Get Mystery Box with random crypto!

' #ቡልቡላ ' ምን ማለት ነው ማንኛውም ሰው የሰፈሩን ስያሜ ትርጉም የማወቅ የውዴታ ግዴታ ስላ | BULBULA NEWS⏰

" #ቡልቡላ " ምን ማለት ነው

ማንኛውም ሰው የሰፈሩን ስያሜ ትርጉም የማወቅ የውዴታ ግዴታ ስላለበት እነሆ የሰፈራችሁን ስያሜ ትርጉም ስሙ

የሰፈራችን ሙሉ ስያሜ " ቦሌ ቡልቡላ" ነው።

#ቦሌ የአፈር ዓይነት ስም ሲሆን በአያቶቻችን ጊዜ ከተማው እንደዚህ ሳይዘምን በከብቶች ተወዳጅ የነበረ ጨዋማ ጣዕም የነበረውን አፈር የያዘ መሬት ነበር፡፡

ቦሌ ማለት ከላይ ከዑራኤል - ቦሌ አራብሳ፤ በኛ በኩል ደግሞ እስከ አቃቂ ወንዝ ድረስ ያለውን ቦታ የሚያመላክት ነው፡፡ አዲስ አበባ ስትሞቅ ቦሌ/ዋናው ፣ 22 ገርጂ፣ ቡልቡላ፣ አራብሳ፣ ጨፌ ወደሚሉት ትናንሽ ክፍልፋዮች ተከፋፋለ፡፡

እናም እኛ በዕድለኝነት የምንኖርባት #ቡልቡላም የራሷ የሆነ ትርጉም እና ታሪክ አላት፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በፊት ቡልቡላ ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጥ የስንዴ አምራችነት እንደምትታወቅ እና አሁን ቀውጢ መኖርያ ከተማ እንደሆነች ተወዳጁ የ80ዎቹ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ፀጋዬ ደንደና በመረዋ ድምፁ እንዲህ ሲል አንጎራጉሯል
‹‹ቦሌ ቢየ ቡልቡላ
ዱር ቀመዲቱ ቢቂላ
አመ ጢያራቱ ጉሉፋ››


ትርጉም
<< ቦሌ ቡልቡላ የምትባለው አገር(ቦታ)
ድሮ የስንዴ መብቀያ
አሁን የአውሮፕላን መጋለብያ ..>>

በዚህ ግጥም ውስጥ የቡልቡላን ቀደምት ገፅታ ካሁን ጋር እያነፃፀርን መሳል እንችላለን፡፡

በመሠረቱ ቡልቡላ ከአራት ኪሎ ተነስቶ፡ እስጢፋኖስ ከዚያም በሩዋንዳ አድርጎ የሚመጣውን ወንዝ ለመጥራት የሚጠቀሙበት ስም ነበር። እስከቅርብ ጊዜም በአባሳሙኤል በኩል የሚያልፈውን ይህን የሰፈራችን መጠሪያ ለመሆን የበቃውን ወንዝ ነዋሪዎች እየቀዱ ይጠቀሙ ነበር።

ወደተጠየቀው መሰረታዊ ጥያቄ ስንመለስ #ቡልቡላ የሚለው ቃል ቡልቡሉ ከሚለው የኦሮምኛ ቃል የመጣ ነው፡፡ ትርጉሙም በጥብጥ፣ አዋሕድ፣ አደባልቅ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ "ጌቱ በሶ በጠበጠ" ለማለት " ጌቱ'ን በሶ ቡልቡሌ" ይሆናል ማለት ነው፡፡

#ቡልቡላ ሲሆን ደግሞ ሶስተኛ መደብ- ነጠላ ቁጥር ( #በጥባጭ) ማለት ነው፡፡

ይኸው ቡልቡላ እንድስያሜዋ የተለያዩ የኑሮ ደረጃ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ብሄር፣ ሐይማኖት፣ ባህል… ያላቸውን ሰዎች አንድ ላይ በጥብጣ፤ አዋህዳ አፋቅራ የያዘች ሰፈር መሆኗን አስመስክራለች

የቡልቡላ መሆን ሽልማት ነው፡፡

መልካም ህይወት ከምርጧ ሰፈራችን ጋር

@BBN_Info