Get Mystery Box with random crypto!

Muhe tube .com

የቴሌግራም ቻናል አርማ amuukatube — Muhe tube .com M
የቴሌግራም ቻናል አርማ amuukatube — Muhe tube .com
የሰርጥ አድራሻ: @amuukatube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 176
የሰርጥ መግለጫ

Just feta
No live
Share ande join
Asteyayet kalachu bezi anagrugn
↓↓↓↓↓
@Halalboy2
@Halalboy

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-16 22:02:49 ለይለቱል ቀድር
==========
ክፍል:-②
ለይለቱል ቀድርን መቼ እንፈልጋት?
ለይለተል ቀድር እጅግ የምትገመተዋ ለሊት 27ኛዋ ለሊት ናት፣ ለዚህም ነብዩ
(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ማስረጃ መሆን ይችላል፡-
«ለይለተልቀድርን በ27ኛው ለሊት ውስጥ ፈልጓት»፡፡
ሙሐዲሱ ሸይኽ ሶሒሕ ብለውታል
*
ላሂቅ ቢን ሐሚድ እና ዐክረማ እንዲህ ብለዋል፣ ዑመር (ረድየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ብለዋል፣ «ከናንተ ማነው ለይለቱል ቀድር መች እንደሆነ የሚያውቅ?»

እነሱም መልሰው እንዲህ አሉ፣
«ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምተናል "እሷ ለይለቱል ቀድር
በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ናት፣ ሰባት ሲያልፍ፣ አልያም ሰባት ሲቀር" አሉ።

«ይህም 23ኛው ለሊት ወይም 27ኛው ለሊት»።
ምንጭ:- ሙስነድ አህመድ ቁ(2543)

«አንድ ሰው ወደ ነብያችን በረመዳን
መጥቶ እንዲህ አላቸው የ አላህ ነብይ ሆይ! እኔ ታማሚ ሽማግሌ ነኝ አላህ እንዲወፍቀኝ በ አንዷ ለሊት እዘዘኝ አሉ።
ነብያችንም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «27ኛዎን ለሊት ያዝ» አሉት።
ምንጭ:- ሙስነድ አህመድ ቁ(2149)

በሌላ ሐዲስ ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስርት ቀናቶች ፈልጓት በተለይ በጎደሎ በውትር ቀናት ማለትም በ21,23,25,27 እና በ29 ፈልጓት ብለውናል።

«ለይለተልቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ ለሊቶች በዊትሮቹ
ፈልጓት»፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ይህ ማለት ግን ከናካቴው በሸፍዕ (Even) ለሊቶችም ማለትም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ለማለት አይደለም፡፡

ይህንንም ከሚያስረዱን ማስረጃዎች አንዱ ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ለይለተል ቀድርን በረመዳን የመጨረሻዋ ለሊት ላይ ፈልጓት» ማለታቸው ነው፡፡

ስለ ለይለተል ቀድር በጣም ብዙ ዘገባዎችና በቀላሉ ወደ 40 የሚጠጉ ዘቅዎሎች አሉ ነገር ግን የመጀመረያ ምክሬ የመጨረሻዎቹን 10 ቀናቶች ሳትዘናጉ መፈለጉ በላጭ ነው ባይ ነኝ።

ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል» ብለዎልና አስሮቹን ቀን አደራ በርቱ ያጀማዓ።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
||
ክፍል:-③ ይቀጥላል
#ሼር_አድርጉት
#ወሰለሙ ዓለይኩም
=========
=========
ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉ
@hadit_h
29 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 22:02:48 ለይለቱል ቀድር
==========
ክፍል:-①
#ሼር_አድርጉት
ለይለቱ-ልቀድር ማለት ምን ማለት ነው?
«ለይለተል ቀድር ማለት በአጭሩ የመወሰኛይቱ ሌሊት ማለት ነው፣ ይች ለሊት ትልቅ ቀድር ወይም ደረጃ ያላት ለሊት ናት በተጨማሪም ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ናት።
||
የለይለቱል-ቀድር ደረጃዎች:-
①) ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرٌِ۝
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (1)

