Get Mystery Box with random crypto!

🌹የሱና እህቶች የለውጥ ሚና🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeswnaehitochmena — 🌹የሱና እህቶች የለውጥ ሚና🌹 የ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeswnaehitochmena — 🌹የሱና እህቶች የለውጥ ሚና🌹
የሰርጥ አድራሻ: @yeswnaehitochmena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.34K
የሰርጥ መግለጫ

♡..አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ከመገላለጥ ተጠንቀቂ {{በአላህ ፍቃድ}} ከፈተናዎች ጠባቂሽ የሆነውን ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ!❥...
🍃═══ ¤❁✿❁¤ ═══🍃

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-04 09:08:22 በመረጋጋት ላይ አደራችሁን!!!

-فَعَلَيْكُمْ بِالتُؤَدَةِ
―――――――――――――
በዚህ ዘመን እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እውቀት ፈላጊና አስተማሪ ከሆኑ በርካታ ግለሰቦች በስፋት እያነሰ የመጣው በጥልቅ የማስተዋል፣ የመረጋጋትና በዋናነት ደግሞ የስነምግባር ጉዳይ ነው። እርጋታ፣ ብስለትና ስነምግባር የዲኑ አንድ አካል በማይመስል መልኩ ሆደ ሰፊነት በሚያስፈልግባቸው ርዕሶች ላይ በየቦታው በወንድሞቻችን መካከል የሚታዩ ለከት የሌላቸው ነቆራዎች፣ ስድቦችና ያለ አግባብ ስም ማጠልሸቶች ተበራክተዋል። ሰዎችን ወደ ሐቅ ለማድረስ አቋራጭ የሚመስሉንን በሙኻሊፎች አልያም ተሳስተዋል ብለን ባሰብናቸው ወንድሞች ላይ የሚሰነዘሩ መረን የለቀቁ የጥላቻ ሰበካዎች በተዘዋዋሪ ዳዕዋችንን እየጎዳው ነው። ሁሉንም በልክና በብስለት ማስኬድ አፅንዖት የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ከፊሉ በአቅሙ ልክ ውስን ዘርፎችን ሲሸፍን ሌላው ክፍተቱን እየሞላ ዳዕዋውን ማራመድ ካልተቻለ ትልቅ ክፍተት መፍጠሩ አይቀርም።
በዳዕዋው ውስጥ የተሳትፏችን ልክ በእውቀታችን መጠን የሚገደብ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። አንድ ሰው ስለሁሉም ተናግሮ ማስጠንቀቅና አዳርሶም ማስተማር አይችልም። አንተ የአቅምህን ከተወጣህ ሌላው ወንድምህም ከጎንህ የአቅሙን ካበረከተ ተጋግዘን በአላህ ፈቃድ በአጭር ግዜ ለውጥ ይመጣል። ነገር ግን እኔ የገባሁበት ካልገባህ፣ እኔ የታየኝ ካልታየህ፣ የኔን የዳዕዋ ስልት ካልተገበርክና እኔ ያስጠነቀኩትን ካላስጠነቀክ ብለህ ሽኩቻና ነቆራ በወንድሞችህ ላይ ከከፈትክ በተውሒድ ዳዕዋ ላይ እጅግ ከፍተኛ ችግር ትፈጥራለህ። መንገድህም ይረዝማል። ሸይኽ ኢልያስና መሰል ወንድሞች በዚህ ርዕስ ላይ የሚስተዋልባቸው እርጋታና ብስለት፣ ማስተዋልና ስክነት እንዲሁም መሰረታዉ እውቀት ላይ ትኩረት መስጠት ለብዙ ወጣት ዱዓቶች አስተማሪ ነው።
ሰዎች ዘንድ መታወቂያህ ስህተት መልቀምና ስህተት የመሰለህን በመሰብሰብ "ረድ" ማዘጋጀት ከዚያም በአቋራጭ መድረስ ሳይሆን መሰረታዊ የዐቂዳና ተያያዥ ርዕሶችን በማስተማር መሆን አለበት። በእያንዳንዱ ርዕስና አለመግባባት ላይ መልስ ካልሰጠው በተጨማሪም ተዕሊቅና ተድቂቅ ካላደረኩ ማለት እጅግ አስከፊ ውድቀት ውስጥ ይከተናል።
ከጥንት አበዎች አንስቶ እስከ አሁን ያሉ ሊቃውንቶች በቅድሚያ ህዝቡ ዘንድ የሚታወቁት በጀርሕና ተዕዲል ብቻ ሳይሆን በሚያሰራጩት እውቀት፣ በዒባዳቸው ትጋት፣ በስነምግባራቸው ምጥቀት ነው። እነዚህ ምስጉን ስብዕናዎች በነዚህ መልካም ባህሪያት ከመታነፃቸውም ጋር ከተለያዩ አንጃዎችና ግለሰቦች የሚነሱ ውዥንብሮችንና ማምታቻዎችን የአላህን ፊት ፈልገው፣ እውቀትና ስርኣትን በተላበሰ መልኩ መልስ ይሰጣሉ። ውጤቱም ምስጉን ይሆናል።

ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27
1.1K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 19:44:55 "የሒጃብ ቀን" ወይስ "የፈሳድ ቀን"?!

ኢስላም ራሱን የቻሉ ህልውናዎች ያሉት መሰረቱ የፀና በየግዜያቱ ልማድና ዘዬ በተከታዮቹ ከፍታና ዝቅታ ሙቀትና ቅሬታ የሚቀያየር እምነት አይደለም። መሰረታዊ ነጥቦቹን በየግዜው ብቅ ከሚሉ የከሀዲያን በቀል ተፅዕኖዎች ለመሸሽ በሚል ፈሊጥና ከዘመኑ ጋር እንራመድን ባዘለ ሙግት ፅኑ እሳቤው የሚገፈፍና በሸውራራ ምልከታና በዝንባሌዎች ማዕቀፍ የሚኮላሽ አይሆንም።

እርግጥ ነው ዘመናዊነትን ከኢስላም ጋር በማይጋጩ ነገሮች አጣጥመን ልንጠቀምበት ከዘመኑ ጋር ልንራመድ ህይወታችንን ልናቀልበትና ልናቀናበት ይገባል። ነገር ግን ኢስላምን ዘመናዊ እናድርገው ብለን ወደ ገደል የምንጎትተው እምነት ሊሆን በፍፁም አይችልም። አምላካችን አሏህ ይህን እምነት የደነገገውና የሰዎች መመሪያ ያደረገው እስከ ምፅዐት ቀን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዘመናቶች በተሻገሩ ቁጥር ኢስላምን በታወረ ልቦናችን የምንዘምትበት በአጠረ እውቀታችን የምንጠራራበት እምነት አይደለም። ፋይሉ ከ1400 አመታት በፊት ተዘግቷል።

የምዕራባዊያን ተፅዕኖ ያስበረገጋቸው በኢስላም ቀና ማለት ያቃታቸው በስሜት አለንጋ የተገረፉ ስብዕናዎች ኢስላምን እናዘምነው በሚል ወይም ቅቡልነቱን እናግነነው በሚል ሸውራራ እይታ ማህበረሰቡን ከትክክለኛው የኢስላም እሳቤ ወደ ወረደው አዘቅት እያወረዱት የቆመበትን ምንጣፍ እየጎተቱን ይገኛሉ። እውነት ነው አላህ እንዲህ ማለቱ ፦

"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሀይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈፅሞ አይወዱም " አል-በቀራ 120

