Get Mystery Box with random crypto!

ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ brana_book — ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ brana_book — ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @brana_book
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 373

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-08 21:04:51
403 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:16:17

329 viewsMIKIYAS DANAIL, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 12:10:36
120 viewsMIKIYAS DANAIL, 09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 13:56:37 ይህን ስያሜ የተረዱ የጥንታውያን የኢትዮጵያ ቤተ ክትስትያን መጻሕፍትና ሊቃውንት ዛሬ ሁላችንም በተልምዶ "ካቶሊክ" በማለት የምንጠራቸውን ወገኖች የሚገልጹት እንዲ በማለት ነበር፡፡ ሃይማኖቱን ሲጠቅሱ "ሃይማኖተ ሮም"ተከታዮቹን ሲጠቅሱ "ሰብአ ሮምያ ወይም ሮማውያን" በማለት ነው፡፡
ስልዚህም ሐዋርያዊት የሆነች ቅደስት ቤተክርስቲያን በአስተምህሮም ሆን በድርሰኖቿ ልትጠራቸው የሚገባው በተገቢው አስማት (ስሞች) ሲሆን ይኸውም ሃይማኖቱን ስንጠራ "ሃይማኖተ ሮም" ቤተክርስቲያኒቱን "የሮም ቤተክርስቲያን" ተከታዮቹን ድግሞ "ሰብአ ሮም ወይም ሮማውያን" በማለት ልንጠራቸው ይገባል፡፡ በአጠቃለይ ቤተክርስቲያን አለማቀፋዊት ነች ስንል እንዲህ ማለታችን ነው፤
ቤተክርስቲያን የሁሉም ናት፣ በሁሉም ያለችናት፣ በሰማይምም በምድርም ያለችናት ማቴ28÷19፡፡

ቤተክርስቲያን በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ አትከፈልም አትወሰንም፤
ቤተክርስቲያን ስለመልካም አመለካከትና አሠራር ለሁሉም የምታስተምር መንፈሳዊት ተቋምናት፡፡

ቤተክርስቲያን የሰብአዊነትና የርኅራኄ ሥራ የምትሠራ ከፖለቲካና ከጥገኝነት ነፃ የሆነች ለሰው ልጅ ሁሉ መልካም ሥራ የምትሠራ መንፈሳዊት አደባባይናት፡፡

ቤተ ክርስቲያን አብ የመሠረታት ወልድ ያነፃት መንፈስ ቅዱስ የፈጸማት፤ መሠረቱ አብ፣ ህንጻዋ ወልድ፣ ጉልላቷ መንፈስ ቅዱስ የሆነች በጎ ፈቃድና ነፃነት ያላት መንፈሳዊት ሐመር ነች፡፡

ቤተክርስቲያን በዚህ አለች በዚያ የለችም የማትባል ሰማያዊትና ምድራዊት የሆነች መንፈሳዊት ተቋም ናት ገላ3÷25-29፡፡

~~°°°•••••••••••°°°~~
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።


ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!!!
እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን !!!
አምላክ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን
አሜን!
ተጻፈ:- ጥር 14/2015 ዓ/ም

መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479
https://www.facebook.com/mikiyas24/
የቴሌግራም ቻናል
: https://t.me/brana_Book
264 viewsMIKIYAS DANAIL, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 13:56:37 ሐዋርያት በሰበሰቡዋት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት" ምንጭ ፦ ጸሎተ ሃይማኖት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
የቤተክርስትያን መሠረታዊ ባህርያት ምንድን ናቸው
~••ቅድስት (Holy)••~
#ቅድስት_ናት፡- ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ የመሠረታት፣ ያነጻት፣ የቀደሳት ናትና ቤተክርስቲያን ቅድስትናት ኤፌ5÷26 የሐዋ 20÷28፡፡

ቅድስና የባህርይ የሆነ የሊቀ ቀዳሲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያናትና ቤተክርስቲያን ቅድስትናት 1ቆሮ6÷19፡፡ ቤተክርስቲያን በኃጢአት፣ በክህደት ረክሰው የነበሩ በእምነት፣ በንስሐ ወደ እርሷ ገብተው ይቀደሳሉና ቲቶ3÷3፡፡ የመጣበትን የኃጢአት መንገድ ትቶ በጽድቅ ጎዳና እንዲመለስ የምታደርግ የመንፈስ ቅዱስ ግምጃ ቤትናት ኤፌ2÷8 ቆላ1÷21፡፡

