Get Mystery Box with random crypto!

ይህን ስያሜ የተረዱ የጥንታውያን የኢትዮጵያ ቤተ ክትስትያን መጻሕፍትና ሊቃውንት ዛሬ ሁላችንም በተ | ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

ይህን ስያሜ የተረዱ የጥንታውያን የኢትዮጵያ ቤተ ክትስትያን መጻሕፍትና ሊቃውንት ዛሬ ሁላችንም በተልምዶ "ካቶሊክ" በማለት የምንጠራቸውን ወገኖች የሚገልጹት እንዲ በማለት ነበር፡፡ ሃይማኖቱን ሲጠቅሱ "ሃይማኖተ ሮም"ተከታዮቹን ሲጠቅሱ "ሰብአ ሮምያ ወይም ሮማውያን" በማለት ነው፡፡
ስልዚህም ሐዋርያዊት የሆነች ቅደስት ቤተክርስቲያን በአስተምህሮም ሆን በድርሰኖቿ ልትጠራቸው የሚገባው በተገቢው አስማት (ስሞች) ሲሆን ይኸውም ሃይማኖቱን ስንጠራ "ሃይማኖተ ሮም" ቤተክርስቲያኒቱን "የሮም ቤተክርስቲያን" ተከታዮቹን ድግሞ "ሰብአ ሮም ወይም ሮማውያን" በማለት ልንጠራቸው ይገባል፡፡ በአጠቃለይ ቤተክርስቲያን አለማቀፋዊት ነች ስንል እንዲህ ማለታችን ነው፤
ቤተክርስቲያን የሁሉም ናት፣ በሁሉም ያለችናት፣ በሰማይምም በምድርም ያለችናት ማቴ28÷19፡፡

ቤተክርስቲያን በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ አትከፈልም አትወሰንም፤
ቤተክርስቲያን ስለመልካም አመለካከትና አሠራር ለሁሉም የምታስተምር መንፈሳዊት ተቋምናት፡፡

ቤተክርስቲያን የሰብአዊነትና የርኅራኄ ሥራ የምትሠራ ከፖለቲካና ከጥገኝነት ነፃ የሆነች ለሰው ልጅ ሁሉ መልካም ሥራ የምትሠራ መንፈሳዊት አደባባይናት፡፡

ቤተ ክርስቲያን አብ የመሠረታት ወልድ ያነፃት መንፈስ ቅዱስ የፈጸማት፤ መሠረቱ አብ፣ ህንጻዋ ወልድ፣ ጉልላቷ መንፈስ ቅዱስ የሆነች በጎ ፈቃድና ነፃነት ያላት መንፈሳዊት ሐመር ነች፡፡

ቤተክርስቲያን በዚህ አለች በዚያ የለችም የማትባል ሰማያዊትና ምድራዊት የሆነች መንፈሳዊት ተቋም ናት ገላ3÷25-29፡፡

~~°°°•••••••••••°°°~~
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።


ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!!!
እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን !!!
አምላክ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን
አሜን!
ተጻፈ:- ጥር 14/2015 ዓ/ም

መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!
••••••••••••••••••
የፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉ ፤ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, እና Share ያድርጉ :-
~•••••••~•••••••~•••••~
የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/mikiyas.danail
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063973695479
https://www.facebook.com/mikiyas24/
የቴሌግራም ቻናል
: https://t.me/brana_Book