ከዛሬ ነገ እየከነፈ ሙስሊሟ ሴት እየተንሸራተተች የት ነው ያለችው? አንዱን ሲያስጥሏት እየወረደች አንዱን እያነሳች በመጨረሻም የእነሱን መንገድ በምልአተ ልቦናዋ ኮቴ በኮቴ እየተከተለች ትጓዝ ይዛለች። መታገል የመጀመሪያው ፈተና ላይ መሆኑን አላወቀችም። ድንበርህን አሳልፈህ ከሰጠህ ቡኃላ በሜዳህ ለሚጫወቱ አካላት መጫወቻ ትሆናለህ። አመቱን ሙሉ የሒጃብ ቀን ብለን ብናከብር የሒጃብን ልቅና በዚህ መንገድ ልናስጠብቀው በፍፁም አንችልም። ይባስ ብሎም ይህ አካሄድ ሴቶችን ከትክክለኛው የሒጃብ መፍሁምና ጭብጥ እያራቃቸው መጥቷል። ለዚህም ነው በየቦታው የቻይና ሱሪና ጠባብ ቀሚስ የታጠቁ ሙልጭልጭ ያለ ሂጃብ የለበሱ በጥቅሉ ማንነታቸው ግራ የገባቸው ሴቶች እንደ አሸን የፈሉት። ሀይ ባይ አጥተው ነውራችን የሆኑት። ግዜው በገፋ ቁጥር ነገሩም እየከፋ አበረታችና አጨብጫቢው እየፋፋ ሴቶችንም ለሐራም ማደኑም እየገፋ መጥቷል።

ፀጉራቸውን እንኳን በተገቢው መልኩ ያልሸፈኑ ብጥስጣሽ ጨርቆችን ከአናታቸው ላይ ጣል ያደረጉ በሰፋፊ ልብሶች መሸፈን ያለበት አካላቸው በጠባብና ባለ ወገብ ማሰሪያ ቀሚሶች ያሰሩና አካላቸውን የማይሰትሩ ቀሚሶች ያጠለቁ ከዚህ ሲከፋም ጠባብ ሱሪዎች ታጥቀው ብቅ የሚሉ እህቶችን ሰብስቦ "የሒጃብ ቀን" እያሉ ማጃጃል ትልቅ ውርደት ነው። የንፁህ ሴት ልጅ ክብርና መገለጫ የሆነውን ጌታዋን የምታመልክበትን ዒባዳ የሒጃብ fashion show በሚል ቀልድና ሞኝነት በወንዶች መንጋ መሀል ሲያመላልሷት እንዲሁም ቧልትና ዛዛታ በበዛበት መድረክ ላይ ወንድና ሴት ፍጥረቶች ያለ ግርዶሽ አፋጠው በሜክአፕ፣ በሊፒስቲክና .....የተበከለ ፊት በቅጡ ያልተሰተረ ማንነት የተከማቸበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን ተብሎ ይሰየማል? በነሺዳ ስም የሚቅለሰለሱ ፓንክ ቁርጥ ሙነሺዶች የሚጣዱበት አብዛኞዎቹ ታዳሚያን ትክክለኛውን የሒጃብ መስፈርት ያላሟላ ሒጃብ ለብሰው የሚታደሙበት ፕሮግራም እንዴት የሒጃብ ቀን መሰናዶ ሊሆን ይችላል? በዚህ የፈተና ነፋስ በከፍተኛ ፍጥነት በሚነፍስበት ዘመን እሳትና ጭድን አቀራርቦ ደህና ምክር እንኳን መስጠት ከባድ መፍሰዳ ያስከትላል በሚባልበት እውነታ ከዛዛታው መሀል ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? ምን አልባት ፕሮግራሙን ኢስላማዊ ለማስመሰል አንዲት ሙሐደራ ቢጤ ነገር ጣል ሊያደርጉባት ይቻል ይሆናል ይህም መሰረቱ በወደቀ ቤት ላይ ሚስማር እንደመምታት ነው።

እውነታውን ስንመለከት "ዓለም አቀፍ የሂጃብ ቀን" ተብሎ በፌብራሪ 1 የሚከበረውን በዓል አንዲት በአሜሪካ የምትኖር ትውልዷ ባንግላዲሽ ዜግነቷ አሜሪካዊ የሆነች በ 11 አመቷ ወደ ሀገረ አሜሪካ ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰዳ የምትኖር እንስት በሂጃቧ ምክንያት በሚደርስባት ጫና ያስጀመረችው የሚዲያ ዘመቻ መሆኑ ነው። ማንም ቢሆን መልካም አላማን አንግቦ አንዳች ነገርን ይዞ በዲን ስም ከመነሳቱ በፊት በሸሪዓ ሚዛን ተለክቶና ተገምግሞ የኢስላም ሊቃውንቶችን ትክክለኛ ይሁኝታ ቁርኣንና ሐዲሥን አስደግፎ መስለሓና መፍሰዳው ታይቶ መሆን አለበት። የቢድዓ ጉዳይ ከሆነ ግን ምንም አይነት የቅቡልነት መንገድ አይኖረውም።