②) በርሷ ላይ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች በተለየና ምንዳው የበለጠ ነው።
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٌٍ۝
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (3)

③) በርሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-

تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٌٍ۝
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (4)

④) ለሊቷ ዒባዳህ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرٌِ۝
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (5)

⑤) የተባረከች ለሊት ናት።
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينٌَ۝
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (3)

⑥) በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜ እና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል፡፡
አላህም እንዲህ ብሏል፡-

فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٌٍ۝
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (4)

⑦) በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው፡፡

⑨) ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት
ነች፡፡
ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል»፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል፡፡
ኢብኑልቀይም (ረሒመሁላህ) ይችን ንግግር ተናገሩ:-
«ለይለተልቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እርሷን
ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር፡፡ #በረመዳን አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? እንዴት እዘናጋለሁ?!» አሉ።

ለይለቱልቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
ለይለተልቀድር የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው፣ ከረመዳንም ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳን ነብዩ (ሰለላሁ
ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ነው፡-

«ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ "እሷ በርግጥም
የመጨረሻው አስር ላይ ናት" ተባለኝ» ማለታቸው ነው፡፡
*
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡-
«በሱ (በረመዳን) ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች፣ የርሷን ኸይር
የተነፈገ በእርግጥም "ትልቅ ነገር" ተነፍጓል»፡፡
አስ-ሶሒሕ

ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጥር ይገባል፡፡
ፁሁፍ ሲንዛዛ አልወድም እንዳላበዛባችሁ
ክፍል:-② ይቀጥላል…
④) ለይለቱል ቀድርና ምልክቶቹ?
⑤) ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች?
⑥) የዚያች ምሽት ተወዳጅ ዱዓእ ምንድነው?
||
ሼር አድርጉት
#ወሰላሙዓለይኩም
==========
==========
ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉ
@hadit_h
28 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 ➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች
==============
ክፍል:-174
1) «ዙልም (ሰው መበደልን) ተጠንቀቁ! እርሱ የቂያም ቀን ጨለማዎች ሆኖ ይመጣልና»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ሙስሊም ዘግበውታል

2) «መቃብር ላይ አትቀመጡ፣ ወደ መቃብርም አትስገዱ»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ሙስሊም ዘግበውታል

3) «የአንድ ሰው እስልምናው ማማሩ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ኢብን ማጀህ
||
#ሼር_አድርጉት
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
@hadit_h
@hadit_h
28 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 ➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች
==============
ክፍል:-173
1) «እንቅልፍ ተኝቶ ወይንም ረስቶ ሶላት ያለፈው ሰው ባስታወሰ ሰኣት ይስገድ»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:- ቡኻሪ (597)

2) «ሰውየው በሚሰራው ወንጀል ሪዝቁን ይነፈገል»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:- ሶሒህ ኢብኑ ሒባን (4022)

3) ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረድየ-ል-ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ አሉ:- የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የመጨረሻ ንግግር «ሶላትን አደራ፣ ሶላትን አደራ» የሚል ነበር።
ምንጭ:- ሶሒሁል ጃሚዕ
||
#ሼር_አድርጉት
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
@hadit_h
@hadit_h
28 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32
የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ፖል ፖግባ በኢንስትግራም ገፁ ላይ ለ52
ሚሊዮን ተከታዩቹ በሂጃብ ምክንያት በህንድ ሙስሊም ሴቶች ላይ
የሚደርሰውን የመብት ረገጣ የሚያሳይ ቪዲዮ ስቶሪው ላይ ሼር ማድረጉን
ተከትሎ በህንድ ሂንዱስታን እና ሂጃብ ጠሎች " unfollow pogba " ዘመቻ
የተከፈተበት ሲሆን የአለም ሙስሊሞች ደግሞ " follow pogba " የሚል
ካውንተር ዘመቻ ከፍተው ሂጃብ ጠሎች የሚቀንሱትን ቁጥር እያስተካከሉት
ይገኛል::
ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድ ያዳርሱ
@hadit_h
25 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 ➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች
==============
ክፍል:-172
1) ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል:- "ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው"።
ሙስሊም ዘግቦታል

