Get Mystery Box with random crypto!

ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ brana_book — ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ brana_book — ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @brana_book
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 373

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-11-05 16:32:27
66 viewsMIKIYAS DANAIL, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 21:06:26 ምሥጢረ ሜሮን

ምሥጢረ ሜሮን ከምሥጢረ ጥምቀት ቀጥሎ ወዲያውኑ የሚፈጸም ማኅተመ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
በተጨማሪም የአጠቃቀም ሥርዓቱና ጸሎቱ የተለየ ሆኖ ቅብዓ ሜሮን ለምሥጢረ ክህነትና ለምሥጢረ ተክሊል ማክበሪነት ያገለግላል፡፡
ሜሮን ማለት ቅብዐ ቅዱስ፣ የተባረከ ሽቱ፣ ብፁዓን ጳጳሳት ከበለሳንና ከዕፀወ ዕጣን ከአስጳዳቶስ ከሌላም ከብዙ ዓይነት ሽቱ፣ ሥርዓተ ጸሎት ፈጽመው የሚያወጡት ነው፡፡

ምሥጢረ ሜሮን ከጥምቀት ጋር ተያይዞ ከጥምቀት ቀጥሎ የሚፈጸም፣ መንፈስ ቅዱስን የሚያሳድር፣ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቃችንን፣ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ መወለዳችንን የሚያረጋግጥልን ታላቅ ምሥጢር ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ፣ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ሲወጣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ባረፈ ጊዜ የአብ የባሕርይ ልጅነቱ በባሕርይ አባቱ ምስክርነት ተረጋግጧል፡፡
እንደዚሁም ሁሉ አማኞች ተጠምቀው ሲወጡ በቅዱስ ቅብዐት በሜሮን ከብረው የጸጋ ልጅነት ማግኘታቸው ይረጋገጣል፡፡
ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ መወለዳቸው ይታወቃል፡፡
ምሥጢረ ሜሮንን የመሠረተልን ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “እኔ በንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል” (ማቴ 3፡ 11) በማለት እንደመሰከረለት በመንፈስ ቅዱስና በእሳት የሚያጠምቅ እሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡
ለሐዋርያትም ተስፋ እንዳደረገላቸው በበዓለ ሃምሳ ከአብ የሠረፀ መንፈስ ቅዱስን ላከላቸው፤ በደቀ መዛሙርቱ ላይ እፍ ባለባቸው ጊዜ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበሉ፡፡
ከዕርገት በፊትም ደቀ መዛሙርቱን እስከ ቢታንያ አውጥቶ እጁን አንሥቶ በላያቸው ጭኖ ባርኳቸዋል፡፡
በዚሁ መሠረትም ቅዱሳን ሐዋርት የተቀበሉትን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ለተከታዮቻቸው በአንብሮተ ዕድ ያድሉ ነበር፡፡
አዳዲስ ተጠማቂዎችም በሐዋርያትና በተከታዮቻቸው አንብሮተ እድ እየተደረገላቸው በልጅነት ይከብሩ ነበር፡፡
ከጊዜ በኋላ ተጠማቂዎች እየበዙ ሲመጡ ለአባቶቻችን እግዚአብሔር ገልጾላቸው ቅብዐ ሜሮኑን በአንብሮተ እድ እያከበሩ ለአብያተ ክርስቲያናት በማከፋፈል ምሥጢረ ሜሮን በአንብሮተ እድ ምትክ እንዲፈጸም ማድረግ ጀመሩ፡፡
ይህንንም የቤተ ክርስቲያን አባቶች በሎዶቅያ ጉባኤ ወስነው አጸኑ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በሐዲስ ኪዳን በቅብዐ ሜሮን የሚታደለውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በተመለከተ ሲያብራራ “እናንተስ ከቅዱሱ ያገኛችሁት ቅብዐት አላችሁ፤ ሁሉንም ታውቃላችሁ፡፡
እውነትን የምታውቁ ስለሆናችሁ፣ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን እንደማታውቁ አድርጌ አልጽፍላችኁም፡፡” (1ዮሐ 2፡20-22) በማለት አስተምሮናል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ከዚህ አሳብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልእክት “ከእናንተ ጋር በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፡፡
ደግሞም ያተመንና የመንፈስ ቅዱስን ፊርማ በልቦናችን የሰጠን እርሱ ነው፡፡” በማለት አስተላልፎልናል፡፡ (2ቆሮ 1፡ 21-23)