#አሐቲ_አንዲት_One
ቤተ ክርስቲያን እንዲት ናት ስንል ምን ማለታችን ነው? የሚለውን መሠረታዊ ሀሳብ መረዳት አለብን፤

አንዲትናት፡- ራሷና መስራቿ ክርስቶስ አንድ እንደሆነ ሁሉ ቤተክርስቲያን በወርቅ፣ በአፈር፣ በገጠርና በከተማ ብትሠራ አንዲት ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስንል እግዚአብሔር ግዕዛን ካላቸው ፍጥረታት ጋር ያለው ግንኙነት ስለሆነ በገዳም፣ በደብር፣በገጠር ብትሠራ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሰው ከመፈጠሩ በፊት በዓለመ መላዕክት የነበረችው የመላእክት አንድነት /ዓለመ መላእክት ከአቤል ጀምሮ እስከ ሐዲስ ኪዳን መግቢያ ድረስ የነበሩ የደጋግ ሰዎች አንድነት/ህብረት እና በክርስቶስ ደም የተመሠረተች የፀጋና የጽድቅ ምንጭ የሆነች አማናዊት የክርስቲያኖች አንድነት ናትና አንድ ባህርይ ያላት ናት፡፡ ምዕመናን እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ሃይማኖታቸውን የሚመሰክሩባት የአንድ የክርስቶስ አካል ናትና ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ ኤፌ 4፤5 ቆላ1፤18 ኤፌ1፤23፡፡

በተራ ካህን፣ በአበምኔት፣ በሊቀጳጳስ፣ በፓትርያርክ ብትገለገል፤ በተራግምጃ፣ በወርቀ-ዘቦ ብትገለገል ቤተክርስቲያን አንዲትናት፡፡ መስዋዕቱም ጥምቀቱም የሚገኘው ፀጋም አንድ፣ ቃለ እግዚአብሔርም አንድነው ዘዳ6÷4

በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የአንድነቱ መሠረት ሃይማኖት ነው፣ መገለጫው ደግሞ በምሥጢራት አንድነት (ሱታፌ) ነው፤ በምዕራባውያን (ካቶሊኮች) ዘንድ የአንድነቱ መሠረት ለሮማው ፓፓ መታዘዝና በእርሱ የአስተዳደር የዕዝ ሠንሰለት ሥር መሆን ነው፡፡ በፕሮቴስታንቶች ዘንድ ደግሞ ቤ/ክ ማለት የግለሰቦች ስብስብ (Congregation) ብቻ ነው፡፡

“Denominationalism might not be the ideal, but in a world of sin and misery, God in his providence can use each faithful denominational stone who hold to the once for all faith delivered to the saints that is articulated in the Apostles Creed to build his holy temple.” (Protestants’ view of Unity of the Church)

#ሐዋርያዊት_Apostolic
ሐዋርያዊትናት፡- የዓለምን ተስፋ የፈጸመው መሲህ ለሥራው ተከታዮች አድርጎ የሾማቸው 12ቱሐዋርያት መሪዎችና ቤተክርስቲያንን ከጌታ ተረክበው ያስረከቡን እነሱ ናቸው፡፡ የእስራኤል ዘሥጋ ታሪክ በ12ቱ የያዕቆብ ልጆች እንደ ተጀመረ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖች እምነት የክርስትና ምስክሩ የቅዱሳን ሐዋርያት ትምህርት ነውና ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት::

‹‹የኦርቶዶክስ ሊቃውንት›› ለመባል መመዘኛው ምንድን ነው?
በኦርቶዶክስ ነገረ መለኮት (Orthodox Theology) ጭብጥ፣ በተለይም በነገረ አበው የትምህርት ዘርፍ (Patrology) መሠረት ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባት›› መባል የሚቻለው ቢያንስ አራት መሠረታዊ መመዘኛዎችን ያሟላ ብቻ ነው (ሁሉንም ማሟላት ግዴታ ነው)፡፡

እነርሱም፡- ኦርቶዶክሳዊ ዶግማና ቀኖናን የጠነቀቀ አስተምህሮ (Orthodoxy Teaching)፣የቅድስና ሕይወት (Holiness of life)፣ ሲኖዶሳዊ እውቅና (Church approval) እና ወደ ዘመነ ሐዋርያቱ የቀረበ ቀደምትነት (antiquity) ናቸው፡፡

በዚህ ስሌት መሠረት ‹‹አባት›› የሚለው ቅጽል ዕድሜን፣ ጾታንና ሥልጣነ ክህነትን የሚገልጽ አይደለም ማለት ነው፡፡ በቅርብ ዘመናት የተነሱትም ‹‹ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን›› (Doctors of the Church) ቢባሉ ጭብጡ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ማንም ተነስቶ ራሱን በዚህ ደረጃ መሾምም ሆነ ሌላው በዚህ የክብር ረድፍ ሊያሰልፈው አይችልም!