2) "የዙልሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና ከእናንተ አንድኛችሁ ኡድሂያን ማረድ ከፈለገ ፀጉሩን እና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ"።
ምንጭ:- ሙስሊም ዘግበውታል (1977)

3) "ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሰጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማእረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልህም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል"።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ሙስሊም ዘግበውታል
||
#ሼር_አድርጉት
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
@hadit_h
23 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች
==========
ክፍል:-167
1) «መልካም ስነምግባርና መልካም ጉርብትና፣ ቤትን ያሳምራሉ እንዲሁም እድሜንም ይጨምራሉ»።
ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:- ሲልሲለቱ ሶሒሀህ (519)

2) «በሙናፊቆች ላይ በጣም ከባድ ሶላቶች የዒሻ ሶላት እና የሱብሒ ሶላት ናቸው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ሙስሊም ዘግበውታል

3) «ከእያንዳንዱ ዋጂብ ሶላት ቡሀላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ከመግባት የሚያግደው ሞት ብቻ ነው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦ ሶሒሁል ጃሚዕ (6464)
||
#ሼር_አድርጉት
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ!
@hadit_h
18 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 የቀኑ 3ቱ ሀዲሶች
============
ክፍል:-166
1) «አዛን ሲባል ሁሉም የሰማይ በሮች ይከፈታሉ፣ በዛ ጊዜ የሚደረግ ዱዓ
ተቀባይ ነው»።
ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦ ሶሒሁል ጃሚዕ (818)

2) «ለሙአዚን የቂያማ እለት ሰውም ጂኑም እንዲሁም አጠቃላይ እርሱ አዛን ሲል በነበረበት ጊዜ የሰሙት ነገሮች ሁሉ ነገ ከአላህ ፊት ይመሰክሩለታል።»
ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)

3) «ወደቤትህ በምትገባ ግዜ «አሰላሙዓለይኩም» ብለህ ግባ ይሄን ካልክ በአንተም ላይ በቤተሰቦችህም ላይ የአላህ በረከት ይወርድባችኋል።»
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

ﺣﺴﻦ ﺻﺤﻴﺢ ‏(ﺍﻟﻜﻠﻢ ﺍﻟﻄﻴﺐ‏) (63)
||
#ሼር_አድርጉት
ቴሌግራም ቻነሉን ተቀላቀሉት
@hadit_h
18 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 ⛤ጀናዛ ላይ ዝሙት የፈፀመው

እባካችሁን ውድ የቻናል ቤተሰቦቼ እኔ ይሄንን ነገር ለናንተ አድርሻለሁ እናንተም ለወዳጅ ዘመድዎ እንድታደርሱ(forward/share) እንድታደርጉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ
በሌላ ነገር እስክንገናኝ ወሰላሙን አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
በዱአቹ አትርሱኝ
ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ
➱ @abukerr
╔════ ════╗
             @hadit_h
╚════ ════╝

•┈•❈••✦✾ቴሌግራማችንን ✾✦••❈•┈•
      Join & share
@hadit_h
✿✶┈┈┈┈•✶✶✾✶✶•┈┈┈┈✶✿
17 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:17:32 የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች
==========
ክፍል:-165
1) «ሰወችን በአብዛሀኛው ጀነት እንዲገቡ የሚያደርጋቸው አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ናቸው፣ ሰወችን በአብዛሀኛው ጀሀነም እሳት እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ምላስ እና ብልት ናቸው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ቲርሚዚ ዘግበውታል

❷) «ቀልብህ እንዲለሰልስ ከፈለግክ ዳሃን መግብ፣ የየቲምን ራስ ዳብስ (የቲምን እርዳ)»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦ ሶሒሁል ጃሚዕ (1410)

➌) «የሞቱ ሰወች ቀብራቸው ውስጥ በሚቀጡ ጊዜ ድምፃቸውን እንስሳቶች ይሰማሉ»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦ ሶሒሁል ጃሚዕ (1965)
||
#ሼር_ሼር
ቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉት
@hadit_h
20 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