Get Mystery Box with random crypto!

ለይለቱል ቀድር ========== ክፍል:-② ለይለቱል ቀድርን መቼ እንፈልጋት? ለይለተል ቀድር | Muhe tube .com

ለይለቱል ቀድር
==========
ክፍል:-②
ለይለቱል ቀድርን መቼ እንፈልጋት?
ለይለተል ቀድር እጅግ የምትገመተዋ ለሊት 27ኛዋ ለሊት ናት፣ ለዚህም ነብዩ
(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ማስረጃ መሆን ይችላል፡-
«ለይለተልቀድርን በ27ኛው ለሊት ውስጥ ፈልጓት»፡፡
ሙሐዲሱ ሸይኽ ሶሒሕ ብለውታል
*
ላሂቅ ቢን ሐሚድ እና ዐክረማ እንዲህ ብለዋል፣ ዑመር (ረድየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ብለዋል፣ «ከናንተ ማነው ለይለቱል ቀድር መች እንደሆነ የሚያውቅ?»

እነሱም መልሰው እንዲህ አሉ፣
«ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምተናል "እሷ ለይለቱል ቀድር
በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ናት፣ ሰባት ሲያልፍ፣ አልያም ሰባት ሲቀር" አሉ።

«ይህም 23ኛው ለሊት ወይም 27ኛው ለሊት»።
ምንጭ:- ሙስነድ አህመድ ቁ(2543)

«አንድ ሰው ወደ ነብያችን በረመዳን
መጥቶ እንዲህ አላቸው የ አላህ ነብይ ሆይ! እኔ ታማሚ ሽማግሌ ነኝ አላህ እንዲወፍቀኝ በ አንዷ ለሊት እዘዘኝ አሉ።
ነብያችንም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «27ኛዎን ለሊት ያዝ» አሉት።
ምንጭ:- ሙስነድ አህመድ ቁ(2149)

በሌላ ሐዲስ ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስርት ቀናቶች ፈልጓት በተለይ በጎደሎ በውትር ቀናት ማለትም በ21,23,25,27 እና በ29 ፈልጓት ብለውናል።

«ለይለተልቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ ለሊቶች በዊትሮቹ
ፈልጓት»፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ይህ ማለት ግን ከናካቴው በሸፍዕ (Even) ለሊቶችም ማለትም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ለማለት አይደለም፡፡

ይህንንም ከሚያስረዱን ማስረጃዎች አንዱ ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ለይለተል ቀድርን በረመዳን የመጨረሻዋ ለሊት ላይ ፈልጓት» ማለታቸው ነው፡፡

ስለ ለይለተል ቀድር በጣም ብዙ ዘገባዎችና በቀላሉ ወደ 40 የሚጠጉ ዘቅዎሎች አሉ ነገር ግን የመጀመረያ ምክሬ የመጨረሻዎቹን 10 ቀናቶች ሳትዘናጉ መፈለጉ በላጭ ነው ባይ ነኝ።

ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል» ብለዎልና አስሮቹን ቀን አደራ በርቱ ያጀማዓ።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
||
ክፍል:-③ ይቀጥላል
#ሼር_አድርጉት
#ወሰለሙ ዓለይኩም
=========
=========
ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉ
@hadit_h