ሐዋርያት ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን ምስክር ለመሆን የበቁበት ምክንያት፤ ክርስቶስን በዓይናቸው አይተውታል በእጃቸው ዳስሰውታል፤ ትምህርቱን በጆሮአቸው ሰምተዋል 1ዮሐ1÷1 ከትንሳኤውም በኋላ አይተውታል ዮሐ 21÷7 በኢየሱስ ክርስቶስ ተልከዋል ማቴ 28÷19፣ በስሙ ሐዋርያዊ ተአምራት ሲፈጽሙ ኑረዋል፡፡ ሐዋርያት በዓይናቸው ያዩትን፣ በጆሮቸው የሰሙትን የቤተክርስቲያንን ሕይወት ፈጽመዋል፡፡ ስለሆነም ሐዋርያት የተናገሩት ትምህርት ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምስክር ስለሆነ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊት ናት፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ያደረጉት ተአምራት፣ የጾሙት ጾም፣የጸለዩት ጸሎት፣ ያስተማሩት ትምህርት፣ የሠሩት ሥርዓት በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተፈጻሚ ሆነዋል፡፡



#ኩላዊት_ዓለም_አቀፋዊት_Universal_catholic-

በተልምዶ አጠራር ካቶሊክ/catholic እያልን የምንጠራው የሮም ቤተክርስትን፣ ሮማውያን ወይም ሃይማኖተ ሮም ነው፤ ይህ ስያሜ ለሮማውያን ሃይማኖት በተለምዶ የተቀጸለ እንጂ
ምክንያታዊ መጠሪያቸው አይደለም፤ የቤተክርስቲያን የታሪክ ሊቃውንት እንደሚገልጹት ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን አራት ዐበይት ጠባያት /መገለጫዎች አሏት ከእነርሱ ውስጥም አንዱ የሆነው ስፋኒት፣ ርትዕት፣ ምርጥ፣ ዓለም አቀፋዊ በእንግሊዘኛው /catholic ናት፡፡

በታሪክ እንደሚታወቅ ለቤተክርስቲያን ካቶሊክ የሚለውን ስያሜ የሰጠው አግናጥዮስ ዘአንጾክያ /Ignatius of Antioch ነው፡፡ አግናጥዮስ የህን ስያሜ የተጠቀመው ለቤተክርስቲያን የቅዱስ ቁርባን አፈጻጸም ሥርዓት ምን መምሰል እንዳለበት እንዲሁም የክህነት ደረጃዎችን በግልጽ ለይቶ በገለጸበት ጦማር ነበር፡፡ ብዙ ሊቃውንት እንደሚያስረዱት ይህ ስያሜ ለክርስቲያኖች በአንድነት የተሰጠ የወል የተጸውኦ መጠሪያ ስም እንጂ ለአንድ ወገን የተሠጠ መጠሪያ አይደለም፡፡ ይህ ስያሜ የሚገልጸው በሁሉም ሥፍራ በሰማይም በምድርም ያለች፣ የሚታዩና የማይታዩ ቅዱሳን ኅብረትና አንድነት፣በዘመነ ብሉያ ትንቢት የተነገረላትና በዘመነ ሐዲስ ፍጻሜ ያገነች ፣በነቢያትና በሐዋርያት አስተምህሮ የተመሠረተች፣ በመልክአ ምድር ያልተከፋፈለች፣ በአንድ ወገን አስተምህሮ በንፍቀት ያልተለየች ቤተክርስትያንን ነው፡፡ ይህ ስያሜ ጥልቅ ስፍሕ ሐተታ ያለው ቢሆንም ብዙ ሊቃውንት ስፋኒት /ከአጽናፍ አጽናፍ ያለች/፣ ርትዕት የነገረ እግዚአብሔርና የነገረ ድኅነት አስተምህሮ ያለትን፣ ለሁሉም አማንያን የቅድስና ሕይወትን የምታስተምር ቤተ ክርስቲያን እንደሚገልጽ ይስማማሉ፡፡
186 viewsMIKIYAS DANAIL, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 13:56:12         ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!!!
     እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን !!!
አምላክ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን   
አሜን!
      ተጻፈ:- ጥር 1/2015 ዓ/ም
                                
       መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
       ~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤”     ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
          ••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
       ~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479
https://www.facebook.com/mikiyas24/
የቴሌግራም ቻናል 
: https://t.me/brana_Book
154 viewsMIKIYAS DANAIL, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 12:10:57
ተጠንቀቁ!!!
209 viewsMIKIYAS DANAIL, 09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 12:09:31 ተጠንቀቁ!!!
212 viewsMIKIYAS DANAIL, 09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 16:53:22
172 viewsMIKIYAS DANAIL, 13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 18:13:18 **መግዛት ለምትፈልጉ#
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_በ0986025463_0966214181_ይደውሉ
181 viewsMIKIYAS DANAIL, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