ሒጃብ አላህ ለሴቶች የደነገገው ጥበባዊና ፍትሓዊ የሆነ ሸሪዓዊ ልባስ ነው። አንዲት ሴት የጥብቅነትና የጨዋነት ምልክት ነው። በዚህ ርዕስ ላይ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ የኢስላም ልሂቃንና ሰባኪያን ሴቶችን ስለ ትክክለኛው ሒጃብ ሊያስተምሩ የመዳኛ መንገድ መሆኑን ሊጠቁሙ የክብሯ፣ የሀሴቷና የልቅናዋ ሰበብ መሆኑን ሊያስገነዝቧት ይገባል።

ነገር ግን አመት ጠብቆ የሒጃብ ቀን ብሎ ማክበርና ከዚህም የባሰው ደግሞ የዛን እለት ብቻ ሒጃብ የሚለበስበትና የተለያዩ እምነት ተከታዮችም እንደ ተራ ፌስቲቫል ሒጃብ ያሉትን ጨርቅ ጣል አድርገው ሲቀልዱ በተነሱት ፎቶ ሶሻል ሚዲያዎችን ሲያጨናንቁ ማየት ከባድ የሆነ ቢድዓና በውስጡም ተዘርዝረው የማያልቁ መፍሰዳዎችን ያካተተ ነው። ይህን ተግባር በፅኑ የሚኮኑንበት ሌላው ምክንያት በተለያዩ ቀናት እንዳሻቸው ክብረ በዓል ከሚያሰናዱ ከሀዲያን ጋር መመሳሰል መንገዳቸውንም መከተል ስላለበት ነው። ኢስላምም ከተደነገጉለት በዓላት ውጪ የተለየ ክብር በዓላትን በየትኛውም መልኩ አያስተናግድም።

ይህን መሰል ነገሮችን የሚያከብሩ ሰዎች በብዛት መስለሓ አለው በሚል ሙግት መሆኑ እርግጥ ነው። ይህን ሲሉ መሰለሓና መፍሰዳን ሚዛን ላይ አስቀምጦ ለመገምገም የሚያስችል የሸሪዓ እውቀትና የቀደመ ኢስላማዊ ልቀትና ምጥቀት ላይ ያሉ ሰዎች አለመሆናቸው ደግሞ ያስተዛዝባል። መፍሰዳና መስለሓን በሸሪዓ ምልከታ፣ በረቀቀ ግምገማና እይታ አላህን ፈሪ በሆነ ልቦና ተመልክተው ብይን መስጠት ያለባቸው በዘርፉ የተካኑ የኢስላም ልሂቃን ብቻ ናቸው። ከዚህ ውጪ በዲን ስም ቢዝነሱን እያጧጧፈ መስለሓ አለው ለሚልሽ ባተሌ ጆሮ አትስጪ ማመዛዘን የሚችለውን ዐቅልሽ አታከራይው ይልቁንም ለዲንሽና ለክብርሽ ዋጋ ስጪ። የመፍሰዳው ብዛት አለች የሚሏትን ጭላንጭል መስለሓ ላይ ቢቆለል አፍነው ይገሏት ነበር። ይህ የነሺዳና ዳንኪራ ጭብጨባ፣ በወንዶች መሀል በፋሺን ሾው ስም ያለ ዕፍረት የሒጃብን መስፈርት በማያሟላ በተጋጌጠና በተቆራረጠ የጨርቅ ቅጥልጣይ ልብስ መመላለስና መሰባበር፣ ኢኽቲላጥና ዛዛታ ሌሎችም ሙንከራቶች እውነት ወደ አላህ የሚያቃርበን ዒባዳ ነውን? በፍፁም!!!

#yes_to_hijab_no_to_hijab_day

ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ
https://t.me/abdurezaq27
1.3K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 13:35:43 ☞ወደ ኢስላምና መጣራትና "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት?!

