2022-11-28 20:41:29
"የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ"
የቤተክርስቲያን ታሪክ ማለት የክርስትና እምነት ታሪክ ማለት ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርታችን የክርስትና እምነት የአምላክ መገለጥ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዘመን በቦታ የተደረገ ስለሆነ መቸ? ወዴትና ለምን? እንደሆነ የምናውቅበት ክፍል ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በጉዞው ኹሉ የገጠመውን ችግርና ምቾት የምንማርበት ነው፡፡
የቤተክርስቲያንን ታሪክ የሚያጠና ተማሪ ከቤተልሔም ዋሻ ጀምሮ እስከ ቀራንዮ ድረስ ከካታኮምብ የግበበ ምድር ሕይወት ጀምሮ እስካለንበት ጊዜ ድረስ ያለውን ኹኔታ እያወዳደረ ያጠናል፡፡ በዚያም የጥናት ጊዜው ያለፈውን ያውቃል፤ ያለበትንም ሁኔታ ያስተውላል፤ ለሚመጣውም ትውልድ ማሳደጊያ የሚሆን ቅርስ በማስታወሻው ቋጥሮ ያስቀምጣል፡፡
+++ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ+++
72 viewsMIKIYAS DANAIL, 17:41