ቅብዐ ሜሮን ሦስት ዓይነት አገልግሎቶች አሉት
1ኛ. ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል፡- አዳዲስ አማንያን(ተጠማቂዎች) ከተጠመቁ በኋላ በሜሮን ተቀብተውና ከብረው ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንዲያድርባቸው ያደርጋል፡፡
2ኛ. የእግዚአብሔር አገልጋዮች (ካህናት) ለመሾም፡- ካህናት አባቶች የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ወይም ሕዝብ ለማገልገል የሚችሉበትን ሥልጣን (ሹመት)፣ ማስተዋል (ጥበብ)፣ ኃይል (ብርታት)፣ ትዕግሥትና
ጽናት የሚያጎናጽፋቸውን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል እንዲችሉ በሚሾሙበት ጊዜ በሜሮን ይቀባሉ
(ይከብራሉ)፡፡
3ኛ. አዳዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲንና ለንዋየ ቅድሳት ማክበሪያ፡- አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ንዋየ ቅድሳቱ የእግዚአብሔር ገንዘቦች እንዲሆኑ በሜሮን ተቀብተው እንዲከብሩ ይደረጋል፡፡
ከጽላቱ ጀምሮ መስቀሉ፣ ጽንሐው፣ ከበሮው፣ ሰኑ፣ ብርቱና የመሳሰለው ሁሉ በሜሮን ከከበረ በኋላ ለአገልግሎት ይውላል፡፡

ቅብዐ ሜሮን ለሁለት ምሥጢራት ማክበሪያነት (ማተሚያነት) ያገለግላል፡፡
ምሥጢረ ክህነትና ምሥጢረ ተክሊል ናቸው፡፡
ምሥጢረ ክህነት ካህናት ከቄሱ ጀምሮ ወደ ላይ ያሉት ማለትም ጳጳስና ቄስ በቅብዐ ሜሮን ከብረው ካህናተ እግዚአብሔር ይሆናሉ፡፡
ይህም በብሉይ ኪዳን “እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ የቅብዐትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈሰዋለህ፤ ትቀባዋለህ፡፡
ልጆቹንም ታቆርባቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፡፡ እንዲሁም የአሮንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ፡፡” (ዘፀ 29፡ 1-8) የተባለውን መሠረት ያደረገ ነው፡፡
በሐዲስ ኪዳንም ካህናትን በቅብዐ ሜሮን አክብሮ ሥልጣነ ሐዋርያትን ማስተላለፍ ጥንታዊ የተለመደና የከበረ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡
ምሥጢረ ተክሊልም ሙሽራውና ሙሽሪት በቅብዐ ሜሮን ታትመው ይከብራሉ፡፡

ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆን የጀመርነው ከተጠመቅንበትና በሜሮን ከከበርንበት ዕለትና ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡
በመቅደስ ሰውነታችን አድሮ የነበረውን አምላክ አሳዝነን አስወጣነው ወይስ አስደስተን እስካሁን ከእኛ ጋር አቆየነው? የእግዚአብሔርን የክብር ዕቃ፣ ማደሪያ መቅደሱንም በጥንቃቄ የማይዙና የሚያቃልሉ ሁሉ የሚቀጡ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
የመቅደሱ ባለቤት እግዚአብሔር ለቤቱና ለሥርዓቱ ቀናዒ ነው፡፡
መቅደሱ የኃጢአት ሸቀጥ ማራገፊያና መነገጃ ሲሆን ዝም ብሎ አያይም፡፡ (ማቴ 21፡12-18) ናቡከዳናፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ማርኮ በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት በክብር ያኖራቸውን ንዋያተ ቅድሳት አስመጥቶ በማቃለል ጣዖታትን እያመለኩ እንዲበሉባቸውና እንዲጠጡባቸው በማድረጉ በንዋየ ቅድሳቱ በተሳለቀባቸው ዕለትም ተገድሎ አደረ፡፡(ዳን 5፡1 እስከ ፍጻሜ) እግዚአብሔርንና የሱ የሆኑትን ሁሉ የማያከብሩ ሰዎች ለማይገባ አእምሮ ተላልፈው እንደሚሰጡ ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ (ሮሜ 1፡ 21) እግዚአብሔር ያከበራቸውን ማቃለል እግዚአብሔርን ማቃለል ነውና፡፡ (ሉቃ 10 -16)

ሜሮን ከተፈላ (ከተዘጋጀ) በኋላ በየሀገረ ስብከቱ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይታደላል፡፡
ከዚህ ውጪ ከአታላዮች በስመ ሜሮን ወይም ቅብዐ ቅዱስ እየገዙ ለምሥጢረ ሜሮን መፈጸሚያነት መጠቀም ሕገ ወጥ ተግባር ነው፡፡
ምእመናን የአታላዮችን ድርጊት በመቃወምና ለካህናት ትክክለኛ አገልግሎት አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት የበኩላቸውን ሁሉ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ምንጭ፡- የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራትና ሥርዓት (2011)
348 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 21:06:24
147 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 08:50:50 https://t.me/brana_Book
325 viewsMIKIYAS DANAIL, 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 22:19:58
303 viewsMIKIYAS DANAIL, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 22:06:58
እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚና አለው
++++++++++++++++++++
በሕይወት የሚያጋጥምህ እያንዳንዱ ሰው
የእራሱ ሚና አለው!
አንዳንድ ይፈትንሃል
አንዳንዱ ይጠቀምብሃል
አንዳንዱ ይወድሃል
አንዳንዱ ያስተምርሃል
እንዳንዱ . . . .
ሁሉም ሰው እንድ ዓይንት እንዲሆን አትጠብቅ!
277 viewsMIKIYAS DANAIL, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:50:52
" የኢትዮጵያ መሪዎች ያልተነገሩ እና ያልተሰሙ ታሪኮች ከጥንት እስከ ዛሬ " የተሰኘው የኤርሚያስ ሁሴን መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

መጽሐፉ የአክሱም ነገስታት ፣ የላስታ ነገስታት ፣ የሰለሞናዊ ነገስታት ፣ የጎንደር ነገስታት ፣ የዘመነ መሳፍንት ፣ የኦሮሞ ሞቲዎች ፣ የምስራቅ አሚሮች ፣ የአዳል ሱልጣኔት ፣ የደቡብ ነገስታት ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፣ የሸዋ ነገስታት ፣ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስታት ፣ የኢትዮጵያ መሪዎችን ታሪክ ከጥንት እስከዛሬ ድረስ በስፋት የሚታትት ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ነው ።

መጽሐፉን ለማንበብ ይሸምቱት
214 viewsMIKIYAS DANAIL, edited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:50:52
የሰው ልጅ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ናት፤ ብዙ ዓይነት ምግቦች የያዘች ቅርጫትንም ትመስላለች፡፡ በቅርጫቱ ውስጥ ከሞሉ ምግቦች የሚስማማንን ለይተን መምረጥ ግን የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው፡፡

ፍሬ ሕይወት እያለ ፍሬ ሞት ቀጥፎ እንደበላ እንደ አባታችን አዳም ከቅርጫት ሙሉ ምግብ ጣፋጭ እያለ መራራ፣ ጤናማ እያለ መርዛማ እንዳንመርጥም ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ “የጅብ ችኩል ቀንድን ይነክሳል” የሚለው አባባልም እዚህ ጋር መታወስ ያለበት ነው፡፡

ቀንድ የነከሰ ጅብ በማይጠቅም ቦታ ጊዜ ማጥፋቱ ብቻ ሳይሆን ሥጋ የሚበላበት ጥርሱን ማጣቱንም ማስተዋል ይገባናል፡፡ እኛም የማይጠቅም ምርጫ መርጠን ጊዜአችንን፣ ጉልበታችንን እና ሌሎች ሀብቶቻችንንም በከንቱ እንዳናባክን አሊያም ብዙ መንገድ ከተዝን በኋላ መንገዳችን ስሕተት መሆኑ ሲገባን “ዳግመኛ አዲስ መንገድ መጀመር አንችልም” ብለን ተስፋ እንዳንቆርጥ በምርጫችን ትክክለኛነት ላይ በጥልቀት ማሰብ የግድ ነው፡፡
181 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:46:19
181 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:46:19
203 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