ከኢስላም ውጪ ያሉ የማህረሰብ ክፍሎችን እምነታቸውን መሰረት ያደረጉ በዓላቶቻቸውን ሲያከብሩ "እንኳን አደረሳቹህ!" አልያም "እንኳን ደስ አላችሁ!" የሚሉ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ግለሰቦች ምን አልባት አብዛኞቹ አንድም ቀን ተሳስተውም ቢሆን እነዚህን ሰዎች ወደ ኢስላም ተጣርተው የማያውቁ ናቸው። ሞራሉም የላቸውም።

ግዴታ የሆነውን ሰዎችን ወደ ኢስላም መጣራትን ትተው በተከለከለው የኩፍር ድግስ ላይ የሚረባረቡት ለምን ይመስላችኋል? ለዚህም ጀብዳቸው የውስጥ ሽንፈታቸው የወለደውን ሆደ ሰፊነታቸውን እንደ ሰበብ ሲያባክኑና ሌላውን በአክራሪነት ሲፈርጁ ይስተዋላል።

በክህደቱና በኩፍሩ ላይ "እንኳን ደስ አለህ!" ያልከውን ሰው በምን አፍህ ነው "ይህ ያለህበት እምነት ስህተት ነው!" ለማለትና ወደ ኢስላም ለመጥራት ሞራሉ የሚኖርህ?! ምን አልባት ይህ ግለሰብ ኢስላምን ያወቀ እለትና አሏህ ወደ ኢስላም የመራው ቀን ይታዘብኃል። ከሁሉ በላይ ደግሞ አሏህ የምትሰራውን ይመለከታል!!!

እስኪ እናስተውል!

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا (140)


"በእናንተም ላይ በመፅሀፉ ውስጥ የአሏህን አንቀፆች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ግዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ። እናንተ ያን ግዜ ብጤያቸው (አምሳያቸው) ናችሁና። አሏህ መናፍቃንን እና ከሓዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና።" [ሱረቱ-ል አን' ኒሳእ: (140)]

የአሏህ አንቀፆች ሲካድባቸውና ሲላገጥባቸው እየተመለከቱ አብሮ መቀመጥ በጥብቅ ከተከለከለና እንዲሁም በዚህ በክህደት ድርጊት ላይ አብሮ መቀማመጥን ካልተዋችሁ የእነርሱ የከሃዲዎቹ አምሳያዎች ናቹህ ከተባለ፣ በእነዚህ የአሏህ አንቀፆች ሲካድባቸውና ሲላገጥባቸው "እንኳን ደስ አላቹህ!" እና "እንኳን አደረሳቹህ!" ማለትስ እንዴት ሊሆን ነው? ጥንቃቄ ያስፈልጋል!!

ለዚህም ሲባል ነው አንድን ግለሰብ አስቀያሚውን ዝሙት ሲፈፅም፣ ሲሰርቅ፣ ሲዋሽና የመሳሰሉ ከባባድ ወንጀሎችን ሲተገብር "እንኳን ደስ አለህ በርታ!" ከማለት በላይ በክህደት በዓላት ላይ "እንኳን ደስ አለህ!" ማለት የበረታ ወንጀል እንደሆነ ኢብኑል ቀይዪምን የመሳሰሉ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች የሚጠቁሙት!!
29/4/2014
https://t.me/abdurezaq27
1.6K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 09:38:04
ሸይኽ ሷሊሕ አል-ዑሰይሚይ

"ጁሙዓ አሏህን የመታዘዝ ቀን ናት። በእርሷ ውስጥ አሏህ ዱዓን የሚቀበልበት፣ ባሪያው የጠየቀውን የሚሰጥበት፣ ምኞቱን የሚያገኝበትና ፍላጎቱን የሚቸርበት ለየት ያለች ወቅት አለች። ስለዚህ ከእርሷ አትዘናጉ። ይህችን ወቅት በጁሙዓ እለት መገባደጃ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ተጠባበቋት። አላህ እንደሚቀበላቹህ እርግጠኞች ሆናችሁ ዱዓን አድርጉ። ጌታችሁ ቸር ነው።"
https://t.me/abdurezaq27
727 views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 15:45:23 "እኔ ብቻ ትክክል ነኝ!"
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
☞ኢብኑል ቀይዪም፦

