

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
78 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 16:56:17 #poem

የተመረኮዙት ልብ ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
78 views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 07:11:54 #ውሳኔ

በሕይወትህ ፈልገህ ፈጣሪህን የጠየከው ነገር እስካሁን ያልተሰጠህ፤ እስካሁን ያልተመለሰልህ፤ እስካሁን ያልተሳካልህ፤ ሕይወትህን ለመቀየርና ሕልምህን እውን ለማድረግ በጠንካራ ውሳኔ ስላልፀናህ ነው፤ ከውስጥህ ጋር ያለውን ክርክርና ግጭት ገና አልፈታህም አዕምሮህን ዕረፍት የውስጥህን ሰላም በመጠበቅ የምትፈልገውን ስትወስንና እንደሚቻል ስታምን ሁሉም ነገር ይሳካል፤ ሁሌም ቢሆን አንድን ነገር ለማሳካት እዛ ሳልደርስ እንዴት እወስናለሁ አትበል፤ መጀመሪያ ወስንና ለማሳካት ስትነሳ ትደርስበታለህ፤ የስኬትህ ትልቁ መንገድ ውሳኔህ ነው።

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
90 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 23:04:47 ልማድ !

አላማ አንተ ውስጥ መሰራት የሚጀምረው ለዚያ አላማ ማስፈፀሚያ የሚሆን ጀግና ሰው ሆነህ መገኘት ስትችል ነው ይሄን ጀግና ሰው የሚፈጥረው ደግሞ የየእለት ልማድ ነው!

"ልማድ ሲሰለጥን ተፈጥሮ ይሆናል "ይለናል ቮልቴር የምንፈልገውን ማንነት ራሳችን ላይ ለመገንባንት እያንዳንዷ የየዕለት ልማዳችን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላት ! ስለዚህ ልማድሽ ላይ አጥብቀሽ ስሪ!

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
92 views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:14:01 #የደስታ_ሚስጥር
#ደስታ

እኔ የምፈልገውን መኪና፤ ቤት፤ ስገዛ ወይም ሕልሜን ሳሳካ እደሰታለሁ ብለህ እራስህን አትሸውድ፤ መኪና የገዛ ሕልሙን ያሳካ ሁሉ ደስተኛ አይደለም፤ ዋናው ነገር ደስተኝነት ሕልም ሲሳካ ወይም የምትፈልገውን ስታገኝ ሳይሆን፤ መጀመሪያ ምንም ሳይኖርህ ባለህ ነገር ለመደሰት ስትወስን ነው በራሥህ የውስጥ ሠላም የምትደሰት ከሆነ፤ የውጭው ረብሻና ጫጫታ ምንም አይመስልህም ዞር ብለህ ብታይ ሕይወት እጅግ በጣም ውብ ናት፤ አሁን ባለህ ስትደሰት ሌላው ቀስስስስስ እያለ ይመጣል ደስታ ደግሞ በነገሮች መገጣጠም የሚመጣ ሳይሆን ደስታህ የውስጥህ ምርጫ ውጤት ነው። ስለዚህ

ደስተኛ ሁን

https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
143 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 21:57:38 ተጠቀምበት !

ፈተና በህይወታችን የሚመጣው እንድም ሊያጠነክረን አንድም በህይወታችን ምን እንደተማርን ሊፈትሸን ነው ! ወደኋላ ካልንለት ይጥለናል ከተጋፈጥነው እና ወደኋላ ሳንል ካሸነፍነው ግን ይሸልመናል!

መልካም ምሽት ተመኘን
https://t.me/consult_emir
https://t.me/consult_emir
139 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