Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ልጅ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ናት፤ ብዙ ዓይነት ምግቦች የያዘች ቅርጫትንም ትመስላለች፡፡ በ | ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

የሰው ልጅ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ናት፤ ብዙ ዓይነት ምግቦች የያዘች ቅርጫትንም ትመስላለች፡፡ በቅርጫቱ ውስጥ ከሞሉ ምግቦች የሚስማማንን ለይተን መምረጥ ግን የእያንዳንዳችን ድርሻ ነው፡፡

ፍሬ ሕይወት እያለ ፍሬ ሞት ቀጥፎ እንደበላ እንደ አባታችን አዳም ከቅርጫት ሙሉ ምግብ ጣፋጭ እያለ መራራ፣ ጤናማ እያለ መርዛማ እንዳንመርጥም ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ “የጅብ ችኩል ቀንድን ይነክሳል” የሚለው አባባልም እዚህ ጋር መታወስ ያለበት ነው፡፡

ቀንድ የነከሰ ጅብ በማይጠቅም ቦታ ጊዜ ማጥፋቱ ብቻ ሳይሆን ሥጋ የሚበላበት ጥርሱን ማጣቱንም ማስተዋል ይገባናል፡፡ እኛም የማይጠቅም ምርጫ መርጠን ጊዜአችንን፣ ጉልበታችንን እና ሌሎች ሀብቶቻችንንም በከንቱ እንዳናባክን አሊያም ብዙ መንገድ ከተዝን በኋላ መንገዳችን ስሕተት መሆኑ ሲገባን “ዳግመኛ አዲስ መንገድ መጀመር አንችልም” ብለን ተስፋ እንዳንቆርጥ በምርጫችን ትክክለኛነት ላይ በጥልቀት ማሰብ የግድ ነው፡፡