በሁሉም መልኩ ተበዳይና ሐቅ ላይ ነኝ የሚሉ ሰዎች እጅግ በርካታ ናቸው። ነገሩ ግን እንደሚገምቱት በፍፁም አይሆንም። እንደውም ይህ ግለሰብ በአንድ በኩል ሐቅ ሊኖረውና በከፊል ደግሞ በደልና ባጢል ሊኖርበት ይችላል። ባላንጣው ዘንድ ደግሞ ሐቅና ፍትህ ሊኖር ይችላል። አንድን ነገር መውደድህ እውርና ዲዳ ያደርጋል። የሰው ልጅ ነፍሱን በመውደድ ላይ የተፈጠረ ነው። የነፍሱን መልካሟን እንጂ ሌላን አይመለከትም። ተቃራኒውን ይጠላል። የተቃራኒውን መጥፎ ነገር እንጂ አይመለከትም። እንደውም ራስ ወዳድነቱ በርትቶበት የነፍሱን ክፋት እንደ መልካም መመልከት ይጀምራል። ልክ አሏህ እንዳለው፦

{أفمن زين له سوء عمله فرآه حسناً}
سوع؊ فاءع

"መጥፎ ስራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?)"

በዚህም ባላንጣው ላይ ያለው ጥሩ ጎን መጥፎ እስኪመስለው ድረስ ጥላቻው ይበረታል።

ለዚህም ሲባል እንዲህ ተብሏል፦ "በጥላቻ ዓይናቸው ተመለከቱት እንጂ በመልካም ዓይን ቢመለከቱ ኖሮ የጠሉትን ነገር ባወደሱ ነበር!"

ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27
1.2K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 12:10:12
ሸይኽ ሷሊሕ አል-ዑሰይሚይ

"ጁሙዓ አሏህን የመታዘዝ ቀን ናት። በእርሷ ውስጥ አሏህ ዱዓን የሚቀበልበት፣ ባሪያው የጠየቀውን የሚሰጥበት፣ ምኞቱን የሚያገኝበትና ፍላጎቱን የሚቸርበት ለየት ያለች ወቅት አለች። ስለዚህ ከእርሷ አትዘናጉ። ይህችን ወቅት በጁሙዓ እለት መገባደጃ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ተጠባበቋት። አላህ እንደሚቀበላቹህ እርግጠኞች ሆናችሁ ዱዓን አድርጉ። ጌታችሁ ቸር ነው።"
https://t.me/abdurezaq27
910 views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 20:05:16 የሸረሪት ቤትና የጣዖታዊያን ምሳሌ!

አጫጭር የተውሒድ ትምህርቶች

☞ቁጥር ①

ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27
1.4K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 10:31:23
የማለዳ ፈዋኢዶች¹¹

"ታላላቅ ስብእናዎችን መገንባትና ማነፅ ከፈለግን በዲን የታነፁ እናቶችን ልናፈራ ይገባናል። ይህን ታላቅ ትውልድ ማግኘት የምንችለው ሴቶችን ዲናቸውን በማስተማርና በኢስላማዊ ተርቢያ ማሳደግ ከቻልን ብቻ ነው። ነገር ግን ሴቶቻችንን ዲናቸውን የማያውቁ ሆነው በመሀይምነትና ፅልመት ላይ ከተውናቸው በፍፁም ታላላቅ የኢስላም ስብእናዎችን እናፈራለን ብለን መጠበቅ የለብንም።"

~ #آثَار ابن باديس رحمه الله (٢٠١/٤)
https://t.me/abdurezaq27
1.5K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 09:47:27 ☞ጣዕረ—ሞት

ሞት የተጣደው ሰው ላይ መላእክቶች ይወርዳሉ። ከአጠገቡም ይቀመጣሉ። ወደ ሞት እየተጓዘ ያለው ሰውም በአይኑ ይመለከታቸዋል። እርሱ ዘንድ ያወራሉ። ከጀነት ወይም ከእሳት የሆነን ሐኑጥና ከፍን ይይዛሉ። ማቹ ዘንድ ያሉ ሰዎች በክፉም በመልካምም የሚያደርጉትን ዱዓ ተቀብለው አሚን ይላሉ። ጣዕረ ሞት ላይ ለሆነው ሰው ሰላምታን ያቀርቡለታል። ሰውዬውም ሰላምታውን በአንደበቱ አልያም በምልክት መናገርና ማመላከት ካልቻለ ደግሞ በቀልቡ ይመልስላቸዋል። በእርግጥም ጣዕረ ሞት ላይ ካሉ ሰዎች ይህን አይነት ነገር ተከስቷል። "አህለን ወሰህለን እንኳን ደህና መጣችሁ! እነዚህ ፊቶች" ብለዋል። ሸይኻችን ጣዕረ ሞት ላይ ከነበሩ ሰዎች ተነግሮት ይሁን አይቶ አላውቅም እንዲህ ብሎ ነግሮኛል "ጣዕረ ሞት ላይ ያለ ሰው "ዐለይከ ሰላም" እንዳሉ ሰምቻለሁ።

ኢብኑ አቢ ዱንያ ይህን ጠቅሷል "ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ የሞተበት ቀን ላይ ቤተሰቦቹን "አስቀምጡኝ" አለ። ቤተሰቦቹም "አስቀመጡት"። እርሱም "እኔ ነኝ አዘኸኝ ትእዛዝህን ያጓደልኩ! እኔ ነኝ ከልክለኸኝ ያመፅኩ" እያለ ሶስት ግዜ ደጋገመ። ከዚያም "ነገር ግን ላ ኢላሃ ኢልለ ላህ" አለ። ከዚያም አይኑን ከፍ አድርጎ በአትኩሮት ወደ ላይ ተመለከተ። አጠገቡ ያሉ ቤተሰቦቹም "የአማኞች መሪ ሆይ! በጣም አፍጥጠህ በአትኩሮት እየተመለከትክ ነው ምንድነው?" አሉ። እርሱም "እኔ አሁን ሰውም አጋንንትም ያልሆኑ አካላቶች ቀርበው ይታዩኛል" አለና ሞተ።

ፈዳለቱ ኢብኑ ዲናር እንዲህ ብለዋል "ሙሐመድ ኢብኑ ዋሲዕን ጣዕረ ሞት ላይ ሆኖ አገኘሁት። እንዲህ እያለ ነበር "የጌታዬ መላእክቶች እንኳን ደህና መጣቹህ! ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ! ከዚህ በፊት አሽትቼው የማላውቀውን ጥሩ መኣዛ እያሸተትኩ ነው።" አለና ወዲያውኑ አይኑን አንጋጠጠና ሞተ።"

አ-ር'ሩሕ ኢብኑል ቀይዪም

ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/abdurezaq27
1.4K viewsedited  06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 10:56:36 አል-ፈታዋ ቁጥር②

☞ጥያቄ፡ የአባቴን ሚስት ባሌ ሰላም ማለት ይችላል?

☞መልስ፡ ሸይኽ ረቢይዕ ኢብኑ ሀዲይ አል-መድኸሊይ፦

" ከእናትሽ ውጪ ያለች የአባትሽ ሚስት ለባልሽ መሕረም አይደለችም። ነገር ግን እናትሽ ለባልሽ መሕረም ናት። እናትሽን መጨበጥ አንድ ቦታ ላይ ለብቻቸው አብሯት መሆን ማግለል ይችላል። ያንቺ እናት ልክ እንደ እናቱ ነው የምትቆጠረው። እናትሽ ከመሕረሞቹ መካከል ናት። ነገር ግን ከእናትሽ ውጪ ያሉ የአባትሽ ሚስቶች ጋር ይህን ማድረግ ይከለከላል። እንደው አባትሽ ቢሞት ወይም ሚስቱን ቢፈታ ያንቺ ባል ከእናትሽ ውጪ ያለችን የአባትሽን ሚስት ሊያገባት ሸሪዓው ይፈቀድለታል። እናትሽን ግን አይፈቀድለትም። እሱ አንቺን በማግባቱ ምክንያት ያንቺ እናት ለዘልአለም በሱ ላይ ሐራም ትሆናለች።"

【 كتاب - فضل العلم والعلماء صفحة رقم : ٢٠٤ 】

•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•
https://t.me/abdurezaq27
1.5K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