2024-05-16 18:36:33
በዎላይታ ዞን ውዝፍ የወር ደመዝ ያልተከፋላቸውን ለመጠየቅ ሰልፍ የወጡ የመንግስት ሰራተኞች ድብደባና እስራት ገጠማቸው
በትናንትናው ዕለት የሶስት ወር ደሞዝ ባለመክፈሉ አደጋ ላይ ወድቀናል የሚሉ የዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ መንግስት ሰራተኞች በሰላማዊ ሰልፍ እስከ ክልሉ ርዕሰ መስተደድር ቢሮ ድረስ የሄዱ ሲሆን ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ አደባባይ እንዲወጡ ያስገደዳቸው የወረዳውን ሆነ የዞኑን መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠይቁም በቂ ምላሽ ባይሰጥም በድጋሚ ዛሬ ወደ ዞኑ የሄዱትን ፓሊስ እንዲያባርርና እንዲታሰሩ መደረጉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ እየሆነ ያለው ነገር የመንግስት ሠራተኛን ከእነ ቤተሰቦቹ ጭምር ለረሃብና ችጋር በማጋለጥ ወደ ጎዳና እንዲወጡ የማድረግ ስልታዊ አሠራር ነው። ብሎም የተማረ የሠው ሃይልን በማዳከም ሌላውን የማህበረሰብ ክፍልን ለመዝረፍና ለመጨቆን ሆነ ተብሎ እየተሠራ ያለ አምባገነናዊነትና ማሀይምነትን ለማስፋፋት ምቹ አጋጣሚዎችን ሁሉ አሟጠው የመጠቀም ህዝብን የማማረር አደገኛ ተልዕኮ ነው" በሚል ያምናሉ።
በመሆኑም የሚመለከተው አካል የሠራተኛውን እና ቤተሰብ ህይወት ለመታደግ ደሞዝና የተለያዪ ጥቅማጥቅም በማስከበርና በመክፈል፣ ትውልድ የማስቀጠል አስቸኳይ እና ቀዳሚ የነፍስ አድን ሥራ እንዲሠራ ስንል እኛም ሆንን ቤተሰቦቻችን ከሞት አፋፍና ጣር ላይ ሆነን እንደአንድ የመንግስት ሠራተኛ ጩሄታችንን ስናሠማ፣ በተራበ አንጀትና በደከመ ጉልበታችን በጠወለገ ድምፃችን ነው" ስሉ የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጿል።
በተቃራኒው የዎላይታ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ቢሆንም በአከባቢው ልማት ስራዎች ቆሞ በአብዛኛው መዋቅር ደመዝ መክፈል አለመቻሉ ለበርካቶች "ለምን" የሚል ጥያቄ ፈጥሯል።
በዎላይታ ዞን በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ደሞዝ ለመንግሥት ሰራተኞች ባለመክፈሉ ምክንያት በአብዛኛው መዋቅር ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ መንግስታዊ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ ተገልጋይ ህብረተሰብ ክፍሎችም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለመግባታቸው የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል።
ደሞዝ ባለመክፈሉ "አደጋ ላይ ወድቀናልና እኔም የመንግሰት ሠራተኛ ነኝ ልጆቼንና ቤተሰቦቼን አድኑልኝ" የሚል ጥሪ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ለተጨማሪ መረጃዎች join us https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
የውስጥ መስመር t.me/ayulaw
13.1K viewsAyu, edited 15:36