Get Mystery Box with random crypto!

BULBULA NEWS⏰

የቴሌግራም ቻናል አርማ bbn_info — BULBULA NEWS⏰ B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bbn_info — BULBULA NEWS⏰
የሰርጥ አድራሻ: @bbn_info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 897
የሰርጥ መግለጫ

#Info Makes Chanege
#አንድ_ላይ_ኾነን_ለውጥ_እንፈጥራለን!
ማንኛውንም ቡልቡላ ነክ ወሬ፥ መረጃ እና ሐሳብ @Bulbula_bot ላይ ልታደርሱን አልያም #ልትጠይቁን ትችላላችሁ።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-04 21:39:58 14
የቡልቡላ አሜን እግርኳስ ፕሮጀክት የ14ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እጅግ በደመቀ ሁኔታ በዛሬው ዕለት በአዲሱ የግሬት ኮሌጅ አዳራሹ ውስጥ ተካሂዷል።

በቅድሚያ የቡልቡላ ራዕይ አዳራሽ ለፕሮግራሙ የተፈቀደ ሲሆን ባለቀ ሰዓት ግን ለሌላ ነገር እንደተያዘ ተሰማ፡ እጅግ ባለቀ ሰዓት ግን ከቢሮክራሲ ነፃ በሆነ ቀና አመለካከት ግሬት ኮሌጅ አዳራሻቸውን የሰፈራችን ተወካይ ለዚህ ፕሮጀክት የምስረታ በዓል ፈቀዱ።

ይህን የዛሬውን ፕሮግራም ለየት የሚያደርጉ ነገሮች ነበሩ
የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት ተገኝተዋል!

የቦሌ ክፍለከተማ የወጣቶችና ስፖርት የስራ ሒደት ኃላፊ ተገኝተዋል

በፕሮግራሙ ላይ ከተጠበቀው ውጪ አዲስና ድንቅ የፕሮግራም ቅደም ተከተል ነበር።

በፕሮግራሙ ላይ የግሬት ኮሌጅ ሥራ አስኪያጅ ተገኝተው በቡልቡላ አሜን ስፖርት ፕሮጀክት በኩል ወረቀት አፅፈው ለሚመዘገቡ ከምዝገባ ክፍያ ውጪ በሆነ ምዝገባ በተጨማሪም ከ 30-35% ቅናሽ ተደርጎ እንዲማሩ ዕድል አመቻችተዋል!

የዛሬው ፕሮግራም እጅግ አስደናቂ ነበር። ፎቶዎችን ከተለያዩ ካሜራማኖች ላይ አሰባስበን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

ዛሬ ከተባበርን ምንም ማድረግ እንደምንችል አይተንበታል። በእውነት ለ #ግሬት_ኮሌጅ ልዩ ምሥጋና ይድረሳቸው፡ ቀና አመለካከት እንዳላቸው በተግባር አሳይተውናል!!

@BBN_info
659 viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:34:01

ዛሬ ለቡልቡላ ልዩ ቀን!

የቡልቡላውያን አለኝታ እና የትውልድ ስነምግባር መቀረጫም እየሆነ ለዘመናት የቆየው የቡልቡላ አሜን እግር ኳስ ፕሮጀክት ነገ 14'ኛ ዓመት መታሰቢያውን ነገ በደማቅ ሁኔታ ያከብራል!

ይህን ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው በቅርቡ የተመረጡት የአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን #ፕሬዝዳንት የሚገኙበት ትልቅ ዝግጅት መሆኑ ነው። በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን የሚላክ ሚዲያ ይኖራል!!

የቦሌ ክፍለከተማ ስፖርት ጽ/ቤት ፡ የሰልጣኝ ቤተሰቦች ፡ የቀድሞ የወንድና የሴት ተጫዋቾች እንዲሁም ሌሎች ቡልቡላ ውስጥና ከቡልቡላ ውጪ የሚገኙ የክብር እንግዶች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

እንኳን አደረሰን፡ አደረሳችሁ!!


በልዩ ምክንያት ቦታ ካልተቀየረ በቀር ፕሮግራሙ የሚከበረው ከአቦ ታክሲ መያዣ ወረድ ብሎ ያለው ሐሮት ታወር አጠገብ በተከፈተው አዲሱ
#የግሬት_ኮሌጅ አዳራሽ ውስጥ ነው!
726 viewsedited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:16:59
ማሳሰቢያ

ትምህርት መች ችጀምራል

መስከረም 2 -6 ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ

መስከረም 3 የ12'ኛ ክፍል ተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት ይጀምራሉ

መስከረም 9 ትምህርት በይፋ ይጀመራል!!

#ሼር፡ ላልሰሙት በሙሉ

@BBN_info
547 viewsedited  18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:23:58
SCHOOL Of Aygoda!

ስኩል ኦፍ አይጎዳን ወክላ በአዲስ አበባ ደረጃ በኢትዮ ማት ኦሎምፒያድ የሒሳብና የታለንት ውድድር የተካፈለቸው ተማሪ ሔመን ፡ስለሺ ከአዲስ አበባ 2'ኛ በመውጣት ሜዳልያ አምጥታለች!

#እንኳን_ደስ_አላችሁ!!

ሔመን ጀግኒት ነሽ በርቺ የኛ ልጆች ገና ታኮሩናላችሁ!

@BBN_info
566 viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 11:59:49 " #ቡልቡላ " ምን ማለት ነው

ማንኛውም ሰው የሰፈሩን ስያሜ ትርጉም የማወቅ የውዴታ ግዴታ ስላለበት እነሆ የሰፈራችሁን ስያሜ ትርጉም ስሙ

የሰፈራችን ሙሉ ስያሜ " ቦሌ ቡልቡላ" ነው።

#ቦሌ የአፈር ዓይነት ስም ሲሆን በአያቶቻችን ጊዜ ከተማው እንደዚህ ሳይዘምን በከብቶች ተወዳጅ የነበረ ጨዋማ ጣዕም የነበረውን አፈር የያዘ መሬት ነበር፡፡

ቦሌ ማለት ከላይ ከዑራኤል - ቦሌ አራብሳ፤ በኛ በኩል ደግሞ እስከ አቃቂ ወንዝ ድረስ ያለውን ቦታ የሚያመላክት ነው፡፡ አዲስ አበባ ስትሞቅ ቦሌ/ዋናው ፣ 22 ገርጂ፣ ቡልቡላ፣ አራብሳ፣ ጨፌ ወደሚሉት ትናንሽ ክፍልፋዮች ተከፋፋለ፡፡

እናም እኛ በዕድለኝነት የምንኖርባት #ቡልቡላም የራሷ የሆነ ትርጉም እና ታሪክ አላት፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በፊት ቡልቡላ ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጥ የስንዴ አምራችነት እንደምትታወቅ እና አሁን ቀውጢ መኖርያ ከተማ እንደሆነች ተወዳጁ የ80ዎቹ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ፀጋዬ ደንደና በመረዋ ድምፁ እንዲህ ሲል አንጎራጉሯል
‹‹ቦሌ ቢየ ቡልቡላ
ዱር ቀመዲቱ ቢቂላ
አመ ጢያራቱ ጉሉፋ››


ትርጉም
<< ቦሌ ቡልቡላ የምትባለው አገር(ቦታ)
ድሮ የስንዴ መብቀያ
አሁን የአውሮፕላን መጋለብያ ..>>

በዚህ ግጥም ውስጥ የቡልቡላን ቀደምት ገፅታ ካሁን ጋር እያነፃፀርን መሳል እንችላለን፡፡

በመሠረቱ ቡልቡላ ከአራት ኪሎ ተነስቶ፡ እስጢፋኖስ ከዚያም በሩዋንዳ አድርጎ የሚመጣውን ወንዝ ለመጥራት የሚጠቀሙበት ስም ነበር። እስከቅርብ ጊዜም በአባሳሙኤል በኩል የሚያልፈውን ይህን የሰፈራችን መጠሪያ ለመሆን የበቃውን ወንዝ ነዋሪዎች እየቀዱ ይጠቀሙ ነበር።

ወደተጠየቀው መሰረታዊ ጥያቄ ስንመለስ #ቡልቡላ የሚለው ቃል ቡልቡሉ ከሚለው የኦሮምኛ ቃል የመጣ ነው፡፡ ትርጉሙም በጥብጥ፣ አዋሕድ፣ አደባልቅ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ "ጌቱ በሶ በጠበጠ" ለማለት " ጌቱ'ን በሶ ቡልቡሌ" ይሆናል ማለት ነው፡፡

#ቡልቡላ ሲሆን ደግሞ ሶስተኛ መደብ- ነጠላ ቁጥር ( #በጥባጭ) ማለት ነው፡፡

ይኸው ቡልቡላ እንድስያሜዋ የተለያዩ የኑሮ ደረጃ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ብሄር፣ ሐይማኖት፣ ባህል… ያላቸውን ሰዎች አንድ ላይ በጥብጣ፤ አዋህዳ አፋቅራ የያዘች ሰፈር መሆኗን አስመስክራለች

የቡልቡላ መሆን ሽልማት ነው፡፡

መልካም ህይወት ከምርጧ ሰፈራችን ጋር

@BBN_Info
609 viewsedited  08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:30:54
ከአውዚሊየም ካቶሊክ ት/ቤት
ማስታወቂያ ለወላጆች

የ2015 ዓም U.KG እና L.KG የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች

ትምህርት መስከረም 9 ይጀምራል

@BBN_info
562 viewsedited  06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:30:16

ታችኛው ኮንዶሚንየም (መከላከያ) ትላንት 6 ሰአት አካባቢ ብሎክ 137 የ5 አመት ህፃን ልጅ ከ3ተኛ ፎቅ ወድቆ ሕይወቱ አልፏል። ዛሬ ቀብር ነበር። የወታደር ልጅ ነው። እጅግ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ነው

የምንችል እየሔድን ቤተሰቡን ብናጽናና መልካም ነው
፡ ለሌሎቻችሁም ጥንቃቄና ትምህርት እንዲሆን ያስፈልጋል!

@BBN_info
607 viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:06:08

ለ2015 አዲሱ ዓመት ምን አዲስ ለውጥ አቅዳችኋል??

ሁላችንም ለለውጥ ለመሻሻልና ለዕድገት ራሳችንን እንደምናዘጋጅ እሙን ነው!

በአካዳሚክ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የቦርድ አባላት የተዋቀረው ግሬት ኮሌጅ ቀጣዩን ዓመት ለህይወታችሁ መሻሻልያ የምታደርጉበትን መንገድ አመቻችቶላችሁ ብቅ ብሏል።

እዚሁ በራፋችን ላይ ቡልቡላ ውስጥ በተጀመረው አዲሱ ቅርንጫፉ፡-
በማስተርስ
በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን

በመጀመያ ዲግሪ
በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ
በማኔጅመንት

በቲቪኢቲ - ደረጃ 4
በIT
HRM[ Human Resourse Managment]
ማርኬቲንግ
አካውንቲንግ

በአጫጭር ስልጠናዎች
Advanced computer training
IFRS , Peachtree, clothing
Photoshop video editing
SPSS, C++ & Java ይሰጣል። ስለዚህ ይስማማኛል በምትሉት ዘርፍ መመዝገብና መማር ትችላላችሁ


#አድራሻ፡ መሐል ቡልቡላ ፡ ከአቦ ታክሲ መያዣ ወረድ ብሎ፡ ሐሮት ታወር አጠገብ

#እማራለሁ! #እለወጣለሁ! "ሰው" #እሆናለሁ!

@BBN_info
587 viewsedited  06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:00:19 ULBULA BILLBOARD

ከቀጣይ እሑድ ጀምሮ ከምንጀምራቸው ፕሮግራሞች መሐከል አንዱ ቡልቡላ ቢልቦርድ የተሰኘ ተወዳጅ ፕሮግራም ነው። በዚህ ፕሮግራም በየሳምንቱ የአገር ውስጥና የባሕር ማዶ ሙዚቃዎችንና ሌሎች የጥበብ ስራዎችን ደረጃ የምናወጣ ሲሆን ሌሎች የማወዳደርያና የሽልማት ሐሳቦችንም የያዘ ፕሮግራም ነው።

የመጀመሪያ የማወዳደር ስራችንን ቡልቡላ ውስጥ የሚገኙ ሬስቶራንቶችንና አስተናጋጆችን እናወዳድርበታለን፡ እንሸልምበታለን

ቡልቡላ ውስጥ መመስገን ያለበት ተቋም የቱ ነው? ክብር እንድንሰጥላችሁና እንድንሸልምላችሁ የምትፈልጉት አስተናጋጅ አለ? ቆሽታችሁን ያሳሰረረው አገልግሎት ሰጪ አካልስ ማነው?

ሁሉንም አሳውቁን፡ ማመስገን ታላቅነት ነው- ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን። ሐሳባችሁን @Bulbula_bot ላይ startን በመንካት ላኩልን።


ቡልቡላ፡ የሥልጡን ማኅበረሰብ መኖሪያ!

@BBN_info
530 viewsedited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:08:02 ቆንጆ የስራ ዕድል
#ለሴቶች

የስራው አይነት፡ #ሴልስ
( የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን መሸጥ)

የስራ ቦታ፡ ቡታጅራ የቻይኖች መሥሪያ ቤት


ቅድመ ኹኔታ፡ በ2014 የተመረቀች ( በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ) ፣ ጥሩ/perfect እንግሊዘኛ መናገር የምትችል ፡ ጠንካራ የሥራ ፍላጎት ያላት።

ደመወዝ፡ ማራኪ$

ተጨማሪ ዕድሎች ፡ ቻይንኛ ቋንቋ በነፃ ትለምዳለች፡ መኖርያ ቤት ከነርሱ ነው፣ በየጊዜው የሥራና ደመወዝ ዕድገት አለው ፡ሰፊ የስራ ዕድል ኔትዎርክ ውስጥ ትገባለች



Inbox @Um_coming

@BBN_info
522 viewsedited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